Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way






























Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
አንድ የገጠር ነዋሪ የሆነ ሰውዬ የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሚናገረውን ውዳሴ እንዲያስተምሩት ጠየቃቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ እንዲህ አሉት: "እንዲህ በል! "ላኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ" በተውሒድ የምስክር ቃል ጀመሩ። (ትርጉሙም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ብቸኛና አጋር የሌለው ነው።) "አሏሁ አክበር ከቢራ" ማለትም "አላህ ከሁሉም ነገር የበለጠ እጅግ ታላቅ ነው።" ማለት ነው። "ወልሐምዱ ሊላሂ ከሢራ" ማለትም "ለአላህ በባህሪዎቹ፣ በድርጊቶቹ፣ በማይቆጠሩ ፀጋዎቹ ብዙ ምስጋና የተገባው ነው።" ማለት ነው። "ሱብሐነሏሂ ረቢል ዓለሚን" ማለትም "አላህ ከጉድለት የጠራ የፀዳ ነው።" ማለት ነው። "ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል ዐዚዚል ሐኪም" ማለትም "በአላህ እገዛና መግጠም ካልሆነ በቀር ከአንድ ሁኔታ ወደ ሌላ ሁኔታ መለወጥ የለም።" ማለት ነው። ሰውዬውም "እነዚህ ቃላት ጌታዬን ለማውሳትና ለማላቅ ነው። ለነፍሴ የማደርገው ዱዐስ?" ብሎ ጠየቃቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ "እንዲህ በል!" አሉት። "አልላሁመጝፊርሊ" (አላህ ሆይ! ማረኝ) ወንጀሎችን በመማርና በመሸሸግ "ወርሐምኒ" (እዘንልኝ) ሃይማኖታዊና ዱንያዊ ጥቅሞችን ለኔ በማድረስ እዘንልኝ። "ወህዲኒ" (ምራኝ!) ወደ ተሻለ ሁኔታና ቀጥተኛውን መንገድ ምራኝ። "ወርዙቅኒ" (ሲሳይን ለግሰኝ!) ሐላል ገንዘብን፣ ጤናን፣ ሁሉንም መልካምና ደህንነት ለግሰኝ።
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአላህ ውጪ ከመማል አስጠነቀቁ። አማኝ የሆነ ሰው ከአላህ በቀር በማንም አይምልምና። ከአላህ ውጪ የማለና ለምሳሌ በላት፣ በዑዛ የማለ ሰው (እነዚህ ሁለቱ ከእስልምና በፊት በድንቁርና ዘመን ይመለኩ የነበሩ ጣዖታት ናቸው።) ነፍሱን ለማዳን ከሽርክ ለመፅዳትና ለዛ መሀላው ማካካሻ እንዲሆነው አስከትሎ "ላኢላሃ ኢለሏህ" የማለት ግዴታ እንዳለበት ተናገሩ። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለባልደረባው "ና ቁማር እንጫወት" ያለ ሰው (ቁማር ማለት ሁለት ወይም ከዛ በላይ የሆኑ ሰዎች በመካከላቸው አሸናፊው የሚወስደው ገንዘብ መድበው ለመሸናነፍ መጫወት ነው። ከመካከላቸውም እያንዳንዳቸው ወይ ያተርፋል ወይ ይከፍላል።) የጠራበትን ወንጀል ለማካካስ አንዳች ነገር መመፅወቱ እንደሚወደድለት ተናገሩ።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጀነት ነዋሪዎች በጀነት ውስጥ እየተጣቀሙ ሳሉ አንድ ተጣሪ እንዲህ በማለት እንደሚጣራ አወሱ "ጀነት ውስጥ ለናንተ ጤና አላችሁ መቼም ትንሽ እንኳ ብትሆን ህመም አትታመሙም። ለናንተ ህያውነት አላችሁ፤ ትንሿ ሞት የሆነችውን እንቅልፍ እንኳ ቢሆን መቼም ጀነት ውስጥ አትሞቱም። ለናንተ ወጣትነት አላችሁ፤ መቼም ጀነት ውስጥ አታረጁም። ለናንተ ጀነት ውስጥ መጣቀም አላችሁ፤ መቼም ጀነት ውስጥ አታዝኑምም አትቸገሩምም። ይህም ይህ የአላህ ዐዘ ወጀል ንግግር ነው: {ይህች ጀነት ትሰሩት በነበራችሁት ተሰጣችኋት በማለት ይጠራሉ።} [አልአዕራፍ: 43]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጀነት ሰዎች ጀነት የገቡ ጊዜ አላህ ተባረከ ወተዓላ ለነርሱ እንዲህ እንደሚል ተናገሩ: እንድጨምርላችሁ የምትፈልጉት አንዳች ነገር አለን? ሁሉም የጀነት ሰዎችም እንዲህ ይላሉ: ፊታችንን አላበራኸውምን? ጀነት አስገብተህስ ከእሳት አላዳንከንምን? አላህም ግርዶሹን አስወግዶ ይገልጠዋል። የፊቱ ግርዶሽም ብርሃን ነው። ወደ ጌታቸው ዐዘ ወጀል ከመመልከት የበለጠ ተወዳጅ ነገርም አይሰጣቸውም።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በጀዚረተል ዐረብ ኢብሊስ ሰጋጅ አማኞች እርሱን ወደ ማምለክና ለጣዖት ወደ መስገድ ይመለሳሉ የሚለውን ተስፋ እንደቆረጠ፤ ነገር ግን በጭቅጭቅ፣ በፀብ፣ በጦርነት፣ በፈተናና በመሳሰሉት በመካከላቸው ለማጣላት ተስፋ ከማድረግ፣ ከመታገል፣ ከመልፋት፣ ከመስራትና ከመጣር አለተወገደም ብለው ተናገሩ።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለት አይነት ሰዎች የእሳት ባለቤቶች እንደሆኑና በሳቸው ዘመን እንዳላዩዋቸውና እንደሌሉ፤ በተቃራኒው ከርሳቸው ህልፈት በኋላ እንደሚመጡ ተናገሩ። የመጀመሪያው አይነት ሰዎች: ሰዎችን የሚመቱበት የከብት ጭራ የሚያክል አለንጋ ይዘው የሚዞሩ ሰዎች ናቸው። እነርሱም ሰዎችን ያለ አግባብ በመምታት የግፈኞች ተባባሪ የሆኑ ፖሊሶች ናቸው። ሁለተኛው አይነት ሰዎች ደግሞ: በተለምዶ የሴቶች ተፈጥሮ የሆነውን የጥብቅነትንና አይነ አፋርነትን ልብስ ያወለቁ ሴቶች ናቸው። በተጨባጭ ገላቸው ላይ ልብስ ያለ ቢሆንም በትክክለኛው ግን የተራቆቱ ናቸው። ምክንያቱም እነሱ ቆዳቸውን ግልፅ ለማውጣት ሰውነትን የሚያሳይ ቀጭን ልብስ ነውና የሚለብሱት፤ (ወይ) ውበታቸውን ለማጉላት የተወሰነ ሰውነታቸውን ሸፍነው የተወሰነውን የገለጡ ናቸውና በማለት እነዚህን ሴቶች ገለጿቸው። በአለባበሳቸውና በአረማመዳቸው የወንዶችን ቀልብ ወደነርሱ እንዲያዘነብል የሚያደርጉ፣ ትከሻዎቻቸውንም የሚያወዛውዙ፣ ሌሎችንም እነርሱ ወደ ወደቁበት ጥመት እንዲያዘነብሉ የሚያደርጉ ናቸው። ከነዚህ ሴቶች ባህሪ መካከልም: ጭንቅላታቸው ያዘነበለ የግመል ሻኛ ይመስላል። የፀጉራቸውን መጠን በማሰሪያና በመሳሰሉት በማሰር ያተልቋታል። በግመል ሻኛ የተመሳሰሉት ፀጉራቸውና ጉንጉናቸው ከጭንቅላታቸው በላይ ከፍ ስለሚልና የግመል ሻኛ እንደሚዘነበለው ፀጉራቸውን በሚጎነጎኑት ሳቢያ ወደአንድ ጎን እስኪዘነበል ድረስ ሰበር ስለሚል ነው። ይህን ባህሪ የተላበሱ ሴቶች እነርሱ ላይ ይህ ከባድ ዛቻ አለባቸው። እርሱም ጀነት ላይገቡ፣ ሽታዋንም ላያገኙ፣ ወደርሷም ላይቀርቡ ነው። የጀነት መዓዛ ከሩቅ ስፍራ ነው የሚሸተው።
ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወንድ ልጅ ወደ ሌላ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ መመልከቱን ወይም ሴት ልጅ ወደ ሌላ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ መመልከቷን ከለከሉ። ሀፍረተ ገላ ማለት: ግልፅ የሆነ ጊዜ የሚያሳፍር የሆነ አካል ሁሉ ነው። የወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ ከእምብርት እስከ ጉልበቱ ሲሆን፤ የሴት ልጅ ደግሞ ከባዕድ ወንዶች አንፃር ሁሉም ሰውነቷ ሀፍረተ ገላ ነው። ከሴቶችና ከዘመዶቿ አንፃር ደግሞ በተለምዶ ቤት ውስጥ ስሰራ ግልፅ የሚሆነውን ያክል ግልፅ ታደርጋለች። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወንድ ልጅ ተራቁቶ ከሌላው ወንድ ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ ወይም ለብቻቸው ከአንድ ብርድ ልብስ ስር መገለላቸውን ከለከሉ። ሴት ልጅም ተራቁታ ወደ ሴት ልጅ በአንድ ልብስ ውስጥ ወይም ለብቻቸው ከአንድ ብርድ ልብስ ስር መገለላቸውን ከለከሉ። ምክንያቱም ይህ አንዱ የሌላኛው ጓደኛውን ሀፍረተ ገላ ወደመንካት ያደርሰዋልና። መንካቱ ደግሞ እንደማየቱ ክልክል ነው። እንደውም ወደ ትልቅ ብክለት ስለሚያመራ መንካቱ ከማየትም በበለጠ ክልክል ነው።
አንድ ሰው ወደ ነቢዩየአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመምጣት እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ሁሉንም ዓይነት ወንጀሎችና ኃጢኣቶች ሰርቻለሁ፤ ትንሽም ሆነ ትልቅ ወንጀል ከመስራት አልተቆጠብኩም፤ ምህረት ይደረግልኝ ይሆን?" ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለሱ "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን ትመሰክር የለምን?" አሉት። ሶስት ጊዜ ደጋግመው ጠየቁት። እርሱም፦ "አዎን እመሰክራለሁ" በማለት መለሰላቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በሁለቱ የምስክር ቃላቶች ትሩፋትና ወንጀል የማስማር አቅማቸው እንደሚማር ነገሩት። ተውበት ያለፈውን ወንጀል ያብሳልና።
ዑለሞችን ለመወዳደርና ለመፎካከር፣ እኔ እንደናንተው ዓሊም ነኝ የሚለውን ለማሳየት ወይም ቂሎችንና ደካማ ግንዛቤ ያላቸውን ልትሟገቱና ልታናግሩ ወይም በመድረኮች ግንባር ቀደም ለመሆንና ከሌላው ቅድሚያ እንዲሰጠው በማለም ዕውቀት ከመፈለግ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አስጠነቀቁ። ይህን የፈፀመ ሰው፤ ለአላህ ብሎ ዕውቀት በመፈለግ ላይ እሱ ለይዩልኝና ያለ ኢኽላስ በመስራቱ እሳት ይገባዋል።