





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ከአቡ በክር አስሲዲቅ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «እኛ ዋሻ ውስጥ ሆነን ሳለን የአጋርያን እግር ከጭንቅላታችን በላይ ሆኖ ተመለከትኩት። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ: ከአጋርያኖች መካከል አንዱ ወደ እግሮቹ ቢመለከት'ኮ ከእግሮቹ ስር ይመለከተን ነበር።" አልኳቸው። እርሳቸውም: "አቡ በክር ሆይ! አላህ ሶስተኛቸው በሆኑ ሁለት ሰዎች ጉዳይ ምንድን ነው የምታስበው?" አሉ።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።የአማኞች መሪ አቡ በክር አስሲዲቅ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በስደት ወቅት ስለነበረው ሁኔታ ሲተርኩ እንዲህ አሉ: እኛ የሠውር ዋሻ ውስጥ ሆነን ሳለን ከጭንቅላታችን በላይ የአጋርያን እግር ሆኖ ተመለከትኩ። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከአጋርያኖች መካከል አንዱ ወደ እግሮቹ ቢመለከት'ኮ ከእግሮቹ ስር ይመከተናል።" አልኳቸው። እርሳቸውም: "አቡ በክር ሆይ! አላህ በእርዳታው፣ በእገዛውና በጥበቃው ሶስተኛቸው በሆኑ ሁለት ሰዎች ጉዳይ ምንድን ነው የምታስበው?" አሉት።
ከአማኞች እናት ዓኢሻ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- መጀመሪያ ወሕይ ወደርሳቸው መውረድ የጀመረው በእንቅልፋቸው የሚያዩት መልካም ህልም ነበር። ንጋት ብርሃን (እንደተፍለቅላቂ ጎህ) በገሃዱ አለም የሚከሰት ቢሆን እንጂ አንድም ህልም አያዩም ነበር። ከዚያም ከሰዎች መገለል እርሳቸው ዘንድ ተወዳጅ ሆነ። በሒራ ዋሻም ከሰዎች ተገልለው ወደ ቤተሰባቸው ሳይመለሱ በርካታ ቀናቶችን አላህን እያመለኩ ያሳልፉ ነበር። ለዚህም ስንቅ ይዘው ነበር የሚወጡት። ከዛም ወደ ኸዲጃ ተመልሰው ለተመሳሳይ ድርጊት ስንቅ ይዘው ይወጡ ነበር። ይህንንም በሒራ ዋሻ ሳሉ እውነት ወደርሳቸው እስኪመጣ ድረስ ቀጠሉበት። መልአኩ ወደርሳቸው መጣና "አንብብ!" አላቸው። (ያኔ የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ይገልፁታል) እኔም "ማንበብ አልችልም!" አልኩት። እንዲህም አሉ "ጭንቅ እስኪለኝ ድረስ ይዞ ጨመቀኝና ለቀቀኝ።" አሁንም "አንብብ!" አለኝ። እኔም "ማንበብ አልችልም።" አልኩት። "አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ይዞኝ ጭንቅ እስኪለኝ ድረስ ጨመቀኝና ለቀቀኝ።" አሁንም "አንብብ!" አለኝ። እኔም "ማንበብ አልችልም።" አልኩት። "አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ይዞ ጭንቅ እስኪለኝ ድረስ ጨመቀኝና ለቀቀኝ።" መልአኩም እንዲህ አለኝ: {አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም) አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲሆን} [አልዐለቅ: 1 - 3] የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እነዚህን አንቀጾች ሸምድደው ልባቸው እየተንቀጠቀጠ ተመለሱ። ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ዘንድም በመግባት "አከናንቡኝ! አከናንቡኝ!" አሉ። ድንጋጤው እስኪወገድላቸው ድረስም አከናነቧቸው። ለኸዲጃም ጉዳዩን ነገሯቸው። "ለነፍሴ ፈርቻለሁ።" አሉ። ኸዲጃም እንዲህ አለቻቸው "(እንደዚህ ከማሰብ) ተከልከል! በአላህ እምላለሁ! ከቶም አላህ አይተውህም። አንተ ዝምድና ትቀጥላለህ፤ ለደካሞች ትረዳለህ፤ ለተቸገሩ ትሰጣለህ፤ እንግዳ ታከብራለህ፤ እውነተኛ ጉዳዮች ላይ ትተባበራለህ።" እርሳቸውንም ይዛ የአጎቷ ልጅ ወደሆነው ወረቃ ቢን ነውፈል ቢን አሰድ ቢን ዐብዲል ዑዛ ዘንድ ሄደች። በጃሂሊያ ዘመን ክርስቲያን የሆነ ሰው ነበር። መጽሐፍን በዕብራይስጠኛ ይፅፍ ነበር። አላህ እንዲፅፍ የሻለትን ያህልም ኢንጂልን በዕብራይስጠኛ ይፅፍ ነበር። አይኑ የታወረ እጅግ የጃጀ ሽማግሌ ነበር። ኸዲጃም ለርሱ "የአጎቴ ልጅ ሆይ! እስኪ የወንድምህ ልጅ የሚለውን ስማ።" አለችው። ወረቃም ለርሳቸው "የወንድሜ ልጅ ሆይ! ምንድን ነው የምታየው?" አላቸው። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የተመለከቱትን ነገሩት። ወረቃም ለርሳቸው "ይህ አላህ በሙሳ ላይ ያወረደው ናሙስ ነው። ህዝቦችህ ከሀገርህ በሚያስወጡህ ጊዜ ዋ ምኞቴ! ምነው ያኔ ጠንካራ ወጣት በሆንኩ! ዋ ምኞቴ በህይወት በኖርኩ!" አላቸው። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "እነርሱ ያስወጡኛልን?" አሉ። እርሱም "አዎን አንተ ይዘኸው የመጣኸውን አምሳያ ይዞ የመጣ አንድም ሰው የለም ጠላት ተደርጎ የተያዘ ቢሆን እንጂ፤ የመልክተኝነት ዘመንህ ላይ ከደረስኩ ጠንካራ እርዳታን እረዳሀለሁ።" አላቸው። ከዚያም ግን ወረቃ ብዙም ሳይቆይ አረፈ። ወሕዩም ተቋረጠ።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።የአማኞች እናት ዓኢሻ ረዺየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንዲህ በማለት ስለ ወሕይ አጀማመር ተናገረች: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- መጀመሪያ ወሕይ ወደርሳቸው መውረድ የጀመረው በእንቅልፋቸው መልካም ህልም በማየት ነበር። በእንቅልፋቸው አንድም ህልም አያዩም ነበር እንደ ንጋት ብርሃን በሚመስል መልኩ በግልፅ የሚከሰት ቢሆን እንጂ። ቀጥሎ እርሳቸው ዘንድ ከሰዎች መገለል ተወዳጅ ሆነ። በሒራ ዋሻም ከሰዎች ተገልለው ወደ ቤተሰባቸው ሳይመለሱ በርካታ ቀናቶችን አላህን ሲያመልኩ ያሳልፉ ነበር። ለዚህም ስንቅ ይዘው ነበር የሚወጡት። ቀጥለው ወደ አማኞች እናት ኸዲጃ ረዲየሏሁ ዓንሃ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- በመመለስ ለተመሳሳይ ድርጊት ስንቅ ይዘው ይወጡ ነበር። ይህንን ማድረጋቸውንም በሒራ ዋሻ ሳሉ እውነት ወደርሳቸው እስኪመጣ ድረስ ቀጠሉበት። መልአኩ ጂብሪልም ዐለይሂ ሰላም ወደርሳቸው በመምጣት "አንብብ" አላቸው። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ማንበብ አልችልም።" አሉ። እንዲህም አሉ: ጭንቅ ጥብብ እስኪለኝና እስኪሳነኝ ድረስ ጭምቅ አደረገኝ። ከዚያም ለቀቀኝና "አንብብ" አለኝ። እኔም "ማንበብ አልችልም።" አልኩት። አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ጭንቅ ጥብብ እስኪለኝና እስኪሳነኝ ድረስ ጭምቅ አደረገኝ። ከዚያም ለቀቀኝና "አንብብ" አለኝ። እኔም "ማንበብ አልችልም።" አልኩት። አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ጭንቅ ጥብብ እስኪለኝና እስኪሳነኝ ድረስ ጭምቅ አደረገኝና እንዲህ አለኝ: {አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም* ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረው (ጌታህ ስም)* አንብብ፤ ጌታህ በጣም ቸር ሲሆን} [አልዐለቅ: 1 - 3] ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አንቀጾቹን ሸምድደው ሞትን ፈርተው ልባቸው እየተንቀጠቀጠ ተመለሱ። የአማኞች እናት ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድ ረዲየሏሁ ዓንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ዘንድም በመግባት እንዲህ አሉ: "በልብስ ጠቅልሉኝ! በልብስ ጠቅልሉኝ!" ፍርሃት እስኪለቃቸው ድረስም በልብስ ጠቀለሏቸው። ለኸዲጃም ጉዳዩን ነገሯትና እንዲህ አሉ: "ሞትን በነፍሴ ላይ ፈርቻለሁ።" ኸዲጃም እንዲህ አለች: "ይህንን ከመናገር ተከልከል! በአላህ እምላለሁ! አላህ በፍፁም አይተውህም። አንተ ዝምድናን ትቀጥላለህ፤ ራሱን ያልቻለን ደካማ ታግዛለህ፤ ሰዎች ካንተ ውጪ ማንም ዘንድ በማያገኙት መልኩ በመስጠት ምንም የሌለውን ድሃ ትረዳለህ፤ እንግዳን ታከብራለህ፤ ትክክለኛ ጉዳዮች ላይ ትተባበራለህ።" ኸዲጃም እርሳቸውን ይዛ የአጎቷ ልጅ ወደሆነው ወረቃ ቢን ነውፈል ቢን አሰድ ቢን ዐብዲል ዑዛ ዘንድ ሄደች። በጃሂሊያ ዘመን የጃሂሊዮችን እምነት በመተው ክርስቲያን የሆነ ሰው ነበር። አላህ እንዲፅፍ የሻለትን ያህልም ኢንጂልን በዕብራይስጠኛ ይፅፍ ነበር። አይኑ የታወረ እጅግ የጃጀ ሽማግሌ ነበር። ኸዲጃም ለርሱ እንዲህ አለች: "የአጎቴ ልጅ ሆይ! እስኪ የወንድምህ ልጅ የሚለውን ስማ።" ወረቃም ለርሳቸው "የወንድሜ ልጅ ሆይ! ምንድን ነው የምታየው?" አላቸው። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የተመለከቱትን ነገሩት። ወረቃም ለርሳቸው "ይህ አላህ በሙሳ ላይ ያወረደው ጂብሪል ነው። ህዝቦችህ ከሀገርህ በሚያስወጡህ ጊዜ ዋ ምኞቴ! ጠንካራ ወጣት በሆንኩ! ዋ ምኞቴ በህይወትም በኖርኩ!" አላቸው። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "እነርሱ ያስወጡኛልን?" አሉ። እርሱም "አዎን አንተ ይዘኸው የመጣኸውን አምሳያ ይዞ የመጣ አንድም ሰው የለም ጠላት ተደርጎ የተያዘና ጉዳት የደረሰበት ቢሆን እንጂ፤ የመልክተኝነት ዘመንህ ላይ ከደረስኩ ጠንካራ እርዳታን እረዳሀለሁ።" አላቸው። ከዚያም ግን ወረቃ ብዙም ሳይቆይ አረፈ። ወሕዩም ለተወሰነ ጊዜ ዘገየ።
ከአቡ ሓዚም እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «አቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ዘንድ አምስት ዓመት ተቀምጫለሁ። ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብሎ ሲያወራም ሰምቸዋለሁ: "በኑ ኢስራኢሎችን ነቢያቶች ነበሩ ጉዳያቸውን የሚመሩት። አንድ ነቢይ በሞተ ቁጥር ሌላ ነቢይ ይተካ ነበር። ከኔ በኋላም ነቢይ የለም። ምትኮች (ኸሊፋዎች) ይኖራሉም ይበዛሉም።" ሶሐቦችም "ምን ያዙናል?" አሉ። እርሳቸውም "የመጀመሪያውን ቃል ኪዳን ሙሉ፤ ሐቃቸውንም ተወጡ። አላህም ለሰጣቸው ሀላፊነት ይጠይቃቸዋል።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዛሬ ላይ ህዝቦችን የሚመሩት መሪዎችና ሹማምንት እንደሆኑት ያኔ በኒ ኢስራኢሎችን የሚመሯቸውና ጉዳያቸውንም በሀላፊነት የሚያዙት ነቢያቶች እንደነበሩ ተናገሩ። ብክለት በመካከላቸው በተንሰራፋ ቁጥርም ጉዳዩን የሚያስተካክልና የለወጡትን ህግ የሚያስወግድ ሌላን ነቢይ አላህ ይልክ ነበር። በነርሱ ላይ ያደርግ እንደነበረው የሚያደርግ ከኔ በኋላ የሚመጣ ነቢይ የለም። ከኔ በኋላ ምትኮች (ኸሊፋዎች) ነው የሚኖሩት እነርሱም በርካታ ይሆናሉ። በመካከላቸውም ልዩነትና ተቃርኖ ይከሰታል። ሶሐቦችም - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ምን ያዙናል?" በማለት ጠየቁ። እርሳቸውም "ከአንዱ መሪ በኋላ ለሌላ መሪ ቃል ኪዳን ቢገባለት። የመጀመሪያው መሪ ቃልኪዳን ትክክለኛ ስለሆነ ታማኝ መሆን ያለባችሁ ለመጀመሪያው ነው። አንድ መሪ እያለ ለሁለተኛ መሪነት ቃል የተገባለት ግን ቃልኪዳኑ ተቀባይነት የሌለው ከንቱ ነው። እርሱም መሪነትን መፈለጉ ክልክል ነው። ለመሪዎች ሐቃቸውን ስጧቸው፣ ታዘዟቸው፤ ከወንጀል ውጪ በመታዘዝና በመስማትም ተኗኗሯቸው። በናንተ ላይ ለሚሰሩት ነገር አላህ ይጠይቃቸዋልም ይታሳሰባቸዋልም።"
ከአነስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የተወሰኑ የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶሐቦች የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሚስቶች ስለርሳቸው ድብቅ (ቤት ውስጥ የሚሰሩት) ዒባዳ ጠየቁ። (የርሳቸውን የቤት ውስጥ ስራ ከሰሙ በኋላ) አንዱ እንዲህ አለ "እኔ ሴት አላገባም!" አንዱ ደግሞ "እኔ ስጋ አልበላም!" አለ። ሌላኛው ደግሞ "እኔ ፍራሽ ላይ አልተኛም!" አለ። እርሳቸውም አላህን ካመሰገኑና ካወደሱ በኋላ እንዲህ አሉ "እንዲህ እንዲህ ያሉ ሰዎች ምን ሆነው ነው? እኔ ግን እሰግዳለሁም እተኛለሁም፤ እጾማለሁም አፈጥራለሁም፤ ሴትንም አገባለሁ! ከኔ ፈለግ ውጭ የሰራ ከኔ አይደለም።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።የተወሰኑ ሶሐቦች - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቤት ውስጥ በድብቅ ስለሚሰሩት ዒባዳ ለመጠየቅ ወደ ሚስቶቻቸው ቤት መጡ። የርሳቸው የቤት ውስጥ አምልኮ ሲነገራቸውም የራሳቸውን ስራ አሳንሰው ተመለከቱና እንዲህ አሉ: "እኛ ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንፃር የት ነን? ለርሳቸው ያሳለፉትንም ሆነ የሚመጣውን ወንጀል ተምረዋል። እኛስ ከርሳቸው ተቃራኒ ምህረት ማግኘታችንን እንኳ አላወቅንም። ስለዚህ ይህን የአላህ ምህረት ለማግኘት አምልኳችን ከገደብ ያለፈ መሆን አለበት።" ቀጥለውም አንዱ "እኔ ሴት አላገባም!" አለ። ሁለተኛው ደግሞ "እኔ ስጋ አልበላም!" አለ። ሌላኛው ደግሞ "እኔ ፍራሽ ላይ አልተኛም።" አለ። ይህ ንግግራቸውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘንድ ደረሰና ተቆጡ። ለሰዎችም ኹጥባ አደረጉ። አላህን አመስግነው ካወደሱ በኋላ እንዲህ አሉ: "እንዲህ እንዲህ ያሉ ሰዎች ምንድነው ጉዳያቸው? ወላሂ እኔ ከሁላቹም እጅግ አላህን ፈሪውና ተጠንቃቂው ነኝ። ነገር ግን እኔ ሌሊት ለመቆም እንድበራታ እተኛለሁ፤ ለጾም እንድበራታም አፈጥራለሁ፤ ሴትንም አገባለሁ። ከኔ መንገድ አፈንግጦ ከኔ መንገድ ውጪ የተሟላ መንገድ እንዳለ የተመለከተና ከኔ መንገድ ውጪ የያዘ ሰው ከኔ አይደለም።"
የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በሁለት ነገሮች መካከል ምርጫ ሲሰጣቸው ወንጀል እስካልሆነ ድረስ የሚመርጡት ገሩን ነው። ወንጀል ከሆነ ግን ከርሱ እጅግ የሚርቁ ነበሩ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የአላህ ክልከላ ስትደፈር ካልሆነ በቀር ለነፍሳቸው ተበቅለው አያውቁም። የአላህ ክልከላ ስትደፈር ግን ለአላህ ብለው ይበቀላሉ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ስለአንዳንድ የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስነምግባር ተናገረች። ከጠቀሰቻቸውም መካከል: እርሳቸው በሁለት ነገሮች መካከል ምርጫ ሲሰጣቸው የሚመርጡት ገሩን ነው። ግን ያ ገር ነገር ወንጀል እስካልሆነ ድረስ ነው። ገር ነገሩ ወንጀል ከሆነ ግን ከሰዎች ሁሉ እጅግ የሚርቁት እርሳቸው ናቸው። ጠንከር ያለውንም ይመርጣሉ። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለነፍሳቸው ብቻ ብለው አልተበቀሉም። ይልቁንም የአላህ ክልከላ እስካልተደፈረ ድረስ ስለነፍሳቸው ሐቅ ይቅር የሚሉና የሚያልፉ ነበሩ። ለአላህ ብለው ግን ይበቀሉ ነበር። እጅግ በጣም ለአላህ ብለው የሚቆጡ ነበሩ።