





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ከሑሰይን ቢን ዐሊይ ቢን አቢጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ስስታም ማለት እርሱ ዘንድ ተወስቼ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ነው።"»
رواه الترمذي والنسائي في الكبرى وأحمدነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የርሳቸውን ስም ወይም ቅጥያ ስም ወይም ባህሪያቸውን በሚሰማ ወቅት እርሳቸው ላይ ሶላት ማውረድ የተወን ሰው አስጠነቀቁ። እንዲህም አሉ: ስስታምነቱ የተሟላ ስስታም ማለት እርሱ ዘንድ ተወስቼ ሶለዋት ያላወረደብኝ ነው። ይህም የሆነው ከሚከተሉት ጉዳዮች አንፃር ነው: የመጀመሪያው: ሶለዋት በማውረዱ ምክንያት ትንሽም ይሁን ብዙ የማይከስርበት፣ ገንዘብ የማያወጣበት፣ ጉልበቱን የማያፈስበት በሆነ ነገር ላይ መሰሰት ስለሆነ፤ ሁለተኛው: በአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ሶለዋት ባለማውረዱ በርሳቸው ላይ ሶላት የማውረድን ምንዳ በነፍሱ ላይ ስለሳሳና ስለነፈጋት ነው። በርሳቸው ላይ ሶለዋት ባለማውረዱ ትእዛዝን ለመተግበርና ምንዳን ለማግኘት ሊፈፅመው ግዴታ የሆነበትን ሐቅ ከመፈፀም ታቅቧልም ሰስቷልም። ሶስተኛው: በርሳቸው ላይ ሶለዋት ማውረድ የተወሰነውን የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሐቅ መወጣት ነው። ያስተማሩን፣ ያቀኑን፣ ወደ አላህ ተባረከ ወተዓላ የጠሩን፣ ይህንን ወሕይና ሸሪዓ ይዘው የመጡልን እርሳቸው ናቸው። ከአላህ ተባረከ ወተዓላ በኋላ የመመራታችን ምክንያት እርሳቸው ናቸው። በርሳቸው ላይ ሶለዋት ያላወረደ ሰው በርግጥም በነፍሱ ላይም ስስታም ሆኗል። ለነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ካላቸው ሐቆች መካከል በትንሹ ሐቅ እንኳ ስስታም ሆኗል።
ሰህል ቢን ሙዓዝ ቢን አነስ ከአባቱ እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ምግብ በልቶ ‹አልሐምዱ ሊላሂለዚ አጥዐመኒ ሀዛ ወረዘቀኒሂ ሚን ገይሪ ሐውሊን ሚንኒ ወላቁውዋህ› ያለ ሰው ያሳለፈው ወንጀል ለርሱ ይማርለታል።"» ትርጉሙም "ያለኔ ኃይልና ብልሃት ይህንን ላበላኝና ለለገሰኝ አላህ ምስጋና የተገባው ነው።" ማለት ነው።
አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ምግብ የበላን ሰው አላህን እንዲያመሰግንና ምግብን በማምጣቱም በመብላቱም በአላህና በእገዛው ካልሆነ በቀር ለኔ ምንም አቅም የለኝም እንዲልም አነሳሱ። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን የተናገረ ሰው ላሳለፈው ትናንሽ ወንጀሎቹ የአላህን ምህረት ለማግኘት የተገባ እንደሆነ አበሰሩ።
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ አይመለስም (ተቀባይነቱ ጥርጥር የለውም)።"»
አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአዛንና ኢቃም መካከል የሚባል ዱዓ ያለውን ደረጃና እርሱ ለተቀባይነት የተገባና የማይመለስ ስለሆነ በዚህ ወቅት አላህን እንድንማፀን ገለፁ።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ይሉ ነበር: "አልላሁመ አስሊሕ ሊ ዲኒለዚ ሁወ ዒስመቱ አምሪ ወአስሊሕ ሊ ዱንያየለቲ ፊሃ መዓሺ፣ ወአስሊሕ ሊ አኺረቲለቲ ፊሃ መዓዲ፣ ወጅዐሊል ሐያተ ዚያደተን ሊ ፊ ኩሊ ኸይር፣ ወጅዐሊል መውተ ራሐተን ሊ ሚን ኩሊ ሸር"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! የነገሮቼ መጠበቂያ የሆነውን ሃይማኖቴን አስተካክልልኝ። በውስጧ ኑሮዬ የሆነውን ዱንያዬንም አስተካክልልኝ። መመለሻዬ የሆነውን የመጨረሻውን አለምም አስተካክልልኝ። ህይወቴን ሁሉንም መልካም ነገር የምጨምርበት አድርገው። ሞቴንም ከሁሉም መጥፎ ነገር የማርፍበት አድርገው።" ማለት ነው።
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለመሙላት የተላኩለት የሆነውን የመልካም ስነምግባር መሰረቶችን የሰበሰበች ዱዓ አደረጉ። እነርሱም: የሃይማኖት፣ የዱንያና የመጨረሻው አለም መስተካከል ናቸው። በነዚህ አጠር ባሉ ቃላቶች የነዚህን ሶስቱንም ያጠቃለለ ጥቅምን አከታትለው ለመኑ። በቅድሚያ በሃይማኖት መስተካከል ጀመሩ። የሁለቱም ሀገሮች ሁኔታ የሚስተካከሉት በርሱ ነውና። እንዲህ አሉ: (አላህ ሆይ! ሃይማኖቴን አስተካክለው።) በተሟላ መልኩ ስነስርዓቱን ጠብቄ እንድቆም ወፍቀኝ (አሳካልኝ)። (የነገሮቼ መጠበቂያ የሆነውን) የጉዳዮቼ ባጠቃላይ ጠባቂ የሆነው ሃይማኖቴ ከተበላሸ ጉዳዮቼ ባጠቃላይ ይበላሻል፤ ባዶዬን እቀራለሁ፣ እከስራለሁ። እንዲስተካከል የተፈለገው የሃይማኖት ጉዳይም ዱንያ ስትስተካከል ካልሆነ በቀር ስለማይስተካከል እንዲህ አሉ: (ዱንያዬን ለኔ አስተካክልልኝ) የሰውነት ጤና፣ ደህንነት፣ ሲሳይ፣ መልካም ሚስት፣ ጥሩ ዘር፣ ሐላል የሆነና አንተን ለማምለክ የሚያግዘኝን የሚያስፈልገኝን በመስጠት (ዱንያዬን ለኔ አስተካክልልኝ) ቀጥለው ዱንያቸው እንዲስተካከል የጠየቁበትን ምክንያት እንዲህ በማለት ጠየቁ: (በውስጧ ኑሮዬ የሆነውን) የኑሮዬና የህይወት ዘመኔ ስፍራ የሆነውን። (መመለሻዬ የሆነውን የመጨረሻውን አለም አስተካክልልኝ።) አንተን ለመገናኘት የምመለስበት የሆነውን ማለት ነው። መጨረሻ የሚያምረውም ስራን በማስተካከልና አላህ ባሪያውን ለአምልኮ፣ ለኢኽላስና ለመልካም ፍፃሜ በመግጠሙ ነው። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መጪው አለምን ከዱንያ በኋላ ያስከተሉት የመጀመሪያው አለም ለሁለተኛው አለም መስተካከል መዳረሻ ስለሆነ ነው። ዱኒያው አላህ በፈለገው መልኩ የተስተካከለለት ሰው መጪው አለምም ለርሱ ይስተካከልለታል በርሷም ውስጥ ይደሰታል። (ህይወቴን አድርግ) የእድሜዬ መርዘምን (በሁሉም በኩል መልካም ነገር የምጨምርበት) መልካም ስራን የማበዛበት (ሞቴን አድርገው) መፍጠኑን (ከሁሉም መጥፎ ነገር የማርፍበት) ሞትን ከፈተናዎች፣ ከመከራ፣ የወንጀልና የዝንጉነት ፈተና ላይ ከመውደቅ፣ ከዱንያ ችግርና ጭንቀት የምገላገልበትና እረፍትን የማገኝበት አድርገው።
ከአቡ ሙሳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እነዚህን ዱዓዎች ያደርጉ ነበር: "ረቢግፊርሊ ኸጢአቲ፣ ወጀህሊ፣ ወኢስራፊ ፊ አምሪ ኩሊህ፣ ወማ አንተ አዕለሙ ቢሂ ሚኒ፣ አላሁምመግፊርሊ ኸጧያየ፣ ወዓምዲ፣ ወጀህሊ፣ ወሀዝሊ ወኩሉ ዛሊከ ዒንዲ፤ አላሁመግፊርሊ ማ ቀደምቱ፣ ወማ አኸርቱ፣ ወማ አስረርቱ፣ ወማ አዕለንቱ፤ አንተል ሙቀዲሙ፣ ወአንተል ሙአኺሩ፣ ወአንተ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ትርጉሙም "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን፣ አለማወቄን፣ በሁሉም ነገር ወሰን ማለፌን፣ አንተ ከኔ የበለጠ የምታውቀውንም ማረኝ። አላህ ሆይ! ወንጀሌን፣ ሆን ብዬ የሰራሁትን፣ አለማወቄን፣ ቀልዴን ማረኝ፤ ይህ ሁሉም ከኔው ነው። አላህ ሆይ! ያስቀደምኩትን፣ ያዘገየሁትን፣ የመሰጠርኩትን፣ ግልፅ ያወጣሁትን ወንጀል ማረኝ፤ አንተ አስቀዳሚ ነህ፣ አንተም የሚያዘገይ ነህ፣ አንተም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህ።" ማለት ነው።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ጠቅላይ ከሆኑት የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዱዓዎች መካከል ይህ አንዱ ነበር: "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ" ሀጢዐቴን "አለማወቄንም" ያለ እውቀት ከኔ የተከሰተውንም ወንጀል ማረኝ። "በሁሉም ነገሬ ወሰን ማለፌንም" ከልክ ማለፌንም ማጓደሌንም ማረኝ። "አንተ ከኔ የበለጠ የምታውቀውንም ማረኝ።" አንተ አውቀኸው እኔ የረሳሁትን ማለት ነው። "አላህ ሆይ! ወንጀሌንና ሆን ብዬ የሰራሁትን ማረኝ" ወንጀልነቱን አውቄና ሆን ብዬ የሰራሁትንም ማረኝ። "ምሬንም ቀልዴንም" በቀልድ የሰራሁትንም በሁለቱም ሁኔታ ላይ ሆኜ የሰራሁትንም ማረኝ። "ይህ ሁሉ ከኔ ነው።" የተጠቀሱት ወንጀሎችና ነውሮች ቢሰበሰቡ ከኔው ናቸው። "አላህ ሆይ! ያስቀደምኩትን ወንጀል ማረኝ!" ያለፈውን "ያዘገየሁትንም ማረኝ" ለወደፊት የምሰራውን ማረኝ። "የመሰጠርኩትንም" የደበቅኩትን "ግልፅ ያወጣሁትንም" ይፋ ያወጣሁትን ማረኝ። "አንተ አስቀዳሚ ነህ! አንተም የሚያዘገይ ነህ!" ከፍጥረትህ የፈለግከውን ወደ እዝነትህ በመግጠምህም ለምትወደው ነገር ታስቀድማለህ። አንተ የፈለግከውንም ሰው እርሱን በማዋረድ ከነዚህ ነገሮች ታዘገየዋለህ። ከነገሮች ያዘገየኸውን የሚየስቀድም፣ ያስቀደምከውንም የሚያዘገይ የለም። "አንተ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህ።" ችሎታው የተሟላ፣ ፍላጎቱ የተሟላ፣ ለምትሻው ነገር ሁሉ ፈፃሚ ነህ ማለት ነው።
ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሚያመሹና በሚያነጉ ጊዜ እነዚህን ዱዓዎች ከማድረግ አይተዉም ነበር። "አላሁመ ኢኒ አስአሉከልዓፊያተ ፊድ-ዱንያ ወልአኺረቲ፣ አላሁመ ኢኒ አስአሉከል ዐፍወ ወልዓፊየተ ፊ ዲኒ ወዱንያየ ወአህሊ ወማሊ፣ አላሁም ስቱር ዐውረቲ -አው ዓውራቲ- ወአሚን ረውዓቲ፣ አሏሁም ሕፈዝኒ ሚን በይኒ የደየ፣ ወሚን ኸልፊ፣ ወዓን የሚኒ፣ ወዓን ሺማሊ፣ ወሚን ፈውቂ፣ ወአዑዙ ቢአዞመቲክ 'አን ኡግታለ ሚን ተሕቲ"» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤ አላህ ሆይ በዱንያዬ፣ በመጪው አለሜ፣ በቤተሰቤና ገንዘቤ ይቅርታህንና ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤ አላህ ሆይ ነውሬን ወይም ነውሮቼን ሸሽግልኝ፣ ከፍርሃቴም ደህንነትን ስጠኝ፤ አላህ ሆይ! ከፊት ለፊቴም፣ ከኋላዬም፣ ከቀኜም፣ ከግራዬም፣ ከበላዬም ጠብቀኝ! ከበታቼ ድንገታዊ ጥቃት ከሚደርስብኝም በልቅናህ እጠበቃለሁ።) ማለት ነው።
አቡዳውድ፣ ነሳኢ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲመሽና ሲነጋ እነዚህን ዱዓዎች ከማድረግ አይተዉም ነበር። (አላሁመ ኢኒ አስአሉከል ዓፊየተ) አላህ ሆይ! ከአለማዊ በሽታዎች፣ መከራዎችና ችግሮች፣ ከዲናዊ ፈተናዎችና ዝንባሌዎች ሰላም መሆንን (ፊድዱንያ ወልአኺረተ) በቅርቡም ሆነ በመጪው አለም እጠይቅሃለሁ። (አልላሁመ ኢኒ አስአሉከል ዐፍው) አላህ ሆይ! ወንጀሎቼን ማበስ፣ ይቅር ማለትህን (ወልዓፊየተ) ከነውር መፅዳትን (ፊዲኒ) በሃይማኖቴ ከሽርክ፣ ከቢድዓና ከወንጀሎች፤ (ወዱንያየ) በዓለማዊ ህይወቴ ደግሞ ከመከራዎች፣ ከሚያውክና ከክፋቶች (ወአህሊ) በቤተሰቤ ላይ በባለቤቴ፣ በልጆቼና ቅርብ ዘመዶቼ (ወማሊ) በገንዘቤና በስራዬ ላይ ደህና መሆንን እጠይቅሃለሁ። (አልላሁመስቱር ዐውራቲ) አላህ ሆይ! እኔ ላይ ያሉትን ነውሮች፣ ጉድለቶች፣ እንከኖችን ሸሽገኝ፤ ወንጀሌንም አብስ። (ወአሚን ረውዓቲ) ድንጋጤዬንና ፍርሃቴን ደህንነት ስጠው። (አልላሁመሕፈዝኒ) አላህ ሆይ! የሚያውኩኝንና መከራዎችን ከኔ አስወግድልኝ። (ሚን በይኒ የደየ፣ ወሚን ኸልፊ፣ ወዓን የሚኒ፣ ወዓን ሺማሊ፣ ወሚን ፈውቂ) (ከፊት ለፊቴም፣ ከኋላዬም፣ ከቀኜም፣ ከግራዬም፣ ከበላዬም) በዚህም አላህ ከሁሉም አቅጣጫዎች እንዲጠብቃቸው ጠየቁ። መከራዎችና መአቶች ወደ ሰው የሚመጡትና የሚዞሩት ከነዚህ አቅጣጫዎች መካከል በአንዱ ነውና። (ወአዑዙ ቢዐዞመቲከ አንኡግታል) በድንገት ከመያዝና ተዘናግቼ ከምጠፋ በልቅናህ እጠበቃለሁ። (ሚንተሕቲ) በመሬት መደርመስ ከመጥፋትም ባንተ እጠበቃለሁ።
የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህን ዱዓ አስተማሯት: "አልላሁመ ኢኒ አስአሉከ ሚነል ኸይሪ ኩሊህ፣ ዓጂሊሂ ወአጂሊህ፣ ማ ዓሊምቱ ሚንሁ ወማለም አዕለም፣ ወአዑዙ ቢከ ሚነ ሸሪ ኩሊህ፣ ዓጂሊሂ ወአጂሊህ ማዓሊምቱ ሚንሁ ወማለም አዕለም። አላሁመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ኸይሪ ማሰአለከ ዐብዱከ ወነቢዩከ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማዓዘ ቢሂ ዐብዱከ ወነቢዩክ፣ አላሁመ ኢኒ አስአሉከል ጀነተ ወማ ቀረበ ኢለይሃ ሚን ቀውሊን አው ዓመሊን፣ ወአስአሉከ አንተጅዐለ ኩለ ቀዷኢን ቀደይተሁ ሊ ኸይራ" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ቅርቡንም የዘገየውንም፣ ከርሱ ያወቅኩትንም ያላወቅኩትንም ሁሉንም እጠይቅሃለሁ፤ ከመጥፎ ነገርም ቅርቡንም የዘገየውንም፣ ከርሱ ያወቅኩትንም ያላወቅኩትንም ከሁሉም መጥፎ ነገር ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ባሪያህና ነቢይህ የጠየቀህን መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ፣ ባሪያህና ነቢይህ ከተጠበቁት መጥፎ ነገርም ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ጀነትንና ወደርሷ የሚያቃርብን ንግግር ወይም ተግባር እጠይቅሃለሁ። ከእሳትና ወደርሷ ከሚያቀርቡ ንግግሮችና ተግባሮች ባንተ እጠበቃለሁ። ለኔ የወሰንከውን ሁሉንም ውሳኔዎች መልካም እንድታደርግልኝም እጠይቅሃለሁ።" ማለት ነው።
رواه ابن ماجه وأحمدነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዓኢሻን (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና ጠቅላይ ዱዓዎችን አስተማሯት። እነርሱም እነዚህ አራት ዱዓዎች ናቸው: የመጀመሪያው: ሁሉንም መልካም ነገር የጠቀለለ ዱዓ ነው (አላህ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ሁሉንም እጠይቅሃለሁ) አጠቃላዩን (ቅርቡንም) ወቅቱ የቀረበውን (የዘገየውንም) መምጫ ወቅቱ የራቀውንም (ከርሱ ያወቅኩትንም) ካሳወቅከኝም (ያላወቅኩትንም) ከአንተ እውቀት ብቻ ከሆነውም እጠይቅሃለሁ። በዚህም ነገሮችን አዋቂና ውስጠ አዋቂ ወደሆነው አላህ ብቻ ማስጠጋት አለበት። ይህንን ዱዓ ላደረገ ሙስሊም አሏህ በላጩንና የተሻለውን ይመርጥለታል። (ከመጥፎ ነገርም ቅርቡንም የዘገየውንም፣ ከርሱ ያወቅኩትንም ያላወቅኩትንም ከሁሉም ነገር) (መጠበቂያዬ) መጠጊያዬ አንተው ነህ። ሁለተኛው ዱዓ: አንድ ሙስሊም በዱዓው ወሰን ከማለፍ ጥበቃን የሚጠይቅበት ነው። (ባሪያህና ነቢይህ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጠየቁህን መልካም ነገር) (አላህ ሆይ እኔ እጠይቅሃለሁ) ከአንተ እፈልጋለሁ። (ባሪያህና ነቢይህ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከተጠበቁት መጥፎ ነገርም) (ባንተ እጠበቃለሁ) እጠጋለሁ። በዚህ ዱዓ ጠያቂው ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የለመኑትን የዱዓ አይነቶች ሳይቆጥር እርሳቸው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህን ከለመኑትና ከርሱ ከፈለጉት የተሻለውን እንዲሰጠው እየጠየቀ ነው። ሶስተኛው ዱዓ: ጀነት መግባትና ከእሳት መራቅን መፈለግ ነው። ይህም የሁሉም ሙስሊም ፍላጎትና የስራው ግብ ነው። (አላህ ሆይ! ጀነትን) በርሷ መጎናፀፍን (ወደርሷ የሚያቃርብን ንግግር ወይም ተግባርን እጠይቅሃለሁ።) የሚያስደስትህን መልካም ስራ እጠይቅሃለሁ። (ከእሳትም በአንተ እጠበቃለሁ።) በአንተ እዝነት ካልሆነ በቀር ከፀያፍ ተግባር መጠበቂያ የለምና። (ወደርሷ ከሚያቃርብ ንግግር ወይም ተግባርም በአንተ እጠበቃለሁ።) ከሚያስቆጣህ ወንጀል በአንተ እጠበቃለሁ ማለት ነው። አራተኛው ዱዓ: በአላህ ውሳኔ የመውደድ ዱዓ ነው። (ለኔ የወሰንከውን ሁሉንም ውሳኔዎች መልካም እንድታደርግልኝ እጠይቅሃለሁ።) አላህ ለኔ የወሰነውን ነገር ሁሉ ለኔ መልካም እንዲያደርግልኝ እጠይቃለሁ። ይህም በአላህ ፍርድ የመውደድ ዱዓ ነው።
ከዓብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዱዓ መካከል ይህ ዱዓ አንዱ ነበር: "አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዘዋሊ ኒዕመቲክ፣ ወተሐውዉሊ ዓፊየቲክ፣ ወፉጃአቲ ኒቅመቲክ፣ ወጀሚዒ ሰኸጢክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ፀጋህ ከመወገዱ፣ ለኔ የሰጠኸኝ ደህንነት ከመቀልበስ፣ ከድንገተኛ መከራህ፣ ከአጠቃላይ ቁጣህ በአንተ እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአራት ነገሮች ተጠበቁ: የመጀመሪያው: (አላህ ሆይ! ፀጋህ ከመወገዱ በአንተ እጠበቃለሁ!) ከሃይማኖታዊም ከአለማዊውም ፀጋህ መወገድ በአንተ እጠበቃለሁ፤ በእስልምና ላይ መፅናትንና ፀጋን የሚያስወግድ ከሆነ ወንጀል ላይ ከመውደቅም መራቅን እጠይቅሃለሁ። ሁለተኛው: (ለኔ የሰጠኸኝ ደህንነት ከመቀልበስ) ወደ መከራ ከመለወጥ ማለት ነው። ዘውታሪ ደህንነትንና ከሁሉም በሽታዎችና ህመሞች ሰላም መሆንን እጠይቅሃለሁ። ሶስተኛው: (ከድንገተኛ መከራህ) ከባድ አደጋ ወይም መዐት ማለት ነው። መከራና ቅጣት በድንገት የመጣ ወቅትና ለተውበትና ለመመለስ ጊዜ ከሌለ ለተፈተነበት ሰው መከራው ትልቅና አደገኛ ይሆናል። አራተኛው: (ከአጠቃላይ ቁጣህ) ለቁጣህ የሚያስገድዱ ከሆኑ ምክንያቶች በአንተ እጠበቃለሁ፤ አንተ የተቆጣህበት ሰው በርግጥም ባዶ ቀረ ከሰረ ማለት ነው። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጠቅላይ የሆኑ ቃላትን የተጠቀሙት የአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ቁጣ ምክንያቶች የሆኑትን ንግግሮች፣ ተግባሮችና እምነቶችን በሙሉ እንዲያጠቃልል ነው።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በነዚህ ቃላቶች ዱዓ ያደርጉ ነበር: "አላህ ሆይ! እኔ በእዳ ከመሸነፍ፣ በጠላት ከመሸነፍና የጠላቶች ደስታ ምንጭ ከመሆን ባንተ እጠበቃለሁ።"
ነሳኢና አሕመድ ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከነዚህ ጉዳዮች ጥበቃን ፈለጉ: የመጀመሪያው: (አላህ ሆይ! እኔ በአንተ እጠበቃለሁ) በሌላ በማንም ሳይሆን (በእዳ ከመሸነፍ) ከእዳ ጭንቀት፣ ችግር፤ እዳውን በመክፈልና በመዝጋት ያንተን እገዛ እጠይቅሃለሁ። ሁለተኛው: (በጠላት ከመሸነፍ) በኔ ላይ ጠላት የበላይ ከመሆንብኝና ከሚቆጣጠረኝ፤ የርሱን ጉዳት መከላከልና በርሱ ላይ ድል መቀናጀትን እጠይቅሃለሁ። ሶስተኛው: (የጠላቶች የደስታ ምንጭ ከመሆን) ሙስሊሞችን በሚያገኛቸው መከራና ችግር ደስተኛ ከመሆናቸው በአንተ እጠበቃለሁ ማለት ነው።