Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way






























Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙስሊም ወንጀለኛ ወንጀሉን በፉከራና በብልግና ይፋ የሚያወጣ ካልሆነ በቀር የአላህን ይቅርታና ምህረት የማግኘት ተስፋ እንዳለው ገለፁ። ወንጀሉን ይፋ የሚያደርግ ግን ይቅርታ አይገባውም። ምሽት ላይ ወንጀል ይሰራል ከዚያም አላህ ሸሽጎለት አንግቶ ሳለ ለሌላ ሰው ትናንት የሆነች ወንጀልን እንደሰራ ይናገራል። ጌታው ሸሽጎለት አድሮ ሳለ የአላህን ግርዶሽ የገለጠ ሆኖ ያነጋል።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ አሳምሮ ካልሆነ በቀር እንዳይሞት አነሳሱ። ይህም ጣእረ ሞት ላይ የሆነ ጊዜ አላህ እንደሚያዝንለትና ይቅር እንደሚለው በማሰብ ተስፈኝነቱን በማመዘን ነው። በሸሪዓ አላህን መፍራት የተፈለገው ስራችንን እንድናሳምር ስለሚረዳን ነው። ይህ ያለበት ሁኔታ ደግሞ የስራ ሁኔታ አይደለምና በዚህ ሁኔታ ላይ የሚፈለገው ተስፈኝነትን ማመዘን ነው።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በኢስራእና ሚዕራጅ ምሽት የአላህ ፍፁም ወዳጅ የሆኑትን ኢብራሂምን ዐለይሂ ሰላም እንዳገኙ ተናገሩ። ለርሳቸውም «ሙሐመድ ሆይ! ለኡመትክ የኔን ሰላምታ አድርስ! ጀነት አፈሯ ምርጥና ውሃዋም ጨውነት የሌለው ጣፋጭ ውሃ እንደሆነ፤ ጀነት ዛፍ የሌለበት ቀጥ ያለና ሰፊ ሜዳ ሲሆን የጀነት ተክልም ምርጥ ንግግሮችና ቀሪ የሆኑ መልካም ስራዎች እንደሆኑ እነርሱም: "ሱብሓነላህ" "ወልሐምዱሊላህ" "ወላኢላሃ ኢለሏህ" "ወሏሁ አክበር" እንደሆኑና አንድ ሙስሊም በደጋገማቸው ቁጥር ጀነት ውስጥ ተክል እንደሚተከልለት ንገራቸው።» አሉ።
አንድ ሰውዬ ቅርብ ዘመዶች እንዳሉትና ከነርሱም ጋር በመልካም መስተጋብር እንደሚኗኗር እነርሱ ግን ከዚህ ተቃራኒ በሆነ መንገድ እንደሚኗኗሩት ለነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስሞታ አቀረበ። እርሱ ይቀጥላቸዋልም፤ ይጠይቃቸዋልም፤ እነርሱ ግን ይቆርጡታል። በበጎነትና በታማኝነት ለነርሱ መልካም ቢውልም እነርሱ ግን በግፍና በድርቅና መጥፎ ይሰሩበታል። ይታገሳቸዋልም፤ ይቅር ይላቸዋልም፤ እነርሱ ግን በፀያፍ ንግግርና ተግባር ይቅርታውን ችላ ይላሉ። ከነዚህ ከተጠቀሱት ተግባራቸው ጋር ዝምድና መቀጠሌን ልግፋበትን? ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለርሱ እንዲህ አሉት: እንዳወሳኸው ከሆነ አንተ ራሳቸውን እንዲያዋርዱና እንዲንቁ ነው ያደረግካቸው። በጎ መዋልህ በዝቶላቸው የነርሱ ነፍስ ግን ፀያፍ ተግባር ብቻ መስራቱ ልክ ትኩስ አመድ እንዳበላሀቸው ነው። አንተ ባወሳህልኝ በጎ መዋል ላይ እስከዘወተርክና እነርሱም ላንተ መጥፎ ማድረግ ላይ እስከዘወተሩ ድረስ በነርሱ ላይ የሚያግዝህና የነርሱን ማወክ የሚከላከልልህ ከአላህ ዘንድ የሆነ አጋዥም ከአንተ አይወገድም።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በግማትና ቀፋፊነት በአህያ ጥንብ ላይ እንደተሰባበሱ ሰዎች አምሳያ ሆነው የሚነሱ እንጂ አንድ ስፍራ ላይ ተቀምጠው ከዚያም በዛ ስፍራ አላህን ሳያወሱበት የሚነሱ ሰዎች የሉም። ይህም አላህን ከማውሳት በወሬ ስለተጠመዱ ነው። የትንሳኤ ቀንም በዚህ አቀማመጣቸው ሰበብ በነርሱ ላይ ቁጭት፣ ጉድለትና ፀፀት እንደማይለቃቸው ተናገሩ።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህን በሚያወሳና በማያወሳ ሰው መካከል ያለውን ልዩነት ከጥቅሙና ማንነቱ ከማማሩ አንፃር የነርሱ ምሳሌን በህይወት ባለና በሞተ ሰው ምሳሌ ገለፁ። ጌታውን የሚያወሳ ሰው ምሳሌ ውጫዊ ማንነቱ በህይወት ብርሃን፣ ውስጣዊ ማንነቱ ደግሞ በእውቀት ብርሃን እንደተዋበ ሰው ነው። ጥሩ ነገር ያለውም እዚህ ላይ ነው። አላህን የማያወሳ ሰው ምሳሌ ደግሞ ውጫዊ ማንነቱ ከውበት እንደተራቆተ ውስጣዊ ማንነቱ ደግሞ በጥመት እንደተሞላ ሙት ሰው ነው ምሳሌው። ከርሱም ጥሩ ነገር አይገኝም። ልክ እንደዚሁ ቤትም የሚኖሩበት ሰዎች አላህን የሚያወሱ ከሆኑ በህያውነት ያለበለዚያ ደግሞ ነዋሪዎቹ አላህን ከማውሳት የተራቆቱ ስለሆኑ በሙታን ይመሰላል። ህያውነትና ሙታንነት የሚለው ባህሪ ለቤት ከሆነ የዋለው የሚፈለግበት ቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ነው።
አንድ ቀን ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባልደረቦቻቸውን ለማናገር ሚንበር ላይ ተቀመጡና እንዲህ አሉ: ከኔ በኋላ በናንተ ላይ እጅግ አብዝቼ የምፈራላችሁ ነገር ቢኖር ለጥቂት ጊዜ የሚቆይ ከመሆኑም ጋር ለናንተ የሚከፈትላችሁን የምድር በረከት፣ የዱንያ ጌጥና ውበት፣ በውስጧ ያለውን የልብስ፣ የአዝርዕትና ሌሎችም ሰዎች በውበቱ የሚፎክሩበት የመጣቀሚያ አይነቶችን ነው። አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: የዱንያ ውበት የአላህ ፀጋ ነው። ይህ ፀጋ ታዲያ ወደ ቅጣትና መዐትነት ይለወጣል ማለት ነውን? ሰዎች የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዝምታ ሲመለከቱ አስቆጥቷቸዋል ብለው በማሰብ ጠያቂውን ወቀሱት። በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ወሕይ እየወረደ እንደነበር ግልፅ ሆነላቸው። ቀጥለውም ላባቸውን ከግንባራቸው ላይ እየጠረጉ ጠያቂው የት አለ? አሉ። እርሱም "እኔ ነኝ!" አለ። አላህን አመሰግነው በርሱም ላይ ካወደሱ በኃላ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: "ትክክለኛ መልካም ነገር መልካሙን እንጂ ሌላ ነገር ይዞ አይመጣም። ነገር ግን ይህቺ የዱንያ ውበት ወደ ፈተና፣ እሽቅድድም፣ ወደ መጪው አለም ሙሉ ለሙሉ ከመዞር ስለምታጠምድ ጥርት ባለ መልኩ መልካም አይደለችም። ቀጥለው እንዲህ በማለት ለዚህ ምሳሌን ጠቀሱ "የፀደይ ቡቃያና አትክልት እንስሶች ለመጋጥ የሚወዱት ስለሆነ አብዝተው በመብላታቸው በቁንጣን ይገላቸዋል፤ ወይም ወደ ሞት ያቀርባቸዋል። ይህ ግን የሆዷ አንድ ጎን እስኪሞላ አትክልቱን ግጣ ቀጥላ ወደ ፀሃይ ዞራ ከሆዷ ቀጭን ሰገራዋን አውጥታ ወይም ሸንታ ሆዷ የገባውን መልሳ አውጥታ አመንዥካ ድጋሚ የምትውጥ ከዚያም ተመልሳ የምትግጥ እንስሳን አይገድላትም። አሉ። ይህ ገንዘብም እንደ ጣፋጭ አትክልትና ቡቃያ ነው። በሐላል መንገድ አግኝቶት በሚያስፈልገው ያህልና በቂውን በሚያገኝበት ብቻ በጥቂት ገንዘብ ላይ የተብቃቃ ሲቀር ከበዛ ይገድላል ወይም ለመግደል ይቀርባል። የሚያስፈልገውን ብቻ ከሆነ የሚጠቀመው አይጎዳውም። ለሚስኪኖች፣ ለየቲሞችና ለመንገደኞች የሚሰጥ ሙስሊም ሰው ምንኛ ያማረ ነው! ገንዘብን በአግባቡ የሚይዝ ይባረክለታል። ያለአግባብ የሚይዘው ደግሞ የርሱ ምሳሌ እየበላ እንደማይጠግብ ሰው ምሳሌ ነው። በርሱ ላይም የትንሳኤ ቀን ይመሰከርበታል።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የትንሳኤ ቀን እጅግ ዝቅተኛ ቅጣት የሚቀጣው የእሳት ነዋሪ ለርሱ ሁለት የእሳት ጫማዎችና ማሰሪያዎች የሚደረግለት ሰው እንደሆነና ከአቃጣይነታቸው የተነሳ የነሃስ ድስጥ እንደሚንፈቀፈቀው አንጎሉም የሚንፈቀፈቅ መሆኑን፤ ከርሱ የበለጠ የሚቀጣ አንድም ሰው አለ ብሎም እንደማያስብ፤ እርሱ ግን እጅግ ዝቅተኛውን ቅጣት የሚቀጣ ነው መሆኑን ተናገሩ። ይህንን የሚያስበውም አካላዊ ቅጣቱ ከመንፈሳዊ ቅጣቱ ጋር በጋራ እንዲቀጣበት ነው።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሰዎች መካከል "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱሁ" የሚለውን ሰላምታን የማቅረብ ስነ-ስርዓትን ጠቆሙ። ይኸውም ህፃን ለትልቅ፣ ጋላቢ ለእግረኛ፣ እግረኛ ለተቀማጭ፣ ጥቂት ቁጥር ያላቸው በብዙዎቹ ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።