





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ጥፍጥናን ቆራጩን ማስታወስ አብዙ።" ሞትን ማለታቸው ነው።
رواه الترمذي والنسائي وابن ماجهነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የሰው ልጅ እርሱን ሲያስታውሰው የመጪው ዓለምን የሚያስታውስበትንና ለዱንያ ጥፍጥና በተለይ ደሞ ክልክል ለሆኑ መጣቀሚያዎች ያለውን ፍቅር ከቀልቡ የሚያጠፋለትን ሞትን አብዝቶ እንዲያስታውስ አነሳሱ።
ከዐብደላህ ቢን ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር በሒጅር በኩል አለፍን። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለኛ እንዲህ አሉን: "እነርሱን ያገኛቸው አምሳያ እንዳያገኛችሁ ያሰጋልና እያለቀሳችሁ ካልሆነ በቀር እነዚያ ነፍሳቸውን ወደበደሉ ሰዎች መኖሪያ እንዳትገቡ።" ከዚያም ግመላቸውን አንቀሳቀሱና አልፈዋት እስኪሄድ ድረስ በፍጥነት ተጓዙ።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በሠሙዶች መኖሪያ በኩል ሲያልፉ ወደዚህ መንደር የሚገባ ሰው እነርሱ ላይ የደረሰውን በማስተንተን እያለቀሰ ካልሆነ በቀር ነፍሳቸውን ወደበደሉ ሰዎች መንደር ከመግባት ወይም ከመምጣት ከለከሉ። ይህም እነርሱን እንዳገኛቸው አይነት ቅጣት እንዳያገኘው ስለሚያሰጋ ነው። ቀጥለው እንስሳቸውን በጩኸት አስነስተው አልፈው እስኪሄዱ ድረስ ፈጥነው ተጓዙ።
ከሑዘይፋህ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ዘንድ ነበርን እንዲህም አለን: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ስለ ፈተና ሲያወሱ የሰማ ማንኛችሁ ነው?" የተወሰኑ ሰዎችም "እኛ ሰምተናቸዋል።" አሉ። ዑመርም "ምናልባት ሰማን የምትሉት ሰውዬው በቤተሰቡና በጎረቤቶቹ የሚፈተነውን አይነት ፈተና ይሆን?" አላቸው። እነርሱም "አዎ" አሉ። ዑመርም "ይህማ ሶላት፣ ፆምና ሶደቃ ያስምረዋል። ነገር ግን ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንደ ባህር ነውጥ ስለምትናወጠው ፈተና ሲያወሱ የሰማ ማንኛችሁ ነው?" አለ።» ሑዘይፋህ እንዲህ አለ: «ዑመር ሰዎችን ዝም አስባለ። እኔም: እኔ ሰምቻለሁ። አልኩኝ። ዑመርም "አላህ አባትህ ምን አይነት ልጅ እንዲወልድ ነው ያደረገልን! አንተ ሰምተሃልን?" አለ።» ሑዘይፋም እንዲህ አለ «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:- "ሰሌን ላይ የሚተኛ ሰው ቆዳው ላይ ሰንበር እንደሚያወጣው ፈተናም በቀልብ ላይ በተደጋጋሚ ትቀርባለች። ፈተናዋ ወደ ውስጡ የገባችበት ማንኛውም ቀልብ ጥቁር ጠብታ ቀልቡ ላይ ታርፋለች። ፈተናዋን ያወገዘ ማንኛውም ቀልብ ደሞ ነጭ ጠብታ ቀልቡ ላይ ታርፋለች። ይህም ሁለት ቀልብ እስኪሆን ድረስ ነው። ሰማይና ምድር እስከዘወተሩ ድረስ ፈተና የማይጎዳት እንደ ለስላሳ ድንጋይ የነጣ ቀልብ እና ሌላኛው ደግሞ እንደተገለበጠ ኩባያ ከስሜቱ ጋር የተስማማውን ካልሆነ በቀር ጥሩን ጥሩ የማይል መጥፎንም የማያወግዝ ጥቁር ሆኖ አመዳም ቀለም የያዘ ቀልብ ናቸው።"» ሑዘይፋ እንዲህም አለ፡ «ለዑመር በአንተ እና በፈተናዋ መካከል የተዘጋ በር አለ። ልትሰበርም ትቀርባለች ብዬ ነገርኩት። ዑመርም "አላህ ያጠንክርህና ይሰበራል ማለት ነው? ቢከፈትስ ድጋሚ ሊዘጋ ይችላልን?" አለ። እኔም አይ እንደውም ይሰበራል። ንግግሬ ምንም ስህተት የሌለው መሆኑንና ያ በር ማለት የአንድ ሰውዬ መገደል ወይም መሞት እንደሆነ አስረግጬ ነገርኩት።» አቡ ኻሊድ እንዲህ አለ: «ለሰዕድ እንዲህ አልኩት "የጠቆረ አመዳም ቀለም ማለት ምን ማለት ነው?" ሰዕድም "ከጥቁረት ጋር የተቀላቀለ ንጣት ነው።" አለኝ። "የተዘነበለ ባልዲ ማለትስ" አልኩት። እርሱም "የተገለበጠ ማለት ነው።" አለኝ።»
ሙስሊም ዘግበውታል።የአማኞች መሪ ዑመር ቢን ኸጧብ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከተወሰኑ ሶሓቦች ጋር ተቀምጦ ሳለ ለነርሱ እንዲህ አሏቸው: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ስለ ፈተና ሲያወሱ የሰማ ማንኛችሁ ነው?" አንዳንዶቹም "እኛ ስለፈተና ሲያወሱ ሰምተናቸዋል።" አሉ። ዑመርም ረዲየሏሁ ዐንሁ "ምንአልባት የሰማችሁት ሰውዬው በግል ህይወቱ ዙሪያ በሚስቱና በልጆቹ ላይ ባለው ወሰን ያለፈ ውዴታው፤ ለነርሱ ባለው ስስት፣ ብዙ መልካም ነገር ትቶ በነርሱ በመጠመድ ወይም ለነርሱ ማሟላት ያለበትን ሐቅ ባለማሟላት፤ ስርዓት ከማስያዝና ከማስተማር ቸልተኛ በመሆን የሚፈተነውን ፈተናና ልክ እንደዚሁ ሰውዬው በጎረቤቱና በመሳሰሉት የሚፈተነውን ፈተና ነው። ይህንን ነው አይደል ሰምተናል ያላችሁት?" አላቸው። እነርሱም "አዎ" አሉ። ዑመርም "ይህ ፈተናማ የሚያስፈርደው አላህን መተሳሰብ ነው። ከነዚህ መካከል እንደሶላት፣ ፆምና ሶደቃ ባሉ መልካም ስራዎችም ሊማሩ የሚችሉ ወንጀሎች አሉ።" አለ። "ነገር ግን ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አጠቃላይ ስለሆነው፣ ግዝፈቱ ከፍተኛ ስለሆነና ስርጭቱ በብዛት ስለሚዳረስ ባህር እንደሚናወጠው ሰዎችን ስለሚያናውጠው ፈተና ሲያወሩ ማንኛችሁ ነው የሰማው?" አለ። ሰዎችም ዝም አሉ። ሑዘይፋህ ቢን የማንም ረዲየሏሁ ዐንሁ "እኔ ሰምቻለሁ።" አለ። ዑመርም ረዲየሏሁ ዐንሁ ተደሰተ። ለርሱም "አላህ አባትህ ምን አይነት ልጅ እንዲወልድ ነው ያደረገልን! እስኪ ንገረን።" አለው። ሐዘይፋም እንዲህ አለ "ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "የተኛ ሰው ጎን ላይ የሰሌን ምንጣፍ እንደሚለጠፈው ፈተናም በሰው ቀልብ ላይ ትለጠፋለችም ግልፅ ትሆናለችም። ፈተናዋ በቀልብ ላይ ከመለጠፏ የተነሳም ቀልቡ ላይ ምልክት ታወጣበታለች። ይህቺ ፈተናም በተደጋጋሚ ተመላልሳ ትከሰታለች። ይህቺ ፈተና የገባችበት፣ የወደዳት፣ መጠጥ ወደ ሰውነት ውስጥ እንደምትቀላቀለው ከቀልቡ ጋር የተቀላቀለችበት ማንኛውም ቀልብ በቀልቡ ላይ ጥቁር ጠብታ ታርፋለች። ይህቺን ፈተና ያልተቀበለ ማንኛውም ቀልብ በቀልቡ ላይ ነጭ ጠብታ ታርፋለች። በዚህም ቀልቦች ሁለት አይነት ይሆናሉ። አንደኛው: በኢማን ላይ ያለው ጥንካሬ ከፍተኛ ስለሆነ፣ ከጉድለት የፀዳ ስለሆነ ፈተናዋ ያልተለጠፈችበትና ምልክት ያላሳረፈችበት ነጭ ቀልብ ነው። የርሱ ቀልብ ምሳሌም ምንም ነገር እንደማይይዝ ለስላሳ አልማዝ ነው። አላህን እስኪገናኝ ድረስም ምንም ነገር አይጎዳውም። ሌላኛው ቀልብ ደግሞ በፈተናው ሰበብ ቀለሙ ወደ ጥቁርነት የተለወጠና ውሃ እንደማይገባበት የተገለበጠ ጆክ የመሰለ ቀልብ ነው። ልክ እንደዚሁ ይህ የጠቆረ ቀልብ መልካምና ጥበብ የማይቀርበው፤ እንዲሁም የወደደውና ለስሜቱ የተመቸው ካልሆነ በቀር መልካሙን መልካም የማይልና መጥፎን የማያወግዝ ቀልብ ነው።" ሑዘይፋም ለዑመር እንዲህ አለው: "ይህ ፈተና አንተ በህይወት እያለህ አይከሰትም። በአንተና በዚህች ፈተና መካከል ሊሰበር የቀረበ የተዘጋ በር አለ።" ዑመርም "ይሰበራልን? ቢከፈትስ ተመልሶ ሊዘጋ ይችላልን?" አለ። ሑዘይፋም "በፍፁም! ይልቁንም ይሰበራል። ይህ በርም የሆነ ሰው መገደሉ ወይም መሞቱ ነው።" አለ። ሑዘይፋ እንዲህም አለ "አሁን ያወራሁት የተረጋገጠ እውነተኛ ወሬ ነው። የፀሃፊዎች ዘገባም የአንድ ሰው የምርምር ሀሳብ ውጤትም አይደለም። ይልቁንም የነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሐዲሥ ነው።"
ከአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «አንዲት ሚስኪን ሴትዮ ሁለት ሴት ልጆቿን ተሸክማ እኔ ዘንድ መጣች። ሶስት ቴምሮችን ሰጠኃት። ለእያንዳንዳቸው አንድ አንድ ሰጠቻቸው። የቀረችውንም ተምር ራሷ ልትበላው ወደ አፏ ስታነሳ ሁለቱ ልጆቿም ጎመጁ ልትበላው ፈልጋ የነበረችውንም ተምር ለሁለት ሰነጠቀችና አካፈለቻቸው። ስራዋ እጅግ አስደንቆኝ ያደረገችውን ለአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) አወሳሁላቸው። እርሳቸውም "አላህ ለርሷ በዚህ ስራዋ ወይ ጀነትን ግድ አድርጎላታል፤ ወይም በዚህ ስራዋ ከእሳት ነፃ አውጥቷታል።" አሉ።»
ሙስሊም ዘግበውታል።የአማኞች እናት ዓኢሻ (አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና) እንዳወሳችው: አንድ ሚስኪን ሴት ሁለት ሴት ልጆቿን ተሸክማ ዓኢሻን ለመነቻት። ዓኢሻም ሶስት ቴምሮችን ሰጠቻት። ለእያንዳንዷ ልጆቿ አንድ አንድ ቴምር ሰጠችና አንዷን ቴምር ደግሞ ልትበላት ወደ አፏ አስጠጋች። ነገር ግን ልትበላት የፈለገቻትን አንዷን ቴምር ሁለቱ ልጆቿ መፈለጋቸውን ተረዳችና ያንኑም ቴምር ለሁለት ከፍላ አከፋፈለቻቸው። የሴትዬዋ ጉዳይም ዓኢሻን (አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና) ስለደነቃት ሴትዬዋ የሰራችውን ሁሉ ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነገረቻቸው። እርሳቸውም እንዲህ አሏት: "አላህ በዚህች ተምር ምክንያት ወይ ጀነትን ግድ አድርጎላታል፤ ወይም ደሞ በዚህች ተምር ምክንያት ከእሳት ነፃ አድርጓታል።
ከአቡ ሁረይራ ረዲየላሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፡ "አንዳችሁ ወደ መቀመጫ ስፍራ የደረሰ ጊዜ ሰላምታን ያቅርብ፤ ከመቀመጫ ስፍራ መነሳት የፈለገም ጊዜ ሰላምታን ያቅርብ። መጀመሪያ ያቀረበው ሰላምታ መጨረሻ ላይ ከሚያቀርበው ሰላምታ የበለጠ አይደለም።"
አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ አሕመድ ዘግበውታል።ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰዎች ወደ ተቀማመጡበት ስፍራ የመጣ ሰው ሰላምታ እንዲያቀርብና መነሳትም የፈለገ ጊዜ የተቀማመጡትን ሰዎች በድጋሚ ሰላምታ እንዲያቀርብላቸው ጠቆሙ። በሚመጣበት ወቅት (ሲቀላቀላቸው) ያቀረበው የመጀመሪያው ሰላምታ በሚለያይበት ወቅት (ሲሰናበታቸው) ከሚያቀርበው የመጨረሻ ሰላምታ የበለጠ የሚያደርገው ነገር እንደሌለ ተናገሩ።
ከሙስዐብ ቢን ሰዕድ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ሰዕድ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከሌሎች ሰዎች የበለጠ ደረጃ እንዳለው ተሰማው። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉት: "የምትረዱትና የምትቀለቡት በደካሞቻችሁ ሰበብ አይደለምን?"
ቡኻሪ ዘግበውታል።ሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - ራሱን በጀግንነትና በመሳሰሉት ምክንያት ከርሱ በታች ካሉ ደካማ ሰዎች የበለጠ አድርጎ አሰበ። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "በደካሞቻችሁ፣ በነርሱ ዱዓ፣ ሶላትና ኢኽላስ ካልሆነ በቀር ትረዳላችሁን? ትቀለባላችሁን?" አሉ። አብዛኛው ጊዜ ደካማዎች ዱዓቸውን እጅግ ለአላህ አጥርተው፣ አምልኳቸውንም እጅግ ተመስጠው ነው የሚፈፅሙት። ይህም ቀልባቸው በዱንያ ጌጣጌጥ ከመንጠልጠል የፀዳ ስለሆነ ነው።
ከሑዘይፋ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ማዕድ ለመጋራት የተገኘን ጊዜ የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እጃቸውን ወደ ማዕዱ ከመስደዳቸውና (ከመጀመራቸው) በፊት እኛ እጃችንን አንሰድም ነበር። አንድ ቀን ከርሳቸው ጋር ማዕድ ለመጋራት ተገኘን። (ከፍጥነቷ የተነሳ) ልክ እየተገፈተረች በሚመስል መልኩ የሆነች አንዲት ልጅ መጣችና እጇን ወደ ማዕዱ ሰደደች። የአላህ መልክተኛም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እጇን ያዟት። ቀጥሎም (ከፍጥነቱ የተነሳ) ልክ እየተገፈተረ በሚመስል መልኩ አንድ የገጠር ሰውዬ መጣና እጁን ወደ ማዕዱ ሰደደ። የአላህ መልክተኛም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እሱንም እጁን ያዙትና እንዲህ አሉ: "ሸይጧን የአላህ ስም እንዳይወሳበት በማድረግ ምግቡን ለራሱ የተመቸ ያደርገዋል። እርሱም ይህቺን ሴትዮ ምግቡን ለራሱ ለማስመቸት ይዞ መጣ። እጇንም ያዝኳት። ይህንንም ሰውዬ ምግቡን ለራሱ ለማስመቸት ይዞ መጣ። እጁንም ያዝኩት። ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! የሸይጧንን እጅ ከሴትዮዋ እጅ ጋር ይዤዋለሁ።"»
ሙስሊም ዘግበውታል።ሑዘይፋ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳወሱት: ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ማዕድ ለመጋራት በተገኙ ጊዜ የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እጃቸውን ወደ ማዕዱ ከመስደዳቸውና ከመጀመራቸው በፊት እነርሱ እጃጀውን አይሰዱም ነበር። አንድ ቀን ከርሳቸው ጋር ማዕድ ለመጋራት ተገኘን። ከፍጥነቷ የተነሳ አመጣጧ ልክ እየተገፈተረች በሚመስል መልኩ የሆነች አንዲት ሴትዮ መጣችና እጇን ወደ ማዕዱ ሰደደች። የአላህ መልክተኛም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እጇን ያዟት። ቀጥሎም ከፍጥነቱ የተነሳ አመጣጡ ልክ እየተገፈተረ በሚመስል መልኩ የሆነ አንድ የገጠር ሰውዬ መጣና እጁን ወደ ማዕዱ ሰደደ። የአላህ መልክተኛም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ምግቡን ከመንካቱ በፊት እጁን ያዙትና እንዲህ አሉ: "ሰውዬው የአላህ ስም ሳይወሳበት ምግቡን የጀመረ ጊዜ ሸይጧን ምግቡን ለመመገብ ይመቻቻል። እርሱም ይህቺን ሴትዮ ምግቡን ለራሱ ለማስመቸት ይዟት መጣ። እጇንም ያዝኳት። ይህንንም ሰውዬ ምግቡን ለራሱ ለማስመቸት ይዞት መጣ። እጁንም ያዝኩት። ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ! የሸይጧንን እጅ ከሴትዮዋ እጅ ጋር በእጄ ነው።" ካሉ በኋላ የአላህን ስም ካወሱ በኋላ ተመገቡ።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "ዱንያ ለአማኞች እስር ቤት ለከሃዲዎች ጀነት ናት።"»
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - አማኝ የሆነ ሰው በዱንያ ትእዛዛትን በመፈፀምና ክልከላን በመራቅ በኩል ሸሪዓዊ በሆኑ ሃላፊነቶች ስለታሰረ የዱንያ ህይወት ለአማኝ እስር ቤት እንደሆነች እና ከዚህም ሲሞት አላህ ለርሱ ወዳዘጋጀለት ዘውታሪ ፀጋ ተሸጋግሮ እንደሚያርፍ ተናገሩ። ከሃዲ የሆነ ሰው ደግሞ ነፍሱ የፈለገችውን ሁሉና ዝንባሌው የመራውን ሁሉ ስለሚሰራ ዱንያ ለከሃዲ ጀነት መሆኗንና ሲሞትም አላህ የትንሳኤ ቀን ወዳዘጋጀለት ዘውታሪ ቅጣት ይሸጋገራል ብለው ተናገሩ።
ከሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህን መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጠየቅኳቸውና ሰጡኝ። ድጋሚ ጠየቅኳቸውና ሰጡኝ። ከዚያም እንዲህ አሉኝ: "ሐኪም ሆይ! ይህ ገንዘብ ለምለምና ጣፋጭ ነው። ይህንን ገንዘብ ነፍሱ እንደተከበረች (ሳይለምን) የወሰደው ሰው ለርሱ ይባረክለታል። ነፍሱን (ለልመና) በማውጣት የወሰደው ሰው ለርሱ አይባረክለትም። እርሱም እየበላ እንደማይጠግብ ሰው ምሳሌ ነው። ከላይ ያለች እጅ ከታች ካለች እጅ የተሻለች ናት።" ሐኪምም እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በእውነት በላከዎ ጌታ እምላለሁ! ዱንያን እስከምለያይ ድረስ ከዚህ በኋላ ማንንም አልለምንም። አልኩኝ።"» አቡ በክር ሐኪምን ስጦታ ሊሰጠው ይጠራው ነበር። አንዳችም ከርሱ አልቀበልም ብሎ እምቢ አለ። ከዚያም ዑመር ሊሰጠው ጠራው። ከርሱ ከመቀበልም እምቢ አለ። ዑመርም እንዲህ አለ: "እናንተ ሙስሊሞች ሆይ! እኔ ለሐኪም ከምርኮ ገንዘብ አላህ ድርሻው ያደረገለትን ሐቁን አቀረብኩለት። እርሱ ግን እምቢ አለ።" ሐኪም እስኪሞት ድረስ ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከተቀበለ በኋላ የአንድንም ሰው ገንዘብ በመውሰድ አላጎደለም ነበር።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- ነቢዩን - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - የዱንያ መጣቀሚያ የምትሆንን ጠየቀና ሰጡት። ድጋሚ ጠየቃቸውና ሰጡት። ከዚያም ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉት: "ሐኪም ሆይ! ይህ ገንዘብ የሚጓጓለትና የሚከጀል ነው። ይህንን ገንዘብ ሳይለምን ነፍሱ እጅግ ሳትጓጓና ችክ ሳይል ያገኘው ሰው ለርሱ ይባረክለታል። ነፍሱን ለሰዎች በማቅረብና በመከጀል ያገኘው ሰው ለርሱ አይባረክለትም። እርሱም እየበላ እንደማይጠግብ ሰው ምሳሌ ነው። ከላይ ያለች ሰጪ እጅ ከታች ካለች ከምትለምን እጅ አላህ ዘንድ የተሻለች ናት።" ሐኪምም እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በእውነት በላከዎ ጌታ እምላለሁ! ዱንያን እስከምለያይ ድረስ (አሁን ከሰጡኝ) ከርሶ ገንዘብ በኋላ የማንንም ገንዘብ ለምኜ አላጎድልም።" አልኩኝ። የአላህ መልክተኛ ምትክ አቡ በክር - አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና - ሐኪምን ስጦታ ሊሰጠው ይጠራው ነበር። አንዳችም ከርሱ አልቀበልም ብሎ እምቢ አለ። ከዚያም የአማኞች መሪ ዑመርም - አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና - ሊሰጠው ጠራው። ከርሱ ከመቀበልም እምቢ አለ። ዑመርም እንዲህ አለ: "እናንተ ሙስሊሞች ሆይ! እኔ ለሐኪም ከከሃዲያን ጋር ምንም ጦርነትና ጂሃድ ሳይደረግ ከተሰበሰበ ከምርኮ ገንዘብ አላህ ድርሻው ያደረገለትን ሐቁን አቀረብኩለት። እርሱ ግን እምቢ አለ።" ሐኪም እስኪሞት ድረስም ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከተቀበለ በኋላ የአንድንም ሰው ገንዘብ በመውሰድ አላጎደለም ነበር።