





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ከአቡል ዐባስ ዐብደላህ ቢን ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «አንድ ቀን ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ኋላ ነበርኩ። እንዲህም አሉኝ: "አንተ ልጅ ሆይ! እኔ ቃላቶችን አስተምርሃለሁ! የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ (አላህ) ይጠብቅሀል፤ የአላህን (ትእዛዛት) ጠብቅ ፊት ለፊትህ ታገኘዋለህ፤ የጠየቅክ ጊዜ አላህን ጠይቅ! ፤ እገዛን የፈለግክ ጊዜም በአላህ ታገዝ! እወቅ! ህዝብ ባጠቃላይ በአንዳች ነገር ሊጠቅሙህ ቢሰባሰቡ እንኳ አላህ ለአንተ በፃፈልህ ነገር ካልሆነ በስተቀር አይጠቅሙህም። በአንዳች ነገር ሊጎዱህ ቢሰባሰቡም አላህ ለአንተ የፃፈብህ ካልሆነ በስተቀር አይጎዱህም። ብእሮቹም ተነስተዋል ፅሁፉም ደርቋል።" ከቲርሚዚይ ውጪ በሌሎች ዘገባም "የአላህን (ትእዛዝ) ጠብቅ ፊትለፊትህ ታገኘዋለህ። በድሎት ወቅት ከአላህ ጋር ተዋወቅ በችግርህ ወቅት ይደርስልሃል። እወቅ! የሳተህ ነገር ሊያገኝህ አልነበረም። ያገኘህም ነገር ሊስትህ አልነበረም። እወቅ! ድል ከትእግስት ጋር ነው፤ ስኬት ከችግር ጋር ነው፤ ከችግር ጋርም ድሎት አለ።"
رواه الترمذي وغيرهኢብኑ ዓባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ህፃን እንደነበሩና ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሚጋልቡበት ተፈናጥጦ ሳለ ለሱ ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ እንዳሏቸው ይነግሩናል: እኔ አላህ በሷ የሚጠቅምህን ነገሮችንና ጉዳዮችን አስተምርሀለሁ። አላህ ትእዛዙንና ወደርሱ መቃረቢያን እየፈፀምክ በሚያገኝህ ሁኔታና ወንጀልና ሀጢዐቶች ውስጥም በማያገኝህ ሁኔታ የአላህን ትእዛዛት በመጠበቅና ክልከላውንም በመራቅ አላህን ጠብቅ! ይህንን ከፈፀምክ ምንዳህ በዓለማዊም በአኺራዊም ጣጣዎችህ የአላህ ጥበቃ የማይለይህና ወደየትም ብትዞርም የቸገረህን በመርዳት አላህ የሚጠብቅህ ትሆናለህ። አንዳች ነገር መጠየቅ የፈለግክ ጊዜም ከአላህ በስተቀር ማንንም አትጠይቅ! ለጠያቂዎች ልመና ምላሽ የሚሰጠው እሱ ብቻ ነውና። እገዛን የፈለግክ ጊዜም ከአላህ በስተቀር በማንም አትታገዝ! የምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አንተን ለመጥቀም ቢሰባሰቡ እንኳ አላህ ላንተ ከፃፈልህ በስተቀር አንድም ጥቅም እንደማታገኝና የምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አንተን በመጉዳት ላይ ቢሰባሰቡም አላህ ባንተ ላይ ከወሰነብህ በስተቀር ባንተ ላይ አንድም ጉዳት እንደማያደርሱብህ አንተ ዘንድ እርግጠኝነት ይኑር! ይህንን ጉዳይ የላቀውና የተከበረው አላህ ጥበቡና እውቀቱ ባስፈረደው መልኩ ፅፏታልም ወስኗታልም። አላህ የፃፈው ነገርም አይለወጥም። የአላህን ትእዛዛት በመጠበቅና ክልከላውን በመራቅ አላህን የጠበቀ ሰው አላህ ባሪያው ያለበትን ሁኔታ ያውቃልና እርሱን በመርዳትና በማገዝ ከፊትለፊቱ ይሆናል። ሰው በድሎት ወቅት አላህን ከታዘዘ አላህም በጭንቁ ወቅት ስኬትና መውጫ መንገድን ያበጅለታል። ሁሉም ሰው አላህ በወሰነለት መልካምም ይሁን መጥፎ ነገር መውደድ አለበት። ከችግሮችና ፈተናዎች ጋርም አንድ ባሪያ ትእግስትን መያዝ አለበት። ትእግስት የስኬት ቁልፍ ነው። ችግር በበረታ ወቅት ከአላህ የሆነ ስኬት ይመጣል። አላህ ችግርን ሲያመጣ ድሎትንም ያስከትልበታል።
ከአቡ ዓምር አቡ ዓምራ ነውም ተብሏል: ከሱፍያን ቢን ዐብደላህ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በኢስላም ውስጥ ከርሶ ውጪ ስለርሱ አንድንም ሰው የማልጠይቀው የሆነን አንድን ንግግር ንገሩኝ አልኳቸው። እርሳቸውም 'በአላህ አምኛለሁ በል ከዚያም ቀጥ በል።' አሉኝ"
ሙስሊም ዘግበውታል።ሶሐቢዩ ሱፍያን ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ‐ ስለርሱ አንድንም ሳይጠይቅ እርሱን አጥብቆ የሚይዘው የሆነን የኢስላምን ሀሳቦች የጠቀለለ የሆነን ንግግር እንዲያስተምሩት ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጠየቀ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ "አላህ ብቻውን ጌታዬ፣ አምላኬ፣ ፈጣሪዬ፣ አጋር የሌለው በእውነት የሚመለከው ብቸኛ መሆኑን አረጋግጫለሁ። በል!" አሉት። ከዚያም ለአላህ ትእዛዝ የአላህን ግዴታዎች በመፈፀምና የአላህን ክልከላዎች በመተው ታዛዥ ይሁን፤ በርሱ ላይም ይዘውትር።
ከአቡ ዓብደላህ ጃቢር ቢን ዐብደላህ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው: «አንድ ሰውዬ የአላህን መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፡- “ እስኪ ንገሩኝ! ግዴታ ሰላቶችን ከሰገድኩ፣ ረመዷንንም ከፆምኩ፣ የተፈቀደውን ሐላል አድርጌ፣ የተከለከለውንም ሐራም አድርጌ ከቆጠርኩና (ከተቀበልኩ) በዛም ላይ ምንም ካልጨመርኩ ጀነት እገባለሁን?” ነቢዩም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - “አዎን!” አሉት።»
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አምስቱን ግዴታ ሰላቶች የሰገደና አንድም ተጨማሪ ሰላት ጨምሮ ያልሰገደ ፣ ረመዳንን የፆመና ከዚህም ሱና ፆሞችን ያልጨመረ፣ (ሐላል) ፍቁድ ነገሮችን በፍቁድነታቸው አምኖ የተገበረና ሐራም ነገሮችን በክልክልነታቸው አምኖ የራቀ ጀነት እንደሚገባ ይገልጻሉ።
ከሙዓዝ ቢን ጀበል - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ጀነት የሚያስገባኝንና ከእሳት የሚያርቀኝን ስራ ይንገሩኝ። አልኳቸው። እርሳቸውም: "በርግጥም ስለ ትልቅ ጉዳይ ነው የጠየቅከኝ፤ ጉዳዩ አላህ በርሱ ላይ ላቀለለለት ሰው ቀላል ነው። አላህን ልትገዛና በርሱ ላይ ምንንም ላታጋራ፤ ሶላትን ቀጥ ልታደርግ (በአግባቡ ልትሰግድ)፤ ዘካን ልትሰጥ፤ ረመዳንን ልትጾም፤ የአላህንም ቤት ሐጅ ልታደርግ ነው።" አሉና ቀጥለውም እንዲህ አሉ: "የመልካም ነገሮችን በር አልጠቁምህምን? ጾም ጋሻ ነው፤ ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋው ሁሉ ምፅዋትም ወንጀልን ታጠፋለች፤ የሰውዬው በሌሊቱ አጋማሽ የሚሰግደው ሶላት" አሉና ቀጥለው {ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ስፍራዎች ይራራቃሉ} ከሚለው {ይሰሩትም በነበሩት} እስከሚለው ድረስ [ሱረቱ ሰጅዳ: 16‐17] አነበቡ። ቀጥለውም "የነገሩ ሁሉ ራስ፣ ምሰሶውንና ሻኛውን ልንገርህን?" አሉ። እኔም "እንዴታ የአላህ መልክተኛ ሆይ!" አልኳቸው። እርሳቸውም "የነገሮች ሁሉ ራስ (ዋና) እስልምና ነው፤ ምሰሶው ሶላት ነው፤ ሻኛው ጂሃድ ነው።" አሉ። ቀጥለውም "ይህን ሁሉ የሚቆጣጠረውን ነገር ልንገርህን?" አሉ። እኔም "እንዴታ የአላህ ነቢይ ሆይ!" አልኳቸው። ምላሳቸውን ያዙና "በራስህ ላይ ይህቺን ቆጥባት!" አሉ። እኔም "የአላህ ነቢይ ሆይ! እኛ በምንናገረው እንያዛለንን?" አልኳቸው። እርሳቸውም "እናትህ ትጣህና ሙዓዝ ሆይ! ምላሳቸው ያጨደችው ካልሆነ በቀር ሰዎችን በፊታቸው ወይም በአፍጢማቸው እሳት ውስጥ የሚደፋቸው (ሌላ ነገር) አለ እንዴ?" አሉኝ።»
ቲርሚዚ ዘግበውታል።ሙዓዝ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ: ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ጉዞ ላይ ነበርኩ። አንድ እለት እየተጓዝን ሳለ ወደርሳቸው ቀረብ አልኩኝና እንዲህ አልኳቸው: የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጀነት የሚያስገባኝና ከእሳትም የሚያርቀኝን ስራ ይንገሩኝ። እርሳቸውም እንዲህ አሉ: በነፍስ ላይ መስራቱ ከባድ ስለሆነ ስራ ነው የጠየቅከኝ። አላህ በርሱ ላይ ላቀለለለት ግን ገርና ቀላል ነው። የእስልምናን ግዴታዎች ፈፅም: የመጀመሪያው: አላህን በብቸኝነት መገዛትና በርሱም አንዳችን አታጋራ፤ ሁለተኛው: በቀንና ምሽት አምስቱን ግዴታ ሶላቶች: ፈጅር፣ ዙህር፣ ዐስር፣ መግሪብና ዒሻን መስፈርታቸውን፣ ማዕዘናቸውንና ግዴታዎቻቸውን አሟልተህ ቀጥ አድርገህ መስገድ ነው፤ ሶስተኛው: ግዴታ የሆነብህን ዘካ ማውጣት ነው: ይህም ገንዘብ በሸሪዓ የተገደበን መጠን በደረሰ ጊዜ ለሚገባው አካል የሚሰጥ በሁሉም ገንዘብ ላይ ግዴታ የሆነ ገንዘባዊ አምልኮ ነው፤ አራተኛው: ረመዳንን ትጾማለህ: እርሱም አምልኮን በመነየት ጎህ ከወጣችበት ወቅት ጀምሮ ፀሐይ እስክትገባ ድረስ ከመብላት፣ ከመጠጣትና ከሌሎችም የሚያስፈጥሩ ነገሮችም መቆጠብ ነው። አምስተኛው: የሐጅ አምልኮን ለመተግበር አላህን ለማምለክ መካን በማሰብ የአላህን ቤት ሐጅ ማድረግ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: ወደ መልካም በሮች የሚያደርስ መንገድ አላሳውቅህምን? ይህም እነዚህን ግዴታዎችና ሱና ተግባራትን በመከተል ነው: የመጀመሪያው: ሱና ጾም መጾም ነው። ይህም ስሜትን በመስበርና ሀይልን በማድከም ወንጀል ላይ ከመውደቅ የሚከላከል ነው። ሁለተኛው: ሰደቃ (ግዴታ ያልሆነ ምፅዋት) መስጠት ነው። ይህም ወንጀል ከተሰራ በኋላ ወንጀልን ታጠፋለች፣ ታስወግዳታለች፣ ፋናዋንም ታብሳታለች። ሶስተኛው: በሌሊቱ የመጨረሻ ሲሶ የተሀጁድ ሶላት መስገድ ነው። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) {ጎኖቻቸው ከመጋደሚያ ስፍራዎች ይራራቃሉ} በሶላት፣ በዚክር፣ በመቅራትና በዱዓ {ጌታቸውን ይጠሩታል።} {ለመፍራትና ለመከጀል ከሰጠናቸውም (ጸጋ) ይለግሳሉ። ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም።} ማለትም የትንሳኤ ቀን በጀነት ውስጥ በሚያገኙት ፀጋ አይኖቻቸው በርሱ የምትረጋበትን ነፍሳቸው አታውቅም። {ይሰሩትም በነበሩት ለመመንዳት።} ቀጥለው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: የሃይማኖቱ መሰረት የሆነውን አልነግርህምን? መሰረቱ በርሱ ላይ የሚደገፍበት ምሰሶውንስ አልነግርህምን? ሻኛውንስ አልነግርህምን? ሙዓዝም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - "እንዴታ የአላህ መልክተኛ ሆይ!" አለ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና: የነገሮች ራስ (ዋና) እስልምና ነው። እርሱም ሁለቱ የምስክር ቃላቶች ናቸው። የሃይማኖቱ መሰረት ከሰውዬው ጋር የሚቆይለት በሁለቱ ቃላት ነው። ምሰሶው: ሶላት ነው። ቤት ያለምሰሶ እንደማይኖር ሁሉ ያለ ሶላትም እስልምና የለም። የሰገደ ሰው ሃይማኖቱ ይጠነክራልም ከፍ ይላልም። ሻኛውና ከፍታው ደሞ በጂሃድና የአላህን ቃል ከፍ ለማድረግ የእስልምና ጠላቶችን ለመዋጋት አቅምን በመለገስ ነው። ቀጥለው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: ቀደም ብዬ የነገርኩህን ነገር የሚያስረውና የሚጠብቀውን ልንገርህን? ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምላሳቸውን ያዙና "ይህንን ቆጥብ። የማይመለከትህን አትናገር።" አሉት። ሙዓዝም: "ጌታችን በምንናገረው ሁሉ ይቀጣናል? ይተሳሰበናል? ይይዘናልን?" አላቸው። ቀጥለውም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "እናትህ ትጣህ" አሉት። በዚህም እርሱን መርገም ፈልገው ሳይሆን ነገር ግን ዐረቦች ሊታወቅና ሊገነዘቡት የሚገባን ነገር ለማስገንዘብ የሚናገሩት ንግግር ነው። ቀጥለው "እንደ ክህደት፣ ዘለፋ፣ ስድብ፣ ሀሜት፣ ነገር ማሳበቅ፣ ቅጥፈትና በመሳሰሉት ምላሳቸው ባጨደችው ክፋት ካልሆነ በቀር ሰዎችን እሳት ውስጥ በፊታቸው የሚጥላቸውና የሚደፋቸው (ሌላ ነገር) አለ እንዴ?" አሉት።
ከኢብኑ ዓባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከተከበረውና ከላቀው ጌታቸው በሚያስተላልፉት (ሐዲሠል ቁድሲይ) እንዲህ አሉ፦ "አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን ፅፏል። ይህንንም አብራርቶታል። አንድን መልካም ስራ (ለመስራት) አስቦ ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳን ይጽፍለታል። እሱ (ለመስራት) አስቦ ከሰራት ደግሞ አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ (ከዛም በላይ) እስከ ብዙ እጥፍ ድርብ የሚደርስ ምንዳዎችን ይጽፍለታል። አንድን ኃጢዐት (ለመስራት) አስቦ ያልሰራት አላህ እሱ ዘንድ ለሱ ሙሉ ምንዳ ይጽፍለታል። እሱ (ለመስራት) ካሰባትና ከሰራት አላህ ለሱ አንዲት ኃጢዐት ይጽፍበታል።"
رواه البخاري ومسلم في صحيحيهما بهذه الحروفመልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ መልካሞችና ኃጢዐቶችን እንደወሰነ ከዚያም ለሚፅፉት ሁለት መላእክቶች እንዴት እንደሚፅፉት እንዳብራራ ገለፁ። መልካምን ለመስራት የፈለገ፣ ያሰበና የቆረጠ ሰው ባይሰራትም እንኳ ለሱ አንድ ምንዳ ትፃፍለታለች። ከሰራት ደግሞ በስራዋ አምሳያ ከአስር እስከ ሰባት መቶ እጥፍ ከዚያም አልፎ እስከ ብዙ እጥፍ ድርብ ትባዛለች። ይህ የምንዳ ጭማሪው ቀልቡ ውስጥ ባለው ኢኽላስ፣ በጥቅሙ ወደ ሌሎች ተሻጋሪነትና በመሳሰሉት ልክ ተንተርሶ ነው ። ኃጢዐትን ለመስራት የፈለገ፣ ያሰበና የቆረጠ ከዚያም ለአላህ ብሎ ሳይሰራት የተዋት ሰው ለሱ አንድ ምንዳ ይጻፍለታል። ወደዛች ኃጢዐት የሚያዳርሱ መንስኤዎችን ካለመፈፀም ጋር በሌላ ነገር በመጠመዱ ሳቢያ ከተዋት ምንም ነገር አይፃፍለትም። ኃጢዐቱን መስራት ስለተሳነው ከተወ ደግሞ በሱ ላይ ያለመው ትፃፍበታለች። ከሰራት ደግሞ አንዲት ሀጢዐት ትፃፍበታለች።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ እንዲህ ብሏል: ‹የኔን ወዳጅ (ወሊይ) ጠላት አድርጎ የያዘን ሰው በርግጥም ጦርነት እንዳወጀኩበት አሳውቄዋለሁ። ባሪያዬ ግዴታ ካደረግኩበት በበለጠ ወደ እኔ ተወዳጅ በሆነ በአንዳችም ነገር አይቃረብም። ባሪያዬ ወደ እኔ በትርፍ ስራዎች ከመቃረብ አይወገድም የምወደው ቢሆን እንጂ፤ የወደድኩትም ጊዜ የሚሰማበት መስሚያው እሆነዋለሁ፣ የሚያይበት መመልከቻ እሆነዋለሁ፣ የሚጨብጥበት እጅ እሆነዋለሁ፣ የሚራመድበት እግር እሆነዋለሁ፣ ቢጠይቀኝ እሰጠዋለሁ፣ ከኔ ጥበቃ ከፈለገም እጠብቀዋለሁ።›"»
ቡኻሪ ዘግበውታል።ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በሐዲሠል ቁድስ አላህ እንዲህ እንዳለ ተናገሩ: ከወዳጆቼ መካከል አንድንም የኔን ወዳጅ ያወከና ያስቆጣ ከኔ ጋር ጠላት እንደሆነ አውጄያለሁም አሳውቄዋለሁም። ወሊይ ማለት: አላህን ፈሪ አማኝ ነው። አንድ ባሪያ ባለው ኢማንና ፈሪሃ አላህነት ልክ የአላህ ወሊይነት ይኖረዋል። አንድ ሙስሊም አላህ ግዴታ ያደረገበትን ትእዛዛትን መፈፀምና ክልክሎችን መተውን ያህል ወደ አላህ የሚያቃርበው ጌታው ዘንድ ተወዳጅ የሆነ ምንም ነገር የለም። አንድ ሙስሊም ወደ ጌታው ከግዴታዎች በተጓዳኝ በትርፍ ስራዎች ከመቃረብ አይወገድም የአላህን ውዴታ የሚያገኝ ቢሆን እንጂ፤ አላህ የወደደው ጊዜም አላህ እነዚህን አራት አካላቶቹን ያቀናለታል: በመስሚያው ያግዘዋል። አላህን ከሚያስደስት ነገር ውጪ ሌላ ምንም አይሰማም። በመመልከቻው ያግዘዋል። አሏህ እንዲታይ የሚወደውንና የሚያስደስተውን ነገር እንጂ ሌላ አይመለከትም። እጁንም ያግዘዋል። በእጁ አላህን ከሚያስደስት ነገር በቀር አይሰራም። አላህን ወደሚያስደስት ነገር ካልሆነ በቀር እንዳይራመድ በማድረግም እግሩንም ያግዘዋል። መልካም ነገር ወዳለበት ካልሆነ በቀርም አይንቀሳቀስም። ከዚህም ጋር አላህን አንዳች ነገር ከጠየቀው አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፤ ተማፅኖውንም የሚሰማው ይሆናል። የአላህ ጥበቃ ካስፈለገውና የአሏህን ከለላ ፈልጎ ከተጠጋ ጥራት የተገባው አላህም ከሚፈራው ነገር ይጠብቀዋል።
ከአቡ ሙሐመድ ዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዓስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "አንዳችሁ ዝንባሌው ይዤ የመጣሁትን እስከሚከተል ድረስ አላመነም።"
رويناه في كتاب الحجة بإسناد صحيحነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አንድ ሰው ውዴታው መልክተኛው -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይዘውት የመጡትን ትእዛዛትን፣ ክልከላዎችንና ሌሎችንም እስከሚከተል ድረስ፤ እርሳቸው ያዘዙትን እስኪወድና የከለከሉትንም እስኪጠላ ድረስ ኢማኑ የተሟላ አማኝ አይሆንም ብለው አብራሩ።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "አራት (ባሕርያት) በእርሱ ላይ ያለበት ሰው ሙናፊቅ ሆኗል፤ ከአራቱ ባህሪዎች ውስጥ አንዱ ያለበት ደግሞ እስኪተዋት ድረስ አንድ የሙናፊቅነት ባህሪ ይኖረዋል፦ ሲናገር ይዋሻል፤ ቀጠሮ የያዘ ጊዜ ያፈርሳል፤ ሲከራከር ወሰን ያልፋል፤ ቃልኪዳን ከገባ በኋላ ቃልኪዳኑን ይክዳል።"
رواه البخاري ومسلمነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአራት ነገሮች አስጠነቀቁ። እነዚህ አራት ነገሮች አንድ ሙስሊም ላይ የተሰባሰቡ ጊዜ በነዚህ ነገሮች ሰበብ ከመናፍቃን ጋር እጅግ በጣም ይመሳሰላል። ይህ ግን እነዚህ አራት ነገሮች እርሱ ላይ በብዛት የሚስተዋሉ ከሆነ ነው እንጂ አልፎ አልፎ የሚስተዋልበት ከሆነ ግን እዚህ ውስጥ አይካተትም። እነሱም:- የመጀመሪያው: ሲያወራ ሆን ብሎ ይዋሻል፣ በንግግሩም እውነቱን አይናገርም። ሁለተኛ: አንድ ቃል ኪዳን ከገባ ቃልኪዳኑን አይሞላም። ቃልኪዳን ለገባለት ሰውም ቃሉን ያፈርሳል። ሶስተኛ: ቀጠሮን የቀጠረ ጊዜ የገባውን ቃል አይሞላም። ቀጠሮውን ያፈርሳል። አራተኛ: ከአንድ ሰው ጋር የተጨቃጨቀና የተሟገተ ጊዜ ሙግቱ ሀይለኛ ይሆናል። ከእውነትም ይዘነበላል። እውነትን ላለመቀበልም በተንኮል ጥመትና ውሸትን ይናገራል። ንፍቅና ማለት ውስጡ ካለው ተቃራኒ የሆነን ነገር ግልፅ ማውጣት ነው። የዚህ ሀሳብም በተመሳሳይ እነዚህን ነገሮች በሚተገብር ላይ ይገኛሉ። ንፍቅናውም ባዋራው፣ በቀጠረው፣ ባመነው፣ በተከራከረውና ቃልኪዳን በገባለት ሰው ሐቅ ላይ ነው እንጂ እስልምናን ግልፅ እያደረገ ክህደትን በመደበቅ በእስልምና ላይ መናፍቅ ሆኗል ማለት አይደለም። ከነዚህ ነገሮች መካከል አንድ ጉዳይ ያለበትም እስኪተወው ድረስ በርሱ ላይ የንፍቅና ባህሪ አለበት።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ያ የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ከዚህ ኡመት ውስጥ አንድም አይሁድ ይሁን ክርስቲያን ስለኔ ሰምቶ ከዚያም በዛ በተላኩበት ሳያምን የሚሞት የለም። ከእሳት ጓዶች መካከል ቢሆን እንጂ።"
ሙስሊም ዘግበውታል።'ከዚህ ሕዝብ (ኡመት) ሆኖ የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጥሪ የደረሰውና ስለርሳቸው የሚሰማ ሆኖ ከዚያም በርሳቸው ሳያምን የሚሞት አንድም አይሁዳዊም ይሁን ክርስቲያን ወይም ሌላ እምነት ተከታይ የለም ዘላለሙን የእሳት ሰው ቢሆን እንጂ።' ብለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማሉ።