Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way






























Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህቺን አንቀፅ አነበቡ {እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሀፉን ያወረደ ነው። ከእርሱ (ከመጽሐፉ) ግልጽ የሆኑ አንቀጾች አሉ። እነሱ የመጽሀፉ መሠረቶች ናቸው። ሌሎችም ተመሳሳዮች አሉ። እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ማሳሳትን በመፈለግና ማጣመምን በመፈለግ ከርሱ የተመሳሰለውን ይከታተላሉ። (ትክክለኛ) ፍቺውንም አላህ ብቻ እንጂ ሌላ አያውቀውም። በዕውቀትም የጠለቁት "በርሱ አምነናል፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው" ይላሉ። የአእምሮ ባለቤቶችም እንጅ (ሌላው) አይገሰጽም።} አላህ በዚህ አንቀፅ ውስጥ በነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ቁርኣንን ያወረደው እርሱ አላህ መሆኑን ይናገራል። ከቁርኣን ውስጥም መልእክታቸው ግልፅ የሆኑና ያለምንም ማደናገር ድንጋጌያቸው የታወቁ አንቀፆች አሉ። እርሱም የመጽሐፉ መሰረትና በልዩነት ወቅት የሚዳኝ ምንጭ ነው። ቁርኣን ውስጥ በርካታ ትርጓሜን የሚሰጡ አሻሚ አንቀፆችም አሉ። እነዚህ አንቀፆችን አንዳንድ ሰዎች ወይ በትርጓሜው ይደናገራሉ ወይም ከሌላ አንቀፅ ጋር እንደተጋጨ ያስባሉ። ቀጥሎ አላህ ሰዎች ከነዚህ አንቀፆች ጋር ያላቸውን መስተጋብር አብራራ። እነዚያ ልቦቻቸውን ከሀቅ መጣመም የተጠናወተው ሰዎች ሰውን ማሳሳትና ብዥታን ማቀጣጠል በመፈለግ ግልፅ የሆኑትን አንቀፆች በመተው አሻሚ የሆኑትን አንቀፆች ይወስዳሉ። ይህንንም ያደረጉት ዝንባሌያቸውን በሚስማማ መልኩ መፍታትን በመፈለጋቸው ነው። በእውቀት የፀኑት ግን እነዚህን አሻሚ አንቀፆች ያውቃሉ ፍቻቸውንም ወደ ግልፅ አንቀፆች ይመልሳሉ፤ ከአላህ ዘንድ ስለሆነም እርስ በርስ ምንም መጋጨትና ማደናገር ሊከሰት እንደማይችል ያምናሉ። ነገር ግን የንፁህ አይምሮ ባለቤት ካልሆነ በቀር ሊገሰፅም ሆነ ሊመከር እንደማይችል አላህ ገለፀ። ቀጥለው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለአማኞች እናት ዓኢሻህ - አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና - "እነዚያ አሻሚ አንቀፆችን የሚከታተሉትን ከተመለከተች አላህ {እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው} በማለት የጠቀሳቸው ናቸውና ተጠንቀቋቸው አታድምጧቸው።" አሏት።
ከሙሽሪኮች የሆኑ ሰዎች ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጡ። አብዝተው የገደሉና ዝሙት የፈፀሙ ነበሩ። ለነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: የምትጣራው ኢስላምና አስተምህሮቶቹ መልካም ጉዳይ ነው። ነገር ግን የወደቅንበት ሺርክና ከባድ ወንጀል ለርሱ ማስማሪያ አለውን? ወንጀላቸው ከመብዛቱና ከመተለቁ ጋርም አላህ ከሰዎቹ ተውበታቸውን እንደተቀበለ የሚጠቁሙ ሁለት አንቀፆች ወረዱ። ይህ ባልነበር ኖሮ በክህደታቸውና ጥመታቸው ላይ ይቀጥሉ ነበር። ወደዚህ ሃይማኖትም አይገቡም ነበር።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መካ የተከፈተ እለት ለሰዎች ኹጥባ አደረጉ። እንዲህም አሉ፦ እናንተ ሰዎች ሆይ! አላህ ከናንተ ላይ የድንቁርናን ዘመን ኩራት፣ ትዕቢትንና በአባቶች መኮፈስን አስወግዷል። ሰዎች ሁለት አይነት ብቻ ናቸው። ወይ አማኝ፣ በጎ፣ አላህን ፈሪና ለአላህ ባሪያ የሆነ ነው። ይህ ግለሰብ ሰዎች ዘንድ የተከበረ ዘርና ጎሳ ባለቤት ባይሆን እንኳ አላህ ዘንድ የተከበረ ነው። ወይም ደግሞ ከሀዲ፣ አመፀኛና ጠማማ ነው። ይህም ስልጣንና ክብር ያለው ከተከበረ ዘር እንኳ ቢሆን አላህ ዘንድ ከምንም ነገር ጋር የማይስተካከል የተዋረደና የዘቀጠ ነው። ሰዎች ሁሉ የኣደም ልጆች ናቸው። አላህም ኣደምን ከአፈር ነው የፈጠራቸው። መሰረቱ ከአፈር የሆነ ደግሞ በራሱ ሊኮራና ሊደነቅ አይገባውም። የዚህም ማረጋገጫ እንዲህ የሚለው የአላህ ንግግር ነው፦ {እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ። እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ። አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው። አላህ ግልፅን አዋቂ ውስጥንም አዋቂ ነው።} [ሑጁራት: 13
ተከታዩ አንቀፅ በወረደ ጊዜ: {ከዚያም ከድሎታችሁ ሁሉ በዚያ ቀን ትጠየቃላችሁ።} ማለትም አላህ በናንተ ላይ ለዋለላችሁ ፀጋ ማመስገናችሁን የምትጠየቁ ናችሁ። ዙበይር ቢን አልዓዋም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ስለማንኛው ድሎት ነው የምንጠየቀው? እነዚህ ሁለት ፀጋዎች ለመጠየቅ የሚያነሳሱ አይደሉም'ኮ እነርሱም ተምርና ውሃ ናቸው።" ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "እናንተ በዚህ ባላችሁበት ሁኔታ ላይ ከመሆናችሁም ጋር ስለነዚህ ፀጋዎች ትጠየቃላችሁ። እነዚህ ሁለቱም ከአላህ ትላልቅ ፀጋዎቹ መካከል ናቸውና።" አሉ።
ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቁርአንን ሽምደዳውን አሳምሮ፤ አስተማማኝ በሆነ መልኩ፤ ውብና ቆንጆ አድርጎ የሚያነብ ሰው በመጪው ዓለም ያለው ምንዳ ደረጃው ታዛዥና የተከበሩ ከሆኑ መላእክቶች ጋር እንደሆነ፤ ቁርአንን የመሸምደድ አቅሙ ደካማ ስለሆነ ቁርአን ማንበብ በርሱ ላይ ከባድና አስቸጋሪ ሆኖበት እየተንተባተበና እየመላለሰ የሚያነብ ከመሆኑም ጋር ሳያቋርጥ ዘውትር የሚያነብ ሰው ደሞ ለርሱ ሁለት ምንዳ እንዳለው ተናገሩ። አንዱ ምንዳ የማንበቡ ምንዳ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የመላለሰበትና ተቸግሮ የማንበቡ ምንዳ ነው።
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቁርአንን የተማረ፣ በማንበብም ይሁን በቃል ሽምደዳ ማንበቡን ያዘወተረን ሰው ግመሉን ጉልበቷ ላይ በገመድ እንዳሰረ የግመል ባለቤት መሰሉት። ግመሏን በአግባቡ ከተቆጣጠረ እንደያዛት ይቀጥላል። ገመዱን ከፈታው ግን ግመሏ ትሄዳለችም ታመልጣለችም። የቁርአን ባለቤትም ካነበበው ያስታውሰዋል። ቁርአንን በአግባቡ ካልጠበቀ ግን ይረሳዋል። በአግባቡ ቁርአንን እስከተጠባበቀ ድረስም ሒፍዙም ከመኖር አይወገድም።
መልአኩ ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ተቀምጦ ሳለ ከሰማይ በር ሲከፈት እንደሚያሰማው አይነት ድምፅ ሰማ። ጂብሪልም ራሱንና አይኑን ወደ ሰማይ ቀና አደረገ። ቀጥሎ ለነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና -ይህ የሰማይ በር ዛሬ እንደተከፈተና ከዚህ ቀን በፊትም በፍፁም ተከፍቶ እንደማያውቅ ነገራቸው። ከሰማይም ወደ ምድር ከመልአኮች መካከል ከዛሬ በቀር ወርዶ የማያውቅ አንድ መልአክ ወረደ። መልአኩም ለነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሰላምታን አቀረበና እንዲህ አላቸው: ከአንተ በፊት ለማንም ነቢይ ባልተሰጡና ለአንተ ብቻ በተሰጠህ ሁለቱ ብርሃኖች አበስርሃለሁ። እነርሱም: የፋቲሓ ምዕራፍና የበቀራ ምዕራፍ የመጨረሻዎቹ ሁለት አንቀጾች ናቸው። አስከትሎም መልአኩ እንዲህ አለ: አንድም ሰው ከነርሱ አንድ ፊደል እንኳ ብትሆን ካነበበ አላህ በውስጧ ያለውን መልካም ነገር፣ ተማፅኖና ፍላጎት ይሰጠዋል።
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቁርአንን አዘውትሮ በመቅራት ላይ አነሳሱ። ቁርአን የትንሳኤ ቀን ለሚያነቡትና በርሱ ለሚተገብሩ ሰዎች ያማልዳል። ቀጥለውም የበቀራንና የአሉ ዒምራንን ምዕራፎች በማንበብ ላይ ጠንከር አድርገው አነሳሱ። ስለሚመሩና ስለሚያበሩም አብሪዎች ብለው ሰየሟቸው። እነርሱን የማንበብ፣ ትርጉማቸውን የማስተንተንና ውስጣቸው ባለው የመተግበር ምንዳና አጅርም የትንሳኤ ቀን እንደ ሁለት ደመና ወይም ሌላ ጥላ ወይም እርስ በርስ ተጠባብቀው ክንፋቸውን እንደዘረጉ ሁለት የበራሪ መንጋ ተመስለው ባለቤቶቻቸውን አስጠልለው የሚከላከሉለት መሆናቸውን ተናገሩ። አስከትለውም ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የበቀራን ምዕራፍ አዘውትሮ በመቅራት፣ ትርጉሙን በማስተንተንና ውስጡ ባለው በመስራት ላይ አጠንክረው አነሳሱ። ይህም ውስጡ በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ትልቅ በረከትና ጥቅም ስላለው እና ይህንን መተውም የትንሳኤ ቀን ቁጭትና ፀፀት ይዞ ስለሚመጣ ነው። ከዚህ ምዕራፍ ደረጃዎች መካከልም ደጋሚዎች ይህንን ምዕራፍ የሚቀራን ሰው ሊጎዱ አለመቻላቸው ተጠቃሽ ነው።
አቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳወሱት: አንድ ሰውዬ ሌላ ሰው የ{ቁል ሁወሏሁ አሐድ}ን ምዕራፍ ሲያነብ ሰማ። ምሽቱን ሁሉ ሌላ ምዕራፍ ሳይጨምር እርሷን ብቻ ነበር እየደጋገመ የሚያነበው። የነጋም ጊዜ ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በመምጣት ይህንን አወሳላቸው። የጠያቂው አነጋገርም ምዕራፏን ያሳነሳት ይመስላል። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አፅንዖት ለመስጠት በመማል "ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! እርሷ የቁርአንን ሲሶ ትስተካከላለች።" አሉ።