





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ከዋኢል አልሐድረሚይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ሰለማ ቢን የዚድ አልጁዕፊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና የአላህን መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት ጠየቀ: "የአላህ ነቢይ ሆይ! ሐቃቸውን የሚጠይቁ ሐቃችንን ደግሞ የሚከለክሉን መሪዎች በኛ መካከል ቢመጡ ምን ያዙናል እስኪ ንገሩን?" እርሳቸውም ከርሱ ዘወር አሉ። እርሱም ድጋሚ ጠየቃቸው እርሳቸው ግን አሁንም ከርሱ ዘወር አሉ። እርሱም በድጋሚ ለሁለተኛ ወይም ለሶስተኛ ጊዜ ጠየቃቸው። በዚህ ጊዜ አሽዐሥ ቢን ቀይስ ጎተተው። እርሳቸውም "መሪያችሁን ስሙ ታዘዙም! በነርሱ ላይ የተሸከሙት ግዴታ አለባቸው። በናንተም ላይ የተሸከማችሁት ግዴታ አለባችሁ።" አሉ።»
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰዎች እንዲሰሙዋቸውና እንዲታዘዟቸው ሐቃቸውን ከሰዎች እየፈለጉ፤ በነርሱ ላይ ያለባቸውን ፍትህ ማስፈንን፣ ምርኮን ማከፋፈልን፣ ግፍን በመከላከል እኩልነት የመፍጠርን ሐቅ ግን ስለሚከለክሉ መሪዎች ከነርሱ ጋር ምን እንድናደርግ እንደሚያዙን ተጠየቁ። ነቢዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህንን ጥያቄ እንደጠሉ በሚያሳብቅ መልኩ ከርሱ ዘወር አሉ። ጠያቂው ግን ለሁለተኛና ለሶስተኛ ጊዜ ጥያቄውን ደገመላቸው። አሽዐሥ ቢን ቀይስም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - ጠያቂውን ዝም ለማስባል ጎተተው። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲመልሱለት እንዲህ አሉ: "የመሪዎቻችሁን ንግግር ስሙ፤ ትእዛዛቸውን ታዘዙ። በነርሱም ላይ የተጣለባቸው ፍትህን የማስፈን፣ የህዝብን ሐቅ የማሟላት ኃላፊነት አለባቸው። በናንተም ላይ የተጣለባችሁ የመታዘዝ፣ ሐቃቸውን የመወጣት፣ በሚያደርሱት ግፍ ላይ የመታገስ ግዴታ አለባችሁ።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "የእስልምና ሃይማኖት ገር ነው። አንድም ሰው የእስልምናን ሃይማኖት ከመጠን በላይ አያጠብቅም (ሃይማኖቱ) የሚያሸንፈው ቢሆን እንጂ፤ ሚዛናዊ ሁኑ! አቀራርቡ! አብሽሩ! በማለዳ አምልኮ፣ በቀትር አምልኮና በተወሰነ የሌሊት አምልኮ ታገዙ!"
ቡኻሪ ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የእስልምና ሃይማኖት በሁሉም ጉዳዮች በገርነትና በማቅለል ላይ የተገነባ መሆኑን ገለፁ። አለመቻልና አስገዳጅ ምክንያቶች ሲኖሩም ገርነቱ ይጨምራል። በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ከአቅም በላይ መጥለቅና ገራገርነትን መተውም መጨረሻው አለመቻልና ሁሉንም ወይም የተወሰነውን ስራ ማቋረጥ ነው ቀጥለውም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወሰን ሳያልፉ ሚዛናዊ በመሆን ላይ አነሳሱ። አንድ ባሪያ ከታዘዘበት ነገር ማጓደል አይኖርበትም፤ የማይችለውንም ለመስራት አይጫንበትም። ሙሉ ለሙሉ መስራት ካቃተው ወደ ሙሉነት ቀረብ አድርጎ መስራት እንደሚገባ ገለፁ። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስራን አሟልቶ መስራት ያቃተው ሰው ብታንስ እንኳ ዘውታሪነቷን ለማስቀጠል የምትሠራ ሥራ ትልቅ ምንዳ እንደምታስገኝ አበሰሩ። አለመቻል በራሱ ድክመት የመጣ እስካልሆነ ድረስ የምንዳ መጉደልን አያስከትልምና። ዱንያ እውነታዋ ወደ መጪው ዓለም የምንጓዝበት የጉዞና የመሸጋገሪያ ሀገር እንደመሆኗ መጠን ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አምልኮን ነቃ በሚያደርጉ ሶስት ወቅቶች ላይ ዘውትረን በመፈፀም እንድንታገዝ አዘዙ። የመጀመሪያው: የማለዳ ጉዞ ነው: ይህም በመጀመሪያው የቀን ክፍል በማምለክ ነው። ወቅቱም በፈጅር ሶላትና በፀሐይ መውጣት መካከል አምልኮን መፈፀም ማለት ነው። ሁለተኛው: ከዝሁር በኋላ የቀትር ጉዞ ነው። ሶስተኛው: የሌሊቱን ሁሉ ወይም የተወሰነው ክፍል ላይ የሌሊት ጉዞ ነው። የሌሊት ስራ ከቀን ስራ የሚከብድ ስለሆነ "የተወሰነ ከሌሊትም" በማለት የተወሰነውን ሰአት ብቻ እንድናመልክበት አዘዙ።
ከሑዘይፋህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "እነሆ የሚዋሹና ግፈኛ የሆኑ መሪዎች ይመጣሉ። ውሸታቸውን አምኖ የተቀበለና በበደላቸው ላይ ያገዛቸው እርሱም ከኔ አይደለም። እኔም ከርሱ አይደለሁም። ወደኔ ምንጭም (ወደ ሐውድ) አይመጣም። የነርሱን ውሸት አምኖ ያልተቀበለና በበደላቸውም ላይ ያላገዛቸው ሰው ደሞ እርሱ ከኔ ነው። እኔም ከርሱ ነኝ። ወደኔ ምንጭ (ሐውድም) ይመጣል።"
አሕመድ ዘግበውታል።ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እርሳቸው ከሞቱ በኋላ ሲናገሩ የሚዋሹ፣ የማይሰሩትን የሚናገሩና በፍርዳቸው የሚበድሉ መሪዎች በሰዎች ላይ እንደሚሾሙ፤ ወደነርሱ ስራ ገብቶ ውሸታቸውን አምኖ የተቀበለ ወይም ወደነርሱ ለመቃረብ በሚልና እነርሱ ዘንድ ያለውን በመከጀል ለነርሱ የሚመቻቸውን ፈትዋ እንደመስጠት የመሰለ በሚሰሩት ወይም በሚናገሩት በደል ላይ ያገዛቸው እኔ ከርሱ የጠራሁ ነኝ። እርሱም ከኔ አይደለም። እኔም ከርሱ አይደለሁም። የትንሳኤ ቀንም የከውሠርን ምንጭ ሳጠጣ ወደኔ አይመጣም። ወደነርሱ ተግባር ያልገባ፤ ውሸታቸውን ያልተቀበለና በበደላቸው ላይም ያላገዛቸው እርሱ ከኔ ነው። እኔም ከርሱ ነኝ። የትንሳኤ ቀንም ወደ (ሐውድ) ምንጬ ይመጣል ብለው ተናገሩ።
ከሱሀይብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ «ከናንተ በፊት ከነበሩት ህዝቦች መካከል አንድ ንጉስ ነበር። ለርሱም ጠንቋይ ነበረው። (ጠንቋዩ) ያረጀ ጊዜም ለንጉሱ እንዲህ አለው: "እኔ አርጅቻለሁ። ጥንቆላ የማስተምረው አንድ ህፃን ልጅ ወደ እኔ ላክልኝ።" ንጉሱም የሚያስተምረውን ህፃን ልጅ ወደርሱ ላከለት። ልጁም ወደ ጠንቋዩ መንገድ ሲጀምር አንድ ባህታዊ ይመለከታል። እርሱ ዘንድም ተቀምጦ ንግግሩን ያዳምጥና ያስደስተዋል። ዘውትር ወደ ጠንቋዩ ዘንድ ሲሄድ በባህታዊው በኩል ሲያልፍ ተቀምጦ አዳምጦ ይሄዳል። ጠንቋዩም (በማርፈዱ) ይመታዋል። ይህንንም ያጋጠመውን ቅሬታ ለባህታዊው ነገረው። ባህታዊውም: "ጠንቋዩ ይመታኛል ብለህ ከፈራህ ቤተሰቤ ነው ያዘገየኝ በለው። ቤተሰብህ ይመቱኛል ብለህ ከፈራህ ደሞ ጠንቋዩ ነው ያዘገየኝ በላቸው።" አለው። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ አንድ ቀን በመንገዱ ሰዎች እንዳያልፉ መንገድ በዘጋ ትልቅ እንስሳ በኩል አለፈ። እንዲህም አለ: "ጠንቋዩ ነው ትክክለኛ ወይስ ባህታዊው ነው ትክክለኛ የሚለውን ዛሬ ማወቅ እችላለሁ።" ብሎ ድንጋይ አነሳና "አላህ ሆይ! ከጠንቋዩ እምነት ይልቅ የባህታዊው እምነት አንተ ዘንድ ተወዳጅ ከሆነ ሰዎች በመንገዳቸው ያልፉ ዘንድ ይህንን እንስሳ ግደል።" በማለት ወረወረውና ገደለው። ሰዎችም አለፉ። ይህንንም ለባህታዊው ነገረው። ባህታዊውም ይህንን ሲሰማ "ልጄ ሆይ! አንተ ዛሬ ከኔ የተሻልክ ሆነሃል። ጉዳይህ የማየውን ያህል ደርሷልና ትፈተናለህ። ፈተና ሲገጥምህም ወደ እኔ እንዳትጠቁም።" አለው። ልጁም እውሮችንና ለምጣሞችን ይፈውስ፤ ከተለያዩ በሽታዎችም ሰዎችን ያክም ነበር። ይህንንም ታውሮ የነበረ አንድ የንጉሱ አማካሪ ሰማና በርካታ ስጦታዎችን ሸክፎ ወደርሱ በመምጣት "ይህ ሰብስቤ ያመጣሁት ከፈወስከኝ ያንተ ይሆናል።" አለው። ልጁም "እኔ አንድንም ሰው አልፈውስም። የሚፈውሰው አላህ ነው። በአላህ ካመንክ አላህን እለምንልህና ትፈወሳለህ።" አለው። በአላህም አመነ አላህም ፈወሰው። ንጉሱም ዘንድ በመምጣት ከዚህ በፊት ይቀመጥ እንደነበረው ተቀመጠ። ንጉሱም ለርሱ: "አይንህን ማነው የመለሰልህ?" ብሎ ጠየቀው። አማካሪውም: "ጌታዬ" አለው። ንጉሱም: "ከኔ ውጪ ሌላ ጌታ አለህን?" አለው። አማካሪውም: "የኔም ያንተም ጌታ አላህ ነው።" በማለት መለሰለት። ልጁን እስኪጠቁም ድረስም ይዞት ከማሰቃየት አልተወገደም። ልጁም ተይዞ ቀረበ። ንጉሱም በመደነቅ "ልጄ ሆይ! ጥንቆላህ አይነ ስውራንና ለምጣሞችን እስከመፈወስ ደረሰ! ይህንን ሰራህ! ይህንን ሰራህ!" አለው። ልጁም: "እኔ አንድንም አልፈውስም። የሚፈውሰው አላህ ነው።" በማለት መለሰ። ይዞትም ባህታዊውን እስኪጠቁም ድረስ ልጁን ከማሰቃየት አልተወገደም። ባህታዊውም ተይዞ ቀረበ። ለርሱም "ከሃይማኖትህ ውጣ!" ተባለ። እርሱም "በፍፁም!" አለ። መጋዝ አስመጡናና አናቱ መሀል ላይ አስቀመጡት። ከዛም ሁለት ቦታ ከፍለው ጣሉት። ቀጥለው የንጉሱን አማካሪ አቀረቡት። ለርሱም "ከሃይማኖትህ ውጣ!" ተባለ። እርሱም "በፍፁም!" አለ። መጋዝ አናቱ መሀል ላይ አስቀመጠ። ከዛም ሁለት ቦታ ከፍሎ ጣለው። ቀጥለው ልጁን አቀረቡት። "ከሃይማኖትህ ውጣ!" ተባለ። እርሱም "በፍፁም!" አለ። ንጉሱም ልጁን ለተወሰኑ ወታደሮቹ ሰጠና "እርሱን እንዲህ እንዲህ ወደሚባል ተራራ ውሰዱትና ተራራው ላይ ይዛችሁት ውጡ። የተራራው ጫፍ ላይ ስትደርሱ ከሃይማኖትህ ውጣ በሉት። ከተቀበለ አምጡት ካልተቀበለ ወርውሩት።" አላቸው። እርሱንም ወደ ተራራው ይዘውት ወጡ። ልጁም "አላህ ሆይ! በፈለግከው መንገድ ከነርሱ ተንኮል ጠብቀኝ" አለ። ተራራው ተርገፈገፈና ወደቁ። ልጁም ወደ ንጉሱ መጣ። ንጉሱም ለልጁ "ወታደሮቹ ምን ሆኑ?" አለው። ልጁም "አላህ ከነርሱ ተንኮል ጠበቀኝ" አለው። ንጉሱም ለሌሎች ወታደሮች ልጁን ሰጠ። እንዲህም አላቸው: "ልጁን በጀልባ ጭናችሁ ውሰዱት። የባህሩ መሃል ስትደርሱ ከሃይማኖትህ ውጣ በሉት። ከተቀበለ አምጡት ካልተቀበለ ወደ ባህሩ ጣሉት።" ልጁንም ይዘውት ሄዱ። ልጁም "አላህ ሆይ! በፈለግከው መንገድ ከነርሱ ተንኮል ጠብቀኝ" አለ። ጀልባዋ ተገለበጠችና ሰመጡ። ልጁም ወደ ንጉሱ መጣ። ንጉሱም ለልጁ "ወታደሮቹ ምን ሆኑ?" አለው። ልጁም "አላህ ከነርሱ ተንኮል ጠበቀኝ" አለው። አክሎም "እኔ የማዝህን እስካልፈፀምክ ድረስ ልትገለኝ አትችልም" አለው። ንጉሱም: "ምንድነው እርሱ?" አለው። ልጁም "በቅድሚያ ሰዎችን አንድ ሰፊ ሜዳ ላይ ሰብስበህ የዘንባባ ግንድ ላይ ትሰቅለኛለህ። ቀጥሎ ከሰገባዬ ቀስት ትውስዳለህ። ቀጥሎ ቀስቱን ከደጋኑ መሃል ካደረግክ በኋላ "የዚህ ልጅ ጌታ በሆነው በአላህ ስም እወረውራለሁ።" በል። ከዛም ወርውረው። አንተ ይህንን ካደረግክ ትገለኛለህ።" አለው። ንጉሱም ሰዎችን አንድ ሰፊ ሜዳ ላይ ሰበሰበና ልጁን የዘንባባ ግንድ ላይ ሰቀለው። ቀጥሎ ከሰገባው ቀስቱን አወጣና ቀስቱን ደጋኑ መሃል ላይ ካደረገ በኋላ "የዚህ ልጅ ጌታ በሆነው በአላህ ስም እወረውራለሁ።" አለና ወረወረ። ቀስቷም ቅንጡ (ከጆሮው ጎን ያለ አጥንት) ላይ ተሰካች። ልጁም ቀስቱ ያረፈችበትን የጆሮውን ጎን እንደያዘ ሞተ። ሰዎችም "በልጁ ጌታ አምነናል። በልጁ ጌታ አምነናል። በልጁ ጌታ አምነናል።" አሉ። ንጉሱም ጋር በመምጣት እየማሉ "ያ የምትፈራው ነገር ተከሰተብህ አይደል? የምትፈራው ደረሱ፤ ሰዎች አመኑ።" ተባለ። ንጉሱም በመንገድ ዳር ዳር ጉድጓድ እንዲቆፈር አዘዘ። ጉድጓዱም ተቆፈረ። እሳትም ተቀጣጠለ። እንዲህም አለ: "ከሃይማኖቱ ለቆ ያልወጣን። እሳት ውስጥ አቃጥሉት። ወይም እሳት ውስጥ ግባ በሉት።" ህዝቡ ሁሉ አንዲት ህፃን ልጅ የተሸከመች ሴት እስክትቀር ድረስ ንጉሱ እንዳለው እሳት ውስጥ ገቡ። እሳት ውስጥ ለመግባት አመነታች። ያዘለችው ጨቅላ ግን "እናቴ ታገሺ አንቺ እውነት ላይ ነሽ።" አላት።»
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለው ተናገሩ: ከእኛ በፊት ከነበሩት ህዝቦች መካከል አንድ ንጉስ ነበር። ለርሱም አንድ ጠንቋይ ነበረው። ጠንቋዩ ያረጀ ጊዜ ለንጉሱ እንዲህ አለው: "እኔ አርጅቻለሁ። ጥንቆላ የማስተምረውን ብላቴና ወደ እኔ ላክልኝ።" ንጉሱም የሚያስተምረውን ብላቴና ልጅ ወደርሱ ላከለት። ልጁ ወደ ጠንቋዩ መንገድ ሲጀምር መንገድ ላይ አንድ ባህታዊ ነበር። አንድ ቀን እርሱ ዘንድ ተቀምጦ ንግግሩን ያዳምጥና ያስደስተዋል። ዘወትር ወደ ጠንቋዩ ዘንድ ሲሄድ በባህታዊው በኩል ሲያልፍ ተቀምጦ አዳምጦ ይሄዳል። ጠንቋዩም (በማርፈዱ) ይመታዋል። ይህንንም ያጋጠመውን ቅሬታ ለባህታዊው ነገረው። ባህታዊውም: "ጠንቋዩ ይመታኛል ብለህ ከፈራህ ቤተሰቤ ነው ያዘገየኝ በለው። ቤተሰብህ ይመቱኛል ብለህ ከፈራህ ደሞ ጠንቋዩ ነው ያዘገየኝ በላቸው።" አለው። በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ አንድ ቀን ሰዎች እንዳያልፉ መንገድ በዘጋ ትልቅ እንስሳ በኩል አለፈ። እንዲህም አለ: "ዛሬ ጠንቋዩ ነው ትክክለኛ? ወይስ ባህታዊው ነው ትክክለኛ? የሚለውን አውቃለሁ።" ድንጋይም አነሳና "አላህ ሆይ! ከጠንቋዩ እምነት ይልቅ የባህታዊው እምነት አንተ ዘንድ ተወዳጅ ከሆነ ሰዎች በመንገዳቸው ያልፉ ዘንድ ይህንን እንስሳ ግደል።" በማለት ወረወረውና ገደለው። ሰዎችም አለፉ። ይህንንም ለባህታዊው ነገረው። ባህታዊውም ለርሱ እንዲህ አለው: "ልጄ ሆይ! አንተ ዛሬ ከኔ የተሻልክ ሆነሃል። ጉዳይህ የማየውን ያህል ደርሷልና ትፈተናለህ። ፈተና ሲያጋጥምህም ወደ እኔ እንዳትጠቁም።" አለው። ልጁም እውሮችንና ለምጣሞችን ይፈውስ ጀመር። በአላህ ፍቃድም ከተለያዩ በሽታዎችም ሰዎችን ያክም ነበር። ይህንንም ታውሮ የነበረ አንድ የንጉሱ አማካሪ ሰማና በርካታ ስጦታዎችን ሸክፎ ወደርሱ በመምጣት እንዲህ አለው: "ይህ ሰብስቤ ያመጣሁት ከፈወስከኝ ያንተ ይሆናል።" ልጁም "እኔ አንድንም ሰው አልፈውስም። የሚፈውሰው አላህ ነው። በአላህ ካመንክ አላህን እለምንልህና ትፈወሳለህ።" አለው። በአላህም አመነ አላህም ፈወሰው። ንጉሱም ዘንድ በመምጣት ከዚህ በፊት ይቀመጥ እንደነበረው ተቀመጠ። ንጉሱም ለርሱ: "አይንህን ማነው የመለሰልህ?" ብሎ ጠየቀው። አማካሪውም: "ጌታዬ" አለው። ንጉሱም: "ከኔ ውጪ ሌላ ጌታ አለህን?" አለው። አማካሪውም: የኔም ያንተም ጌታ አላህ ነው።" በማለት መለሰ። ልጁን እስኪጠቁም ድረስም ይዞት ከማሰቃየት አልተወገደም። ልጁም ተይዞ ቀረበ። ንጉሱም በመደነቅ እንዲህ አለው: "ልጄ ሆይ! ጥንቆላህ አይነ ስውራንና ለምጣሞችን እስከመፈወስ ደረሰ ማለት ነዋ! ይህንን ሰራህ! ይህንን ሰራህ!" ልጁም: "እኔ አንድንም አልፈውስም። የሚፈውሰው አላህ ነው።" በማለት መለሰ። ይዞትም ባህታዊውን እስኪጠቁም ድረስ ልጁን ከማሰቃየት አልተወገደም። ባህታዊውም ተይዞ ቀረበ። ለርሱም "ከሃይማኖትህ ውጣ!" ተባለ። እርሱም "በፍፁም!" አለ። መጋዝ አስጠሩና አናቱ መለያ ጋር አስቀመጡት። ከዛም ለሁለት ሰንጥቀው ጣሉት። ቀጥለውም የንጉሱን አማካሪ አቀረቡት። ለርሱም "ከሃይማኖትህ ውጣ!" ተባለ። እርሱም "በፍፁም!" አለ። መጋዝ አናቱ መለያ ጋር ተደረገና ለሁለት ተሰንጥቆ ወደቀ። ቀጥለውም ልጁን አቀረቡት። "ከሃይማኖትህ ውጣ!" ተባለ። እርሱም "በፍፁም!" አለ። ንጉሱም ልጁን ከሶስት እስከ አስር ለሚጠጉ ወታደሮቹ አሳልፎ ሰጠው። "እርሱን እንዲህ እንዲህ ወደሚባል ተራራ ውሰዱትና ተራራው ላይ ይዛችሁት ውጡ። የተራራው ጫፍ ላይ ስትደርሱ ከሃይማኖትህ ውጣ በሉት። ከተቀበለ አምጡት ካልተቀበለ ወርውሩት።" አላቸው። እርሱንም ወደ ተራራው ይዘውት ወጡ። ልጁም "አላህ ሆይ! በፈለግከው መንገድ ከነርሱ አንተው ብቃኝ።" አለ። ተራራው ተርገፈገፈ፣ ሀይለኛ መንቀጥቀጥ ተንቀጥቅጦ ወደቁ። ልጁም ወደ ንጉሱ መጣ። ንጉሱም ለልጁ "ወታደሮቹ ምን ሆኑ?" አለው። ልጁም "አላህ ከነርሱ ተንኮል ጠበቀኝ" አለ። ንጉሱም ለሌሎች ወታደሮች ልጁን ሰጠ። እንዲህም አላቸው: "ልጁን በጀልባ ጭናችሁ ውሰዱት። የባህሩ መሃል ስትደርሱ ከሃይማኖትህ ውጣ በሉት። ከተቀበለ አምጡት ካልተቀበለ ወደ ባህሩ ጣሉት።" ልጁንም ይዘውት ሄዱ። ልጁም "አላህ ሆይ! በፈለግከው መንገድ ከነርሱ ተንኮል ጠብቀኝ።" አለ። ጀልባዋ ተገለበጠችና ሰመጡ። ልጁም ወደ ንጉሱ መጣ። ንጉሱም ለልጁ "ወታደሮቹ ምን ሆኑ?" አለው። ልጁም "አላህ ከነርሱ ተንኮል ጠብቀኝ።" አለው። አክሎም "አንተ እኔ የማዝህን እስካልፈፀምክ ድረስ ልትገለኝ አትችልም።" አለው። ንጉሱም: "ምንድነው እርሱ?" አለው። ልጁም "በቅድሚያ ሰዎችን አንድ ገላጣ ሜዳ ላይ ሰብስበህ የዘንባባ ግንድ ላይ ትሰቅለኛለህ። ቀጥሎ ከሰገባዬ ቀስት ትውስዳለህ። ቀጥሎ ቀስቱን ከደጋኑ መሃል ካደረግክ በኋላ 'የዚህ ልጅ ጌታ በሆነው በአላህ ስም እወረውራለሁ።' በል። ከዛም ወርውረው። አንተ ይህንን ካደረግክ ትገለኛለህ።" አለው። ንጉሱም ሰዎችን አንድ ሜዳ ላይ ሰበሰበና ልጁን የዘንባባ ግንድ ላይ ሰቀለው። ቀጥሎ ከሰገባው ቀስቱን አወጣና ቀስቱን ደጋኑ መሃል ላይ ካደረገ በኋላ "የዚህ ልጅ ጌታ በሆነው በአላህ ስም እወረውራለሁ።" አለና ወረወረ። ቀስቷም በአይኑና በጆሮው መካከል ቅንጡ ላይ ተሰካች። ልጁም ቀስቱ ያረፈችበትን የጆሮውን ጎን እንደያዘ ሞተ። ሰዎችም "በልጁ ጌታ አምነናል። በልጁ ጌታ አምነናል። በልጁ ጌታ አምነናል።" አሉ። ንጉሱም ጋር በመምጣት "አየህ ያ የምትፈራውን ነገር? ያለ ጥርጥር ተከሰተብህ። ይሀውም ሰዎች ልጁን ተከትለው ሁሉም በጌታቸው አመኑ።" ተባለ። ንጉሱም በየመንገድ ዳር ዳር ትልቅና ረጃጅም ጉድጓድ እንዲቆፈር አዘዘ። ጉድጓዱም ተቆፈረ። እሳትም በውስጡ ተቀጣጠለ። እንዲህም አለ: "ከሃይማኖቱ ለቆ ያልወጣን። እሳት ውስጥ ጣሉትና አቃጥሉት።" ህዝቡ ሁሉ አንዲት ህፃን ልጅ የተሸከመች ሴት እስክትቀር ድረስ ንጉሱ እንዳለው እሳት ውስጥ ተወረወረ። እሳት ውስጥ ለመግባት አመነታች። ቦታዋን እንደያዘች ቆመች። እሳት ውስጥ መግባቱን ጠላች። ያዘለችው ጨቅላ ግን እንዲህ አላት: "እናቴ ታገሺ አንቺ እውነት ላይ ነሽ።"
ከኡበይ ቢን ከዕብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ሰውዬ ነበር። ከርሱ የበለጠ ቤቱ ከመስጂድ የራቀ አንድም ሰው አላውቅም። ሆኖም አንድም ሶላት አታመልጠውም ነበር። ለርሱም እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀረበለት ‐ ወይም እንዲህ ብየ ጠየቅኩት ‐ : "እንደው በጨለማና ቀን ላይ መሬቱ በሚግልበት ወቅት የምትጋልበው አህያ ብትገዛ አይሻልም?" እርሱም "ቤቴ ከመስጂዱ ጎን ቢሆን አያስደስተኝም። እኔ ወደ መስጂድ ስመጣ የምራመደው እርምጃና ወደ ቤተሰቦቼ ስመለስም የምራመደው እርምጃ እንዲፃፍልኝ እፈልጋለሁ።" አለ። የአላህም መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "በርግጥም አላህ ይህንን ሁሉ ላንተ ሰብስቦልሃል።" አሉት።»
ሙስሊም ዘግበውታል።ኡበይ ቢን ከዕብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተናገሩት: "አንድ ቤቱ ከመስጂደ ነበዊይ እጅግ የራቀ ከአንሷር የሆነ ሰውዬ ነበር። አንድም ሶላት አታመልጠውም ነበር። ይልቁኑም ሁሉንም ሶላት ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ተገኝቶ ይሰግድ ነበር። ለርሱም እንዲህ ተባለ: እንደው በምሽቱ ጨለማና ቀን ላይ መሬቱ በሚግልበት ወቅት የምትጋልበው አህያ ብትገዛ አይሻልም? እርሱም እንዲህ አለ: "ቤቴ ከመስጂዱ ጎን ቢሆን አያስደስተኝም። እኔ ወደ መስጂድ ስመጣ የምራመደው እርምጃና ወደ ቤተሰቦቼ ስመለስም የምራመደው እርምጃ እንዲፃፍልኝ እፈልጋለሁ።" አለ። ንግግሩም ነቢዩ ዘንድ ደረሰ። እርሳቸውም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "በርግጥም አላህ ይህንን ሁሉ ላንተ ሰብስቦልሃል።"
የአማኞች እናትና የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤት ከሆነችው ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከዓኢሻ ጋር ሆነው ሳሉ ሐውላእ ቢንት ቱወይት ቢን ሐቢብ ቢን አሰድ ቢን ዐብዲልዑዛ በዓኢሻ በኩል አለፈች። እኔም "ይህቺ ሐውላእ ቢንት ቱወይት ናት። እርሷም ሌሊት እንደማትተኛ ገለፁልኝ።" አልኳቸው። የአላህ መልክተኛም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "ሌሊት አትተኛም?! የምትችሉትን ስራ ያዙ። በአላህ እምላለሁ። (መስራት) እስክትሰለቹ ድረስ አላህ (ምንዳ ከመስጠት) አይሰለችም።" አሉ።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ዘንድ ሐውላእ ቢንት ቱወይት - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነበረች። ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሲገቡ እርሷ ወጣች። ዓኢሻም እንዲህ አለቻቸው: ይህቺ ሴት ሌሊት አትተኛም። ይልቁንም ሌሊቱን በሙሉ የምታሳልፈው በሶላት ነው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በራሷ ላይ ማክበዷን በማውገዝ እንዲህ አሉ: ሌሊት አትተኛም?! ከመልካም ስራ መዘውተር የምትችሉትን ያህል ብቻ በመስራት ተጠመዱ። በአላህ እምላለሁ! አላህ ባሮቹ ስራን ከመስራት እስኪሰለቹ እና እስኪተዉ ድረስ ለደጋግና ታዛዥ ባሮቹ በአምልኳቸው፣ በመልካምና በጎ ስራዎቻቸው ምንዳና አጅር ከመስጠት አይሰለችም።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "ከናንተ መካከል እውነታን ተመልክቶ ወይም አውቆ ከመናገር ማናችሁንም ቢሆን ለሰዎች ያለው ፍራቻ እንዳይከለክለው።"
ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በባልደረቦቻቸው መካከል ኹጥባ አደረጉ። ከመከሯቸው ጉዳዮችም አንዱ የትኛውም ሙስሊም እውነትን ተመልክቶ ወይም አውቆ ከመናገርና በርሱ ከማዘዝ ሰዎችንና ሀይላቸውን መፍራትና መስጋት እንዳይከለክለው ነው።
ከዑሥማን አሽሸሓም እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «እኔና ፈርቀድ አስሰበኺይ ወደ ሙስሊም ቢን አቢ በክራ መኖሪያ እርሱም መሬቱ ላይ ሳለ ሄድን። እርሱም ዘንድ ገባንና: "አባትህ ስለ ፈተና ሐዲሥ ሲናገር ሰምተሀዋልን?" አልነው። እርሱም እንዲህ አለ: ‹አዎን! አባ በክራን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንዲህ ብሎ ሲያወራ ሰምቼዋለሁ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:- 'አዋጅ! ፈተና ትኖራለች። አዋጅ! ቀጥሎም በዛች ፈተና ከተራማጅ ተቀማጭ የተሻለ የሚሆንባት፤ ወደ ፈተናዋ ከሚሮጥ የሚራመድ የተሻለ የሚሆንባት ፈተና ትከሰታለች። አዋጅ! ይህቺ ፈተና እውን የሆነች ወይም የተከሰተች ጊዜ ለርሱ ግመል ያለው ሰው ወደ ግመሉ ይጠጋ! ለርሱ ፍየል ያለውም ሰው ወደ ፍየሉ ይጠጋ! ለርሱ መሬት ያለውም ሰው ወደ መሬቱ ይጠጋ!' አንድ ሰውዬም እንዲህ በማለት ጠየቃቸው 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! እስኪ ንገሩን ግመልም፣ ፍየልም፣ መሬትም የሌለው ሰውስ ወደየት ይጠጋ?' እርሳቸውም 'ወደ ሰይፉ ያምራና ስለቱን በድንጋይ ይስበር። ከዚያም በመሸሽ መዳን ከቻለ ይሽሽ! አላህ ሆይ! አድርሻለሁኝን? አላህ ሆይ! አድርሻለሁኝን?' አሉ። አንድ ሰውዬም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! እስኪ ንገሩኝ አስገድደው ወደ አንዱ ጎራ ወይም አንዱ ቡድን ላይ ቢወስዱኝና አንዱ በሰይፉ ቢመታኝ ወይም ቀስት መጥቶ ቢወጋኝስ (ወንጀል ይኖርብኛልን?)' በማለት ጠየቃቸው። እርሳቸውም: 'ያንተም የራሱንም ወንጀል ወደርሱ ይመለሳል። ከእሳት ጓዶችም ይሆናል።' አሉት።›"»
ሙስሊም ዘግበውታል።ዑሥማን አሽሸሓምና ፈርቀድ አስሰብኺይ የታላቁ ሶሓቢይ የአቢ በክራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ልጅ የሆነው ሙስሊም ዘንድ አባቱ ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በሙስሊሞች መካከል ስለሚኖር የርስበርስ ፈተናና ጦርነት ሰምቶ ሲያወራ ከሰማ እንዲነግራቸው ሊጠይቁት ሄዱ። እርሱም አዎን! ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እርሳቸው ከሞቱ በኋላ ፈተና እንደሚኖር ይህ ፈተናም በሚከሰት ጊዜም ይህንን ፈተና ችላ ብሎ የተቀመጠ ወደርሷ ከሚራመድ ይበልጣል። ምክንያቱም ቁጭ ያለው አይሳተፍባትምም ስለርሷም አይመራመርምና። ወደርሷ የሚራመድም ወደርሷ ለመመርመርና ለመሳተፍ ከሚሮጠው የተሻለ መሆኑን ተናገሩ። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በርሱ ዘመን ፈተናዋ የተከሰተችበት ወይም ያጋጠመችው ሰው የሚጠጋበት ስፍራ ካገኘ ወደዛ እንዲሸሽ እንዲህ በማለት ጥቆማ ሰጡ: ለርሱ የምትሰማራ ግመል ያለው ወደ ግመሉ ይጠጋ፤ ለርሱ የምትሰማራ ፍየል ያለው ሰው ወደ ፍየሉ ይጠጋ፤ ለርሱ መሬት፣ እርሻ ያለው ሰው ወደ መሬቱ ይጠጋ። አንድ ሰውዬም እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እስኪ ንገሩኝ ግመልም፣ ፍየልም፣ መሬትም የሌለው ሰው ወደየት ይጠጋ?" እርሳቸውም "ወደ መሳሪያው ያምራና ይስበረው ያዶምዱመው ከዚያም መሸሽ ከቻለ ነፍሱንና ልጁን ይዞ ይሽሽ።" አሉ። ከዚያም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶስት ጊዜ እንዲህ በማለት አላህን ምስክር አደረጉ: "አላህ ሆይ! መልዕክትህን አደረስኩኝን? አላህ ሆይ! መልዕክትህን አደረስኩኝን? አላህ ሆይ! መልዕክትህን አደረስኩኝን?" አንድ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እስኪ ንገሩኝ ከሁለቱ ቡድኖች ወይም ጭፍራዎች አንዱን እንድቀላቀል ብገደድና አንዱ በሰይፉ ቢመታኝ ወይም ቀስት መጥቶ ቢገድለኝ ወንጀል ይኖርብኛልን?" አላቸው። እርሳቸውም "የራሱና የተገደለው ሰው ወንጀል ወደርሱ ይመለሳል። የትንሳኤ ቀንም ከእሳት ጓዶች ይሆናል።"
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች ባጠቃላይ ይበልጥ ስነምግባራቸው እጅግ ያማረ ሰው ነበሩ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሰዎች ሁሉ ስነምግባራቸው እጅግ የተሟላ ሰው ናቸው። ንግግርን በማሳመር፣ መልካምን በመለገስ፣ ፊታቸውን በመፍታት፣ መጥፎ ከመስራት በመቆጠብ፣ ሌሎች የሚያደርሱባቸውን ጉዳት በመቻል በሁሉም ስነምግባሮችና መልካምነት ባጠቃላይ ግንባር ቀደም ናቸው።