Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way






























Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ትናንሽ ተደርገው የሚታዩ ወንጀሎችን መስራት ላይ ከመዘናጋትና አብዝቶ ከመስራት አስጠነቀቁ። ትናንሽ ወንጀሎች ተሰባስበው ባለቤቱን ያጠፋሉና። ለዚህም ወደ ሸለቆ ውስጥ የወረዱ ሰዎችን ምሳሌ አደረጉ። ሁሉም ያመጧቸው ትናንሽ እንጨቶች ተጠራቅመው ዳቦዋቸውን ለመጋገር እስኪያስችሏቸው ድረስ እያንዳንዳቸው ትናንሽ እንጨት ይዘው መጡ። ትናንሽ ወንጀሎችም ሰውዬው ሳይቶብት ወይም ከነርሱ አላህ ይቅር ሳይለው በነርሱ ምክንያት የተያዘ ጊዜ ያወድሙታል።
አላህ ዐዘ ወጀል ነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የላካቸው መልካምና በላጭ ስነምግባርን ሊሞሉ እንደሆነ ተናገሩ። ይህም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከርሳቸው በፊት የነበሩ መልክተኞች ላስተላለፉት የመልካምነት ጥሪ አሟይና ዐረቦች የነበሩበትን መልካም ስነምግባር ሊሞሉ ነው የተላኩት። ዐረቦች መልካምን የሚወዱና መጥፎን የሚጠሉ፣ የክብር፣ የቸርነትና የታላቅነት ባለቤት ነበሩ። ታዲያ ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዐረቦች የጎደላቸውን ስነምግባር ሊሞሉ ተላኩ። ለምሳሌ በዘር መኩራራት፣ ኩራት፣ ድሃን መናቅና ከዚህም ውጪ የሚጎድላቸው ስነምግባሮች ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው።
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ በሐዲሠል ቁድሲይ እንዲህ እንዳለ ተናገሩ። "የሰው ልጅ መከራና ችግር በሚወርዱበት ወቅት ጊዜን በማውገዝና በመሳደብ እኔን ያውከኛል ክብሬን ያሳንሳል። ምክንያቱም የሚከሰቱትን ነገሮች አስተናባሪው አላህ ሱብሓነሁ ብቻ ነው። ዘመንን መሳደብ አላህን ዐዘ ወጀል እንደመሳደብ ነው። ጊዜ ለአላህ ትእዛዝ የተገራ ፍጡር ነው። ክስተቶች በአላህ ትእዛዝ ይከሰታሉ።
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዲን የቆመው ስራን አላህ ግዴታ ባደረገው መልኩ ያለምንም ማጓደል ወይም ያለምንም ማታለል በመፈፀም ስራን ለአላህ በማጥራት (በኢኽላስ) እና በእውነተኝነት ላይ በመመርኮዝ መሆኑን ተናገሩ። ለነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ታማኝ (ተቋርቋሪ) የምንሆነው ለማን ነው?" ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም: የመጀመሪያው: ለአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ስራን ለርሱ በማጥራት፣ በርሱ ባለማጋራት፣ በጌትነቱ በተመላኪነቱና በስሞቹና በባህሪያቶቹ በማመን፣ ትእዛዙን በማላቅና በርሱ ወደማመን በመጣራት ታማኝ መሆን (መቆርቆር) ነው። ሁለተኛው: ለመፅሀፉ ታማኝ (ተቆርቋሪ) መሆን ነው። እርሱም የተከበረው ቁርአን ነው። ይህም ቁርአን የአላህ ንግግር መሆኑን፣ የመጨረሻ መፅሀፉ መሆኑን፣ ከቁርአን በፊት የነበሩትን ሁሉንም ህግጋት የሻረ መሆኑን ማመን፤ እናልቀዋለን፣ በአግባቡ እናነበዋለን፣ ግልፅ በሆኑ ህግጋቶቹ እንተገብራለን፣ አሻሚ ትርጓሜ ባላቸው አንቀጾች እናምናለን፣ ቁርአንን አጣመው ከሚተረጉሙ ሰዎች ስለቁርአን እንከላከላለን፣ በምክሮቹ እንገሰፃለን፣ እውቀቶቹን እናሰራጫለን፣ ወደርሱም ጥሪ እናደርጋለን። ሶስተኛው: ለመልክተኛው ሙሐመድ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ታማኝ መሆን (መቆርቆር) ማለት እርሳቸው የመጨረሻ መልክተኛ መሆናቸውን በማመን፣ ይዘውት የመጡትን እውነት ብለን በመቀበል፣ ትእዛዛቸውን በመፈፀም፣ ክልከላቸውንም በመራቅ፣ እርሳቸው ይዘውት በመጡት መልኩ ካልሆነ በቀር አላህንም ባለማምለክ ሐቃቸውን ማላቅ፣ ማክበር፣ ጥሪያቸውን ማሰራጨት፣ ሸሪዓቸውን ማስፋፋትና እርሳቸው ላይ የሚነዛን ብዥታንም ውድቅ ማድረግ ነው። አራተኛው: ለሙስሊም መሪዎች ታማኝ መሆን (መቆርቆር) ማለት: በሐቅ ላይ በማገዝ፣ በጉዳያቸው ባለመቀናቀን፣ አላህን በታዘዙበት ጉዳይም ትእዛዛቸውን በመስማትና በመታዘዝ ነው። አምስተኛው: ለሙስሊሞች ታማኝ መሆን (መቆርቆር) ማለት: ለነርሱ በጎ በመዋል፣ ጥሪ በማድረግ፣ በነርሱ ላይ ጉዳት ከማድረስ በመቆጠብ፣ ለነርሱ መልካሙን በማሰብ፣ በመልካምና አላህን በመፍራት ላይም ከነርሱ ጋር በመተጋገዝ ነው።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁሉም ቀን በሁሉም ለአቅመ አዳም በደረሰ ሙስሊም ላይ ሁሉ በመገጣጠሚያ አጥንቶቹ ቁጥር ያህል አላህ ለሰጠው ጤንነት ለማመስገንና አጥንቶቹን መጨበጥና መዘርጋት በሚችል መልኩ ስለገጣጠመው ለአላህ ብሎ መመፅወት እንደሚገባው ገለፁ። ይህቺም ምፅዋት በመልካም ተግባራት ባጠቃላይ እንደሚፈፀምና ገንዘብ በመስጠት ላይ ብቻ እንዳልታጠረ ገለፁ። ከነርሱም መካከል: በተጣሉ ሁለት ሰዎች መካከል ማስታረቅና መፍረድ ምፅዋት ነው። መጓጓዣው ላይ ለመውጣት ለተሳነው ሰውዬ በማሰቀልህ ወይም እቃውን በመጫን ማገዝህ ምፅዋት ነው። ዚክር፣ ዱዓ ማድረግ፣ ሰላምታ ማቅረብና ሌሎችም መልካም ንግግሮች ምፅዋት ናቸው። ወደ ሶላት የምትራመዳት ሁሉም እርምጃ ምፅዋት ናት። መንገድ ላይ የሚያውክን ነገር ማስወገድም ምፅዋት ነው።
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሶሐቦች ጋር ለመሪዎችና አስተዳዳሪዎች በገርም ይሁን በከባድ፣ በሀብትም ይሁን በድህነት ወቅት፣ ትእዛዞቻቸው ነፍስ የምትወደውም ሆነ የምትጠላው ለነርሱ ታዛዥ እንዲሆኑ ቃል ኪዳን ፈፀሙ። መሪዎች በህዝብ አጠቃላይ ገንዘብ ወይም በማእረግ ወይም ከዚህ ውጪ ባሉ ነገሮች አድሎ ቢፈፅሙ እንኳ መሪዎችን በመልካም መታዘዝና መስማት ግዴታ መሆኑንና እነርሱንም አምፀው ላይወጡ ቃል ኪዳን ፈፀሙ። ምክንያቱም መሪዎችን በመዋጋት የሚመጣው ፈተናና ብልሽት በግፋቸው ሳቢያ ከሚከሰተው ብልሽት እጅግ የገዘፈ ነውና። በንግግራቸው ለአላህ ብቻ ያጠሩ (ሙኽሊስ) ሲሆኑና ወቃሻቸውን ሳይፈሩ እውነትን በማንኛውም ስፍራ መናገርም ሌላው ቃል ኪዳን የተጋቡት ጉዳይ ነው።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኛ ላይ መሪዎች እንደሚሾሙና ከፊል ስራዎቻቸው ከሸሪዓ ጋር የተስማማ ስለሆነ መልካም እንደምንለውና፤ ከፊሉን ደግሞ ከሸሪዓ ጋር ስለሚፃረር እንደምናወግዘው ተናገሩ። ውግዝ ተግባሮቻቸውን ማውገዝ ያልቻለና በቀልቡ የጠላ ሰው በርግጥም ከወንጀልና ንፍቅና ጠራ። በእጁ ወይም በአንደበቱ ማውገዝ የቻለ ሰውና በነርሱ ላይ ይህንን ያወገዘ በርግጥ ከወንጀልና ከወንጀል ተባባሪነት ሰላም ሆኗል። ነገር ግን ድርጊታቸውን የወደደና በርሱ ላይ የተከተላቸው እነርሱ እንደጠፉት ይጠፋል። ከዚያም ሶሐቦች ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ይህን አይነት ባህሪ የተላበሱ መሪዎችን አንዋጋምን?" ብለው ጠየቁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "በመካከላችሁ ሶላትን ቀጥ አድርገው እስከሰገዱ ድረስ በፍፁም እንዳትዋጓቸው!" በማለት ከዚህ ከለከሏቸው።
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለአሏህ እዝነትና ችሮታ እየነገሩን ነው። ይህም አንድ ሙስሊም በሀገሩ እና ጤነኛ ሳለ ልምድ ያደረገው መልካም ስራ ከዚያም ችግር ገጥሞት ታሞ ማድረግ ባይችል፣ ወይም በጉዞ ወይም ደግሞ በሌላ በየትኛውም በቂ ምክንያት ሳያደርገው ቢቀር ልክ ጤነኛና በሀገሩ ሆኖ ሲያደርግ እንደነበረው ምንዳ ሙሉ ሆኖ ይጻፍለታል።
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የኢስላም ሃይማኖት በኢኽላስና በእውነተኝነት ላይ የቆመ መሆኑን ተናገሩ። ይህም ሁሉም አማኝ የታዘዘውን አላህ ግዴታ ባደረገው መልኩ ምንም ሳያጓድልና ሳያታልል በተሟላ መልኩ እስኪፈፅም ድረስ ነው ቅን እንዲሆን የታዘዘው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ለማን ነው ተቆርቋሪነቱ (ታማኝነቱ)?" ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም እንዲህ አሉ፦ በመጀመሪያ: ጥራት ለተገባውና ከፍ ላለው አላህ ተቆርቋሪ (ታማኝ) መሆን ነው። ይህም፦ ለሱ የምንሰራውን ስራ በማጥራትና ባለማጋራት፣ በጌትነቱ፣ በተመላኪነቱ፣ በስሞቹና በባህሪያቶቹ በማመን፣ ትእዛዞቹን በማላቅና በሱ ወደማመን ሌሎችን በመጣራት ነው። ሁለተኛ: ለመጽሐፉ ተቆርቋሪ (ታማኝ) መሆን ነው። እሱም የተከበረው ቁርአን ነው። ይህም: ቁርአን የአላህ ቃል መሆኑንና የመጨረሻው መጽሐፉ መሆኑን በማመን፣ ከእሱ በፊት የነበሩትን ሁሉ ድንጋጌዎች የሻረ መሆኑን በማመን፣ እሱን በማላቅ፣ ትክክለኛ በሆነ መልኩ በማንበብ፣ ግልፅ የሆኑትን በመተግበር አሻሚ የሆኑትን በማመን፣ ከአጥማሚዎች ትርጓሜም በመከላከል፣ በተግሳፆቹ በመመከር፣ ውስጡ ያሉትን እውቀቶች በማሰራጨትና ወደርሱ በመጣራት ነው። ሶስተኛ: ለመልክተኛው ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) መሆን ነው። ይህም: እሳቸው ከመልክተኞች የመጨረሻ መሆናቸውን በማመን፣ ከሳቸው የመጣውን ሁሉ እውነትነቱን በመቀበል፣ ትእዛዛቸውን በመፈፀም፣ ክልከላቸውን በመራቅ፣ እሳቸው ባመጡት ድንጋጌ ካልሆነ በቀር አላህን ባለማምለክ፣ ሐቃቸውን በማላቅና በማክበር፣ ጥሪያቸውን በማሰራጨት፣ ሸሪዐቸውን በማስፋፋት፣ እሳቸው ላይ የሚቀርቡ ክሶችን ውድቅ በማድረግ ነው። አራተኛ: ለሙስሊም መሪዎች ቅን ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) መሆን ነው። ይህም: በሀቅ ላይ በመተባበር፣ ጉዳያቸውን ባለመጋፋትና በአላህ ትእዛዛቶች ሲያዙን እነሱን ሰምቶ በመታዘዝ ነው ። አምስተኛ: ለሙስሊሞች ተቆርቋሪ (ቅን/ ታማኝ) መሆን ነው። ይህም: ለነሱ በጎ በማድረግ፣ እነሱን ወደ በጎ በመጣራት፣ እነሱ ላይ ጉዳት ከማድረስ በመቆጠብ፣ ለነሱ መልካምን በመውደድ፣ በበጎና አላህን በመፍራት ላይ ከነርሱ ጋር በመተባበር ነው።