





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና: እርሳቸው ያነጉ ጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር "አልላሁመ ቢከ አስበሕና ወቢከ አምሰይና ወቢከ ነሕያ ወቢከ ነሙቱ ወኢለይከ ኑሹር" ትርጉሙም "አላህ ሆይ በአንተ አነጋን፣ በአንተም አመሸን፣ በአንተም ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን፣ መቀስቀስም ወደ አንተ ነው።" ያመሹ ጊዜ ደግሞ እንዲህ ይሉ ነበር "አልላሁመ ቢከ አምሰይና ወቢከ አስበሕና ወቢከ ነሕያ ወቢከ ነሙቱ ወኢለይከ ኑሹር" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! በአንተ አመሸሁ፣ በአንተም አነጋሁ፣ በአንተም ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን፣ መቀስቀስም ወደ አንተ ነው።" በሌላ ጊዜም እንዲህ ብለዋል "… ወኢለይከል መሲር" ትርጉሙም "… መመለሻም ወደ አንተ ነው።"
رواه أبو داود والترمذي والنسائي في الكبرى وابن ماجهነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በርሳቸው ላይ ንጋት የገባ ጊዜ (ይህም ጎህ ከመውጣቱ ጋር የቀኑ መጀመሪያ የሆነ ጊዜ ነው።) እንዲህ ይሉ ነበር: (አላህ ሆይ! በአንተ አነጋን) በጥበቃህ ተከልለን፣ በፀጋህ ተሸፍነን፣ አንተን በማውሳት ተጠምደን፣ በስምህ ታግዘን፣ በመግጠምህ ተከበን፣ በብልሃትህና በሀይልህ ተንቀሳቃሽ ሆነን አነጋን ማለት ነው። (በአንተ አመሸን፣ በአንተ ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን።) ይህ ማለት ምሽት ላይ ከማድረግ ጋር ቀደም ተብሎ እንደተብራራው እንዲህ ይላል: አላህ ሆይ ባንተ አምሽተናል፣ ህያው አድራጊ በሆነው ስምህ ህያው እንሆናለን። ህይወትን የሚነጥቅ በሚለው ስምህ እንሞታለን። (መቀስቀስም ወዳንተ ነው።) መቀስቀስ ከሞት በኋላ ነው፤ መለያየት ከመሰብሰብ በኋላ ነው። በሁሉም ወቅቶች ሁኔታችን በዚህ ሁኔታ ይቀጥላል። በተቀሩትም ሁኔታዎቼ ከአላህ አልላቀቅምም አልተወውምም። ከዐስር በኋላ ምሽት የገባ ጊዜም (አላህ ሆይ! በአንተ አመሸሁ፣ በአንተም አነጋሁ፣ በአንተም ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን፣ መመለስም ወደ አንተ ነው።) ይሉ ነበር። በዱንያም መመለሻዬ፣ በመጨረሻም መመለሻዬ ወደ አንተ ነው። ህያው የምታደርገኝም አንተው ነህ፤ የምትገድለኝም አንተው ነህ። ማለት ነው።
ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅግ አብዝተው ያደርጉት የነበረው ዱዓ 'አልላሁመ ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰነተን ወፊል አኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዓዛበን-ናር' የሚለውን ነበር።" (ትርጉሙም: ጌታችን አላህ ሆይ! በዱንያ መልካሙን ስጠን፤ በመጨረሻው ዓለምም መልካሙን ስጠን። ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።) ማለት ነው።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጠቅላይ የሆኑ ዱዓዎችን ማድረግ ያበዙ ነበር። ከነርሱም መካከል: "አልላሁመ ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰነተን ወፊል አኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዓዛበን-ናር" የሚለው ነበር።" (ትርጉሙም: ጌታችን አላህ ሆይ! በዱንያ መልካሙን ስጠን፤ በመጨረሻው አለምም መልካሙን ስጠን። ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።) ማለት ነው። ይህ ዱዓ ጣፋጭ፣ ሰፊና ሐላል የሆነ ሲሳይን፣ መልካም ሚስትን፣ የአይን ማረፊያ የሆነ ልጅን፣ እረፍትን፣ ጠቃሚ ዕውቀትን፣ መልካም ስራንና የመሳሰሉትን ተወዳጅና ፍቁድ የሆኑ ተፈላጊዎችን ባጠቃላይ የዱንያ መልካም ነገሮችን እንዲሁም በቀብር ውስጥ፣ በሒሳብ መቆሚያ ስፍራና በእሳት ውስጥ ከሚያጋጥም ቅጣቶች ሰላም መሆንን፣ የአላህን ውዴታ ማግኘት፣ ዘውታሪ ፀጋ መጎናፀፍን፣ አዛኝ ወደሆነው ጌታ መቅረብን የመሰሉ የመጨረሻው አለም መልካም ነገሮችንም የሚያጠቃልል ዱዓ ነው።
ከሸዳድ ቢን አውስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የምህረት አጠያየቅ (የኢስቲግፋር) አለቃ 'አልላሁመ አንተ ረቢ ላ ኢላሃ ኢላ አንተ፣ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱክ፣ ወአነ ዓላ ዐህዲከ ወወዕዲከ ማስተጦዕቱ፣ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማ ሶነዕቱ፣ አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፣ ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ ፈግፊር ሊ፣ ፈኢነሁ ላየግፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንተ።' ማለትህ ነው።'" እንዲህም ብለዋል "በርሷ አምኖ ቀን ላይ ያላትና በዛው ቀን ከማምሸቱ በፊት የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ባለቤቶች ነው። በርሷ አምኖ ምሽት ላይ ያላትና ከማንጋቱ በፊት የሞተ ሰውም እርሱ ከጀነት ባለቤቶች ነው።" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ፈጥረሀኛል እኔም ባሪያህ ነኝ፣ እኔ በቻልኩት መጠን በቃል ኪዳንህ ላይ እገኛለሁ፤ ከሰራሁት ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ፣ በኔ ላይ የዋልከውን ፀጋ አረጋግጣለሁ፣ ወንጀሌንም ላንተ አረጋግጣለሁና ማረኝ! እነሆ ካንተ በቀር ወንጀሎችን የሚምር የለምና።)
ቡኻሪ ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ምህረት የሚጠየቅበት የተለያዩ ቃላቶች እንዳሉና በላጩና ትልቁ አንድ ባሪያ እንዲህ ብሎ መጠየቁ እንደሆነ ተናገሩ: "አልላሁመ አንተ ረቢ ላ ኢላሃ ኢላ አንተ፣ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱክ፣ ወአነ ዓላ ዐህዲከ ወወዕዲከ ማስተጦዕቱ፣ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማ ሶነዕቱ፣ አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፣ ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ ፈግፊር ሊ፣ ፈኢነሁ ላየግፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንተ።" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ፈጥረህኛል እኔም ባሪያህ ነኝ፣ እኔ በቻልኩት መጠን በቃል ኪዳንህ ላይ እገኛለሁ፤ ከሰራሁት ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ፣ በኔ ላይ የዋልከውን ፀጋ አረጋግጣለሁ፣ ወንጀሌንም ላንተ አረጋግጣለሁና ማረኝ! እነሆ ካንተ በቀር ወንጀሎችን የሚምር የለምና።) በቅድሚያ ባሪያው የአላህን ብቸኝነት ያረጋግጣል። አላህ ፈጣሪው፣ ምንም አጋር ሳይኖረው የሚያመልከው መሆኑን፤ ጥራት ለተገባው አላህ የገባውን በርሱ የማመንና ለርሱ ታዛዥ የመሆንን ቃልኪዳን በአቅሙ ልክ እንደሚወጣ ያረጋግጣል። በአቅሙ ልክ ቃሉን እንደሚወጣ የሚያረጋግጠውም አንድ ባሪያ ምንም ያክል በአምልኮ ላይ ቢቆም አላህ ያዘዘውን ሁሉ መፈፀም ስለማይችል ነው። ለተዋለለት ፀጋ የሚገባውን ምስጋናም ማቅረብ አይችልም። ወደ አላህም ይጠጋል፣ በርሱም ይጠበቃል፣ ባሪያ ከሰራው ክፋት መጠበቂያው አላህ ነውና። አላህ ለርሱ የዋለለትን ፀጋም በታዛዥነት ለርሱ ያረጋግጣል፤ እውቅናንም ይሰጣል። ወደ ነፍሱ በመመለስም ወንጀሉና ኃጢአቱን ያረጋግጣል፤ ያምናልም። በዚህ መልኩ ወደ አላህ ከተቃረበ በኋላ ጌታው እንዲምረው፣ ወንጀሎቹን እንዲሸሽግለት፣ በይቅር ባይነቱ፣ በችሮታውና እዝነቱ ከወንጀሎቹ እንዲጠብቀውም ዱዓ ያደርጋል። ምክንያቱም ከአላህ በቀርም ወንጀሎችን የሚምር የለምና። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህቺ ዱዓ ከንጋትና ምሽት ውዳሴዎች መካከል መሆኗንና በቀኑ መጀመሪያ ፀሀይ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ ወደ መግቢያዋ ዘንበል እስክትል ድረስ ባለው ወቅት ላይ በእርግጠኝነት፣ መልዕክቷን በማሰብ አምኖባት ካለ በኃላ የሞተ ሰው ጀነት የሚገባ መሆኑን ተናገሩ። በምሽትም ወቅት እርሱም ፀሀይ ከገባችበት አንስቶ ጎህ እስኪወጣ ድረስ ያለ ሰውና ከመንጋቱም በፊት የሞተ ጀነት ይገባል።
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በደልን ተጠንቀቁ! በደል የትንሳኤ ቀን ድርብርብ ጨለማዎች ነውና። ስስትንም ተጠንቀቁ! ስስት ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷልና። ስስታምነት ደማቸውን እንዲያፈሱና ሐራም (ያልተፈቀደውን) እንደ ሐላል አድርገው እንዲቆጥሩ አነሳስቷቸዋልና።"
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከበደል አስጠነቀቁ። ከበደል መካከልም: ሰዎችን መበደል፣ ነፍስን መበደል፣ በአላህ ሐቅ ላይ በደል መፈፀም ይጠቀሳሉ። በደል ማለት ሁሉንም የሐቅ ባለቤቶችን ሐቃቸውን ከመስጠት መተው ነው። በደል የትንሳኤ ቀን በባለቤቱ ላይ ከሚያጋጥመው መከራዎችና አስፈሪ ክስተቶች አኳያ ጨለማ ነው። ከስስትም ከለከሉ። እርሱም ከመጓጓት (መንሰፍሰፍ) ጋር እጅግ ስስታምነት ነው። ከስስታምነት መካከል: ገንዘባዊ ሐቆችን ከመወጣት ቸል ማለትና ለዱንያ እጅግ መንገብገብም ይጠቀሳል። ይህኛው የበደል ክፍል ማለትም ስስታምነት ከእኛ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷቸዋል። ይህም ከፊሉ ከፊሉን እንዲገድሉና አላህ እርም ያደረጋቸውን ክልክሎች የተፈቀዱ እንዲያደርጉ አነሳስቷቸዋል።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:- "አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው ምርጡ?' ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም 'ምግብ መመገብህ፣ ሰላምታን ባወቅከውም ባላወቅከውም ሰው ላይ ማቅረብህ ነው።' ብለው መለሱለት።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው በላጩ? ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም ሁለት ነገሮችን ጠቀሱ። የመጀመሪያው: ድሃዎችን ማብላትን ማብዛት ነው። እዚህ ውስጥም ሶደቃ፣ ስጦታ፣ ግብዣ፣ የሰርግ ድግስ ይገባሉ። የማብላቱ በላጭነትም በረሃብና ኑሮ በተወደደበት ወቅት የጠነከረ ይሆናል። ሁለተኛው: አወቅከውም አላወቅከውም በሁሉም ሙስሊም ላይ ሰላምታን ማቅረብ ነው።
ከዓሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉኝ: "'አሏሁመ‐ህዲኒ ወሰዲድኒ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ ምራኝ፣ አስተካክለኝም።) በልና መመራትን ከአሏህ ስትጠይቅ መንገድን መመራትን አስታውስ። መስተካከልን ስትጠይቅ ደሞ የቀስት ኢላማውን የማግኘት ያህል መገጠምን አስታውስ።"»
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዓሊይ ቢን አቢ ጣሊብን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - አላህን እንዲህ ብሎ እንዲጠይቅና እንዲለምን አዘዙት "አላህ ሆይ! ምራኝ" አቅናኝ፣ ጠቁመኝ "አስተካክለኝ" ግጠመኝ፣ በሁሉም ጉዳዮቼ የተቃና አድርገኝ። ሁዳ (መመራት) ማለት እውነትን በዝርዝርም ሆነ በጥቅሉ ማወቅና እውነትን በግልፅም ሆነ በውስጥ ለመከተል መገጠም ማለት ነው። ሰዳድ "መስተካከል" ማለት: በሁሉም ነገሮች በእውነት ላይ ትክክል በሚሆነው ቀጥ ማለትና መገጠም ማለት ነው። "ሰዳድ" ማለት በንግግርም፣ በተግባርም ሆነ በእምነት ቀጥተኛ የሆነ መንገድ ማለት ነው። ሀሳባዊ ነገር በህዋሳዊ ነገሮች ይብራራሉና አንተ ይህን ዱዓ እያደረግክ "መመራትን ስትማፀን የመንገድ መመራትን" አስታውስ፤ ጉዞ የወጣ ሰው መንገድ መመራት እንደሚጠይቀው መመራት እየጠየቅክ እንደሆነ ቀልብህ ላይ አስቀምጥ። መንገድ የወጣ ሰው ከተመራው መንገድ ከመጥፋት ለመዳን ወደቀኝ ወይም ወደግራ ዘንበል አይልም። ቀጥ ብሎ በመሄዱም ሰላምን ያገኛልም ወደ አላማውም በፍጥነት ይደርሳል። "መስተካከልን ስትጠይቅ ደሞ ቀስት ኢላማውን የማግኘትን ያህል መገጠምን አስታውስ።" አንተ ቀስት ስታነጣጥር በፍጥነት መድረሱንና ኢላማውን ማግኘቱ ላይ ነው የምታተኩረው። ቀስት ወርዋሪ ወደ አንድ ኢላማ ባነጣጠረ ወቅት ቀስቱን ወደ ኢላማው አስተካክሎ ያነጣጥራል። ልክ እንደዚሁ ያሰብከውን መገጠም እንደቀስቱ የተስተካከለ እንዲሆን አድርገህ ነው አላህን የምትጠይቀው። በጥያቄህም የፈለግከው የመመራትን ጥግና የመገጠምን ድካ ይሆናል ማለት ነው። በዚህ ዱዓ ስትማፀን የምትፈልገውን ጉዳይ ቀስት ስትወረውር እንደምታልመው ትክክለኝነት እንዲሆን አላህን መገጠም ስትጠይቅ በቀልብህ ይህን ሀሳብ አስቀምጥ።
ከዓሊ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ፋጢማ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ በወፍጮ ምክንያት እጇ ላይ ስለሚያጋጥማት ጉዳይ ለማማከር መጣች። እርሳቸው ዘንድ ባሪያ እንደመጣም ወሬ ደረሳት። ቤት ስትሄድም አላገኘቻቸውምና ይህንን ለዓኢሻ አወሳችላት። እርሳቸው ሲመጡም ዓኢሻ ለርሳቸው ነገረቻቸው። ዓሊይ እንዲህ አለ: «መኝታችን ላይ ሆነን ሳለ መጡ። ለመነሳት ስንዘጋጅም "ባላችሁበት ሁኑ" አሉንና መጥተው የእግራቸው ቅዝቃዜን ሆዴ እስኪሰማው ድረስ በኔና በርሷ መካከል መጥተው ተቀመጡና እንዲህ አሉ: "ከጠየቃችሁት የተሻለን ነገር አልጠቁማችሁምን? መኝታ ስፍራችሁን የያዛችሁ ጊዜ ወይም ወደ መኝታችሁ ስፍራ የተጠጋችሁ ጊዜ ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'ሱብሓነላህ' ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'አልሐምዱሊላህ' ሰላሳ አራት ጊዜ ደግሞ 'አላሁ አክበር' በሉ። ይህም ለናንተ ከአገልጋይ የተሻለ ነው።"»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሴት ልጅ የሆነችው ፋጢማ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና በወፍጮ ስትፈጭ እጇ ላይ ስለሚደርስባት ምልክት ለነቢዩ ስሞታ አቀረበች። ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምርኮኛ የመጣ ጊዜ የቤት ስራን የሚተካላት ከነዚህ ምርኮኞች መካከል አንድ ሰራተኛ እንዲሰጧት ለመጠየቅም ወደርሳቸው ሄደች። ነገር ግን ቤት ውስጥ አላገኘቻቸውም። ዓኢሻን (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና ስለነበር ያገኘችው ለርሷ ነገረቻት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቤታቸው ሲመጡም ፋጢማ ወደርሳቸው ሰራተኛን ልትጠይቃቸው መጥታ እንደነበር ነገረቻቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ፋጢማና ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ዘንድ ፍራሻቸው ላይ ለእንቅልፍ እየተዘጋጁ ሳለ ቤታቸው መጡ። ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ሆዱ ላይ የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የእግር ቅዝቃዜ እስኪሰማው ድረስ በመካከላቸው ተቀመጡ። እንዲህም አሏቸው: ሰራተኛን እንድሰጣችሁ ከጠየቃችሁኝ ይልቅ የተሻለውን ነገር አላስተምራችሁምን? እነርሱም: እንዴታ አሏቸው። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: ምሽት ላይ የእንቅልፋችሁን ስፍራ የያዛችሁ ጊዜ ሰላሳ አራት ጊዜ 'አላሁ አክበር' በሉ። ሰላሳ ሶስት ጊዜ 'ሱብሓነላህ' በሉ። ሰላሳ ሶስት ጊዜም 'አልሐምዱሊላህ' በሉ። እነዚህ ዚክሮች ለናንተ ከሰራተኛም የተሻሉ ናቸው።
ከዐብደላህ ቢን ኹበይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "በዝናባማና በድቅድቅ ጨለማ ምሽት የአላህ መልክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኛን እንዲያሰግዱን ፈልገን ወጣን። አገኘኋቸውና 'በል!' አሉኝ። ምንም አላልኩኝም። ቀጥለውም 'በል!' አሉኝ። ምንም አላልኩኝም። አሁንም 'በል!' አሉኝ። እኔም ምን ልበል? አልኳቸው። እርሳቸውም 'ሱረቱል ኢኽላስ እና ሁለቱን መጠበቂያዎች (ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱን-ናስን) ስታመሽና ስታነጋ ሶስት ጊዜ ካልክ ለሁሉም ነገር ይበቁሃል።' አሉኝ።"
አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።ታላቁ ሶሐባ ዐብደላህ ቢን ኹበይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና በርካታ ዝናብ በሚዘንብበትና ድቅድቅ ጨለማ በነበረበት ምሽት የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲያሰግዷቸው ፈልገው እንደወጡና እንዳገኟቸው ተናገረ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለርሱ "በል!" ማለትም አንብብ! አሉት። እርሱም ምንም አላነበበም። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ንግግራቸውን ሲደጋግሙለት ዐብደላህም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ልቅራ?" አላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ሱረቱል ኢኽላስን እና ሁለቱን መጠበቂያዎች ሱረቱል ፈለቅ እና ሱረቱ አን-ናስን በምሽት ወቅትና በንጋት ወቅት ሶስት ጊዜ ቅራ! ከሁሉም ክፋትና ጉዳት ይጠብቅሃል።" አሉት።
ከአባን ቢን ዑሥማን እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዑሥማን ቢን ዐፋን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ሲሉ ሰማሁዋቸው: "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰማሁዋቸው: ‹ሶስት ጊዜ 'ቢስሚላሂለዚ ላየዱሩ መዐስሚሂ ሸይኡን ፊልአርዲ ወላፊስሰማእ ወሁወስ'ሰሚዑል ዐሊም' (ትርጉሙም: በዚያ ከስሙ ጋር በምድርም ይሁን በሰማይ ምንም ነገር የማይጎዳ በሆነው እንዲሁም ሰሚና አዋቂ በሆነው አላህ ስም።) ያለ ሰው እስኪነጋ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም። በሚያነጋ ጊዜም ሶስት ጊዜ ያላት ሰው እስኪያመሽ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም።› አባን ቢን ዑሥማንን የግማሽ አካል ሽባነት አገኘውና ከርሱ ይሄን ሐዲሥ የሰማው ሰውዬም አተኩሮ ተመለከተው። አባንም ለርሱ እንዲህ አለው: እንደዚ አተኩረህ የምታየኝ ምን ሆነው ነህ? በአላህ እምላለሁ! በዑሥማን ላይ ምንም አልዋሸሁም! ዑሥማንም በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ምንም አልዋሸም። ነገር ግን ዛሬ የደረሰብኝ ነገር የደረሰው ተቆጥቼ ስለነበር ይህን ዚክር ማለት ረስቼ ስለነበር ነው።"»
አቡዳወድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁሉ ቀን ጎህ ከቀደደ በኋላ ንጋት ላይና ፀሀይ ከመግባቷ በፊት ደግሞ ሁሌ ምሽት ላይ ሶስት ጊዜ ይህንን ዚክር ያለ ሰው:(ቢስሚላሂ) በአላህ ስም ከሁሉም ጎጂ ነገር እጠበቃለሁም እታገዛለሁም። (ያ ስሙን ከማውሳት ጋር) ምንም ያህል ቢተልቅ (አንዳችም የማይጎዳው) (በምድርም ውስጥ) ከምድር የሚወጡ በሆኑ መከራዎችም (በሰማይ ውስጥም) ከሰማይ የሚወርዱ በሆኑ መከራዎችም (እርሱ ንግግራችንን ሰሚ) ሁኔታችንንም (አዋቂ ነው።) የምንጎዳ አይደለንም። በሚያመሽ ወቅት የተናገራት እስኪያነጋ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም። በሚያነጋ ወቅት የተናገራት ደግሞ እስኪያመሽ ድረስ ድንገተኛ መከራ አያገኘውም። ሐዲሡን ያወራው አባን ቢን ዑስማንን በወቅቱ የሰውነቱ ግማሽ ሽባ የመሆን በሽታ አጋጥሞት ስለነበር ከርሱ ይሄን ሐዲሥ የሰማው ሰውዬም በግርምት አይን ተመለከተው። አባንም ለሰውዬው እንዲህ አለው "እንደዚህ የምትመለከተኝ ምን ሆነህ ነው? በአላህ እምላለሁ! በዑሥማንም ላይ አልዋሸሁም። ዑሥማንም በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ አልዋሸም። ነገር ግን ይህ በሽታ ባጋጠመኝ እለት አላህ እንድለው አልወሰነልኝም ነበር። የሚያስቆጣ ነገር አጋጠመኝና እነዚህን የተጠቀሱ ቃላቶች ማለትን ዘነጋሁኝ።"