Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way

Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
ዐብደላህ ቢን መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - {በእርሱም ውስጥ (ከትክክለኛ መንገድ) በመዘንበል በዳይ ሆኖ (ማንኛውንም ነገር) የሚፈልግ ሰው ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን።} [አልሐጅ: 25] በሚለው የአላህ ቃል ዙሪያ እንዲህ ማለታቸውን ገለፀ: "አንድ ሰው በሐረም መካ ላይ በምላስ ወይም ሆን ብሎ በመግደል አላህ እርም ያደረገው በሚደፈርበት መልኩ መጥፎን ስራ ለመስራት በነፍሱ ቢያስብና ቢቆርጥ ይህን ሊያደርግ የቆረጠው በየመን ከሚገኘው የዓደን ከተማ ሆኖ ቢሆንና ባይሰራው እንኳ በዚህ ምክንያት አላህ በአሳማሚ ቅጣቱ ሊቀጣው የተገባ ይሆናል። ለዚህ ቅጣት ማሰቡ ብቻ በቂ ነው።"
አነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ሲሉ ተናገሩ: በአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይህ የአላህ ቃል የወረደ ጊዜ: {(1) እኛ ላንተ ግልፅ የሆነን መክፈት ከፈትንልህ። (2) አላህ ከኀጢአትህ ያለፈውንና የሚመጣውን ላንተ ሊምር ጸጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላ ቀጥተኛውንም መንገድ ሊመራህ (ከፈተልህ)። (3) አላህ ብርቱን እርዳታ ሊረዳህም (ከፈተልህ)። (4) እርሱ ያ በምእመናን ልቦች ውስጥ ከእምነታቸው ጋር እምነትን ይጨምሩ ዘንድ እርጋታን ያወረደ ነው። ለአላህም የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አሉት። አላህም አዋቂ ጥበበኛ ነው። (5) ምእመናንንና ምእመናትን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈስባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ ሊያገባቸው ከነርሱም ሀጢአቶቻቸውን ሊያብስላቸው (በትግል አዘዛቸው)። ይህም ከአላህ ዘንድ የሆነ ታላቅ ማግኘት ነው።} [አልፈትሕ: 1-5] እነዚህ አንቀጾች የወረዱትም ሶሓቦች በሑደይቢያ ስምምነቱ መካሄድ ምክንያት ዑምራን ከማድረግ ክልከላ ተጥሎባቸው ሀድያቸውን (ቁርባናቸውን) በሑደይቢያ አርደው ስምምነቱ የሙስሊሞችን ጥቅም ያስጠበቀ አይደለም በሚል ሀዘንና ትካዜ ወርሯቸው ከዛ በሚመለሱበት ወቅት ነበር። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: እኔ ዘንድ ከዱንያ ባጠቃላይ ተወዳጅ የሆነች አንቀፅ በኔ ላይ ወረደች። ቀጥለውም አነበቧት።
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የሱረቱል ከህፍ መጀመሪያ አስር አንቀጾችን በቀልቡ የሸመደደ ሰው በመጨረሻ ዘመን መጥቶ ለራሱ ጌትነትን ከሚሞግተው ከመሲሕ ደጃል ፈተና ይጠበቃል ብለው ተናገሩ። የደጃል ፈተና አደም ከተፈጠረ ጀምሮ ትንሳኤ እስኪቆም ድረስ ምድር ከምታስተናግደው ፈተና ሁሉ ከባዱ ፈተና ነው። ተከታዮቹን ሊፈትንበት ዘንድ ከተለምዶ የወጡ አንዳንድ ተአምራት አላህ አስመችቶለታል። እነዚህን አንቀጾች መቅራት ከርሱ የሚጠብቀው ምክንያትም የሱረቱል ከህፍ መጀመሪያ አስር አንቀጾች ውስጥ ደጃል ሰዎችን ከሚፈትናቸው ፈተናዎች የበለጠ ትላልቅ ተአምራትና አስደናቂዎች ስለሚገኙ ነው። እነዚህን አንቀጾች ያስተነተነ በደጃል አይፈተንም። በሌላ ዘገባም: "ከምዕራፉ መጨረሻ አስር አንቀጾችን የሸመደደ ማለትም {እነዚያ የካዱት ባሮቼን ከእኔ ሌላ አማልክት አድርገው መያዛቸውን (የማያስቆጣኝ አድርገው) አሰቡን .....} ከሚለው ጀምሮ ነው።
ዑቅባ ቢን ዓሚር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለርሱ እንዲህ እንዳሉት ተናገረ: (ጥበቃን በመፈለግ በኩል) እንደነርሱ አምሳያ በጭራሽ ያልታየን አንቀጾች ዛሬ ምሽት አላህ በኔ ላይ አወረደ። እነርሱም ሙዐወዘተይን ናቸው። የ{ፈለቅ} ምዕራፍና የ{አንናስ} ምዕራፍ ናቸው።
አነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) የእናቱ ባል በነበረው በአቡ ጦልሓ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - ቤት ውስጥ ለሚመጡ ሰዎች መጠጥ የሚቀዳው እርሱ እንደነበር ተናገረ። የዛን ግዜ አስካሪ መጠጥ የሚያዘጋጁትም "ቡስር" (ቢጫው ያልበሰለ) ተምር እና ከበሰለው ተምር ቀላቅለው ነበር። ድንገት በአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ትእዛዝ "አዋጅ! በርግጥም አስካሪ መጠጥ ክልክል ተደርጓል።" ተብሎ አዋጅ ተነገረ። አቡ ጦልሓም ለኔ እንዲህ አለኝ "ውጣና ድፋው አፍስሰው!" እኔም ወጥቼ ደፋሁት አፈሰስኩት። አስካሪ መጠጡም በመዲና መንገድ መፍሰሱን ቀጠለ። አንዳንድ ሰዎችም እንዲህ አሉ: "አንዳንድ ሶሐቦች አስካሪ መጠጥ ክልክል ከመደረጉ በፊት ሆዳቸው ውስጥ እያለ ተገድለዋል!" አላህም እነርሱን በማስመልከት ይህንን አወረደ: {በእነዚያ ባመኑትና በጎ ስራዎችን በሰሩት ላይ (ከመከልከሉ በፊት) በተመገቡት ነገር ኀጢአት የለባቸውም።… } [አልማኢዳህ: 93] ማለትም: በነዚያ ባመኑት ላይ አስካሪ መጠጥ ክልክል ከመደረጉ በፊት በበሉትና በጠጡት ምክንያት ወንጀል የለባቸውም ማለት ነው።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶሐቦችን ልቦች በርሷ ምክንያት የራዱበትና ዓይኖች ያነቡበትን ጥግ የደረሰ ምክር መከሩ። ሰሐቦችም የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ምክራቸው ጥግ የደረሰ መሆኑን ስላዩ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምክሮት የተሰናባች ምክር ትመስላለች።" በማለት ከርሳቸው ህልፈት በኋላ አጥብቀው የሚይዙትን አደራ ጠየቁ። እርሳቸውም "አላህን በመፍራት አደራ እላቹኃለሁ።" አሉ። ይህም ግዴታዎችን በመፈፀምና ክልክሎችን በመተው ነው። "ባሪያ በናንተ ላይ ቢሾም ወይም መሪ ሆኖ ቢመጣባችሁ እንኳ ለመሪዎች መስማትና መታዘዝን አደራ እላችኃለሁ።" ማለትም በናንተ ላይ ደረጃው የወረደ (አርጋችሁ የምታስቡት) ፍጡር መሪ ቢሆን እንኳ ፈተና ይቀጣጠላል ተብሎ ስለሚሰጋ በዚህ ላይ እምቢተኛ አትሁኑ ታዘዙት ማለት ነው። "እነሆ ከናንተ መካከል የሚኖር ሰው ብዙ ልዩነትን ያያል።" ቀጥለውም ከዚህ ልዩነት መውጫውን ገለፁላቸው። እሱም የርሳቸውን ሱና(ፈለግ) እና ከርሳቸው በኋላ የተመሩ የሆኑት ቅን ምትኮቻቸውን ሱና አጥብቆ በመያዝ ነው። እነሱም: አቡ በከር አስሲዲቅ፣ ዑመር ቢን አልኸጧብ፣ ዑሥማን ቢን ዐፋንና ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ የሁሉንም መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ናቸው። አጥብቃችሁ የምትይዙትም በማኘኪያ ጥርስ ነክሶ እንደመያዝ ነው። በዚህም ለማለት የፈለጉት ሱናን በመያዝና በማጥበቅ ላይ መጠንከርን ለመጠቆም ነው። በሃይማኖት ውስጥ ከተፈበረኩ አዳዲስ መጤ ጉዳዮችም አስጠነቀቋቸው። ሁሉም አዲስ መጤ ነገር ጥመት ነውና።
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከርሳቸው የተማርነውን ቁርአናዊም ይሁን ሐዲሣዊ እውቀት አንድ አንቀፅ ያህል ትንሽ እንኳ ቢሆን እንድናስተላልፈው አዘዙን፤ ይህም ግን የምንጣራበትንና የምናደርሰውን መልእክት ተረድተነው መሆኑ ቅድመ መስፈርቱ ነው። ከዚያም ሽሪዓችን ጋር እስካልተጋጨ ድረስ ከበኒ ኢስራኢሎች የተከሰተባቸውን ክስተትና መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ ማውራታችንም ችግር እንደሌለው ገለፁ። ከዚያም በሳቸው ላይ ከመቅጠፍ አስጠነቀቁ፤ ሆን ብሎ በሳቸው ላይ የዋሸም ጀሀነም ውስጥ ማረፊያውን እንዲይዝ አሳሰቡ።
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከሰዎች መካከል የተወሰኑ ሰዎች አንድ ፍራሹ ላይ የተደገፈ ሰው፥ ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሐዲሥ ሲደርሰው "በጉዳዮቻችን ላይ በእኛና በናንተ መካከል የሚዳኘን የተከበረው ቁርኣን ነው፤ እሱ በቂያችን ነው፤ በቁርኣን ውስጥ ያገኘነውን ሐላሎች (ፍቁድ) እንሰራበታለን፤ ቁርኣን ውስጥ ያገኘነውን ሐራሞች (እርሞች) እንርቀዋለን። " የሚልበት ዘመን እንደቀረበ ተናገሩ። ቀጥለው ሁሉም በሱናቸው (ሀዲሳቸው) እርም ያደረጉት ወይም የከለከሉት ነገር ደረጃው ልክ አላህ በቁርኣኑ እንደከለከለው አምሳያ እንደሆነ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አብራሩ። ምክንያቱም እሳቸው የጌታቸውን መልዕክት አድራሽ ናቸውና።