Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way






























Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
ልኡካኖች ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጡ። ወደርሳቸውም የደረሱ ጊዜ እርሳቸውን ለማሞገስ ፈልገው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያልወደዷቸውን የተወሰኑ ንግግሮች ተናገሩ። "አንቱ አለቃችን የሆኑ!" አሏቸው። ነቢዩም ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የሁሉም አለቃ አላህ ነው።" በፍጡራኑ ላይ የተሟላ አለቃነት የርሱ ነው። ፍጡራን ባሮቹ ናቸው። "በደረጃ በላጫችን የሆኑ" አሉ። ማለትም በደረጃ፣ በልቅና ከፍ ያሉ ማለት ነው። "እጅግ ታላቅ የሆኑ" በጣም ለጋስ፣ ከፍታና ልቅና ያለዎት ለማለት ነው። ቀጥለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተለመደውን ንግግራቸውን እንዲናገሩ፣ በቃላቶች ወሰን እንዳያልፉና ክልክል ወደሆነው ሺርክና መዳረሻዎቹ ለሚዳርገው ወሰን ማለፍና ያልተገባ ሙገሳም ሰይጣን እንዳይጎትታቸው (መጠንቀቅ እንዳለባቸው) ሱሓቦችን ጠቆሙ።
ኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የመሰናበቻ ሐጅ ወቅት የእርድ ቀን ጀምረተል ዐቀባ ንጋት ላይ ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር እንደነበረ ተናገሩ። የሚወረውሩት ጠጠር እንዲለቅምላቸው አዘዙት። እርሱም ሰባት ጠጠሮች ለቀመላቸው። እያንዳንዱም ጠጠር የሽንብራ ወይም የለውዝ ፍሬ መጠን ነበር ያላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በእጃቸው ላይ አኑረውት ጠጠሮቹን መዳፋቸው ላይ እያንከባለሉ እንዲህ አሉ: የምትወረውሩት ጠጠር በዚህ ልክ ይሁን። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ወሰን ከማለፍና ከማክረር አስጠነቀቁ። የቀደሙ ህዝቦችን ያጠፋው ወሰን ማለፍና በሃይማኖት ላይ ከልክ በላይ ማክረር መሆኑንም ተናገሩ።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነገሮች ባጠቃላይ በአላህ እጅ መሆናቸውንና በትእዛዙና በውሳኔው ካልሆነ በቀር ምንም ነገር እንደማይሆን ለመግለፅ አንዳንድ የድንቁርና ዘመን ጉዳዮችን አብራሩ። እነሱም:- የመጀመሪያው: የድንቁርና ዘመን ሰዎች በሽታ በራሱ ይተላለፋል ብለው ያስቡ ነበር። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሽታ በራሱ ከበሽተኛው ወደ ሌላው ይተላለፋል የሚለውን እምነት ከማመን ከለከሉ። በአጽናፈ ዓለሙ የሚያስተናብረው፣ በሽታን የሚያወርደውም የሚያነሳውም አላህ ብቻ ነው። ይህ ሁሉ በርሱ ፍላጎትና ውሳኔ ካልሆነ በቀር አይከሰትም። ሁለተኛ: የድንቁርና ዘመን ሰዎች ለጉዞ ወይም ለንግድ የወጡ ጊዜ በራሪ ያበሩና ወደ ቀኝ አቅጣጫ ከበረረ ተስፋ ያደርጋሉ፤ ወደ ግራ አቅጣጫ ከበረረ ደግሞ እድለ ቢስነትን አምነው ይመለሱ ነበር። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከዚህ በበራሪ ገደቢስ ማመንን ከለከሉ። ከንቱ እምነት መሆኑንም ገለፁ። ሶስተኛ: የድንቁርና ዘመን ሰዎች ጉጉት በአንድ ግቢ ላይ ካረፈ የዛ ግቢ ቤተሰብ መከራ ያጋጥመዋል ብለው ያምኑ ነበር። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከዚህ ገደቢስነት እምነት ከለከሉ። አራተኛ: በሰፈር ወር ገደቢስነትን ከማመንም ከለከሉ። ይህ ወር በጨረቃ አቆጣጠር ሁለተኛው ወር ነው። ሰፈር በማለት የተፈለገው ከብቶችና ሰዎች ሆድ ውስጥ የሚገኝ ጥገኛ ትል ነው ተብሏል። ይህ ትልም ከቁምጥና በሽታ የበለጠ ይተላለፋል ብለው ይሞግታሉ ብለው የተረጎሙትም አሉ። ይህን እምነትም ውድቅ አደረጉ። አምስተኛ: ከአንበሳ እንደምትርቀው በቁምጥና ከተያዘ ሰውም መራቅን አዘዙ። ይህም ለነፍስ ደህንነትን ከመፈለግ፣ ለጥንቃቄና አላህ ያዘዘውን ሰበብ ለማድረስ ያህል ነው። ቁምጥና (ሥጋ ደዌ): ሰውነትን የሚበላ የሆነ በሽታ ነው።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሽታ ከአንዱ ወደ ሌላው ያለ አላህ ውሳኔ በራሱ ይተላለፋል የሚለው የድንቁርና ዘመን ሰዎች ያምኑት የነበረው እምነት የተሳሳተ ከንቱ እምነት መሆኑን ተናገሩ። የገድ እምነትም ከንቱ አጉል እምነት ነው። እርሱም በማንኛውም የሚሰማ ወይም የሚታይ ወፍ ወይም እንስሳ ወይም አካል ጉዳተኞችን ወይም ቁጥሮች ወይም ቀናት ወይም ከዚህ ውጪ ባሉ ነገሮች ላይ ተመርኩዞ ገደቢስነትን ማመን ነው። ወፍን ያወሱት በድንቁርና ዘመን የታወቀው ገድ ማለት በርሱ ስለነበር ነው። መሰረቱም ስራ ወይም ጉዞ ወይም ንግድ ወይም ከዚህ ውጪ ያለ ጉዳይ ሊጀምሩ ሲፈልጉ ወፍን ይለቃል። ወፊቱ ወደ ቀኝ ከበረረች ጥሩ ገድ በማመን ወደፈለገው ይጓዛል። ወደ ግራ አቅጣጫ ከበረረች ደግሞ ገደቢስነትን በማመን ከፈለገው ጉዳይ ይቆጠባል። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "አልፈእል" (በጎ ምኞት) እንደሚያስደስታቸው ተናገሩ። እርሱም የሰው ልጅ ከሰማው መልካም ቃል አንፃር የሚያጋጥመው የደስታና ሀሴት ስሜት ነው። ይህም በጌታው ላይ መልካም እሳቤ እንዲኖረው ያደርጋልና።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመዲና ነዋሪ የሆኑትን አንሷሮች መውደድ የኢማን መሙላት ምልክት መሆኑን ተናገሩ። ይህም የሆነው ኢስላምንና ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመርዳት ላይ፣ ሙስሊሞችን በማስጠጋት ላይ ባደረጉት ልፋት፣ ገንዘቦቻቸውንና ነፍሳቸውንም በመለገስ በኩል ቀዳሚ ስለሆኑ ነው። እነርሱን መጥላትም የንፍቅና ምልክት ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንሷሮችን የወደደ አላህ እንደሚወደው እነሱን የጠላም አላህ እንደሚጠላው ገለፁ።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶሐቦች እንዲሰሩ፤ ወሰን ሳያልፉና ሳያጓድሉ በቻሉት ልክ አላህንም እንዲፈሩ፤ ስራቸው ተቀባይነት አግኝቶ በነርሱ ላይ የአላህ እዝነት እንዲወርድ ሰበብ እንዲሆንም በስራቸው ለአላህ በማጥራትና ሱናን በመከተል በትክክል መስራትን እንዲያስቡ አነሳሱ። ቀጥለውም ከናንተ መካከል አንድም ሰው በስራው ብቻ አይድንም። ይልቁንም የግድ የአላህ እዝነት ያስፈልገዋል ብለው ነገሯቸው። ሰሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የእርሶ ሥራ እንዲህ መጠኑ ከመግዘፉ ጋርም (መልካም ስራዎ ብቻውን) አያድኖትምን?" አሉ። እርሳቸውም "እኔም ብሆን አላህ በችሮታውና በእዝነቱ እስካልሸፈነኝ ድረስ በስራዬ ብቻ አልድንም።" አሉ።
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከርሳቸው በፊት አላህ በህዝቦች ውስጥ የላከው እያንዳንዱ ነቢይ ከህዝቦቹ መካከል የተመረጡ፣ ረዳቶች፣ ታጋዮች፣ ታማኞች፣ ከርሱ በኋላ ለተተኪነት የሚበጁ፣ ፈለጉን የሚይዙና ትእዛዙንም የሚከተሉ ባልደረቦች ይኖሩታል፤ ከዚያም ከነዚህ መልካም አበዎች በኋላ ግን ምንም መልካም የሌላቸው የማይሰሩትን የሚናገሩና ያልታዘዙትን የሚሰሩ ሰዎች ይመጣሉ። በእጁ የታገላቸው እርሱ አማኝ ነው። በምላሱ የታገላቸው እርሱም አማኝ ነው። በቀልቡም የታገላቸው እርሱ አማኝ ነው። ከዚህ ውጪ የሆነ ሰው ግን የጎመንዘር ፍሬ ያህል እንኳ ኢማን እንደሌለው ተናገሩ።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከርሳቸው በፊት ለነበረ ለአንድም ነቢይ ያልተሰጡ አምስት ነገሮች አላህ ለርሳቸው እንደሰጠ ተናገሩ: የመጀመሪያው: በፍርሃት ተረድቼያለሁ። በኔና በነርሱ መካከል የወር መንገድ ቢቀር ራሱ የጠላቶቼን ልብ ፍርሃት ይወራቸዋል። ሁለተኛው: ምድር ለኛ መስጂድ ተደርጋለች። የትም ብንሆን እንሰግዳለን። ውሃ መጠቀም በተሳነን ጊዜ ደሞ አፈሯ መፅጃ ተደርጎልናል። ሶስተኛ: ለኛ የጦርነት ምርኮ ተፈቅዶልናል። ይህም ሙስሊሞች ከከሃዲዎች ጋር በሚያደርጉት ጦርነት የሚማርኩት ንብረት ነው። አራተኛ: ሰዎችን ከትንሳኤ ቀን መቆም ጭንቀት የምገላግልበት ትልቁ ምልጃ ተሰጥቶኛል። አምስተኛ: ወደ ፍጡራን ባጠቃላይ ወደ ሰዉም ወደ ጂኑም ሁሉ ተልኬያለሁ። ይህም ከርሳቸው በፊት ከነበሩት ነቢያት ተቃራኒ መሆኑ ነው። እነርሱ ይላኩ የነበሩት ወደ ህዝባቸው ብቻ ነበርና።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጀነትና የእሳት ነዋሪዎችን አንዳንድ ባህሪያት ተናገሩ። አብዛኛው የጀነት ነዋሪዎች "ደካማና ዝቅ የሚደረጉ ናቸው።" ማለትም ለአላህ የሚተናነስና የሚዋደቅ፣ ነፍሱንም ለአላህ ዝቅ ያደረገ ነው። አንዳንድ ሰዎች ዝቅ ያደርጉታልም ይንቁታልም። ይህ ለአላህ ብሎ ነፍሱን ዝቅ ያደረገ ሰው የአላህን ችሮታ ፈልጎ በአንድ ጉዳይ በአላህ ላይ ቢምል አላህ መሀላውን እውን የሚያደርግለት፤ የማለበትን ነገር የሚፈፅምለት፤ ፍላጎቱንና ዱዓውን የሚያሟላለት አይነት ሰው ነው። አብዛኛው የእሳት ነዋሪዎች "ልበ ደረቅ የሆነ ሁሉ" ይህ ቃል ደረቅ ለሆነ፣ አክርሮ ለሚሟገት ወይም መልካምን ለማይቀበል ባለጌ ሰው የሚውል ነው። "ትዕቢተኛ" (ጀዋዝ) ይህም ማለት ኩራተኛ፣ ሆዳም፣ ዝርፍጥ፣ ሲራመድ የሚንቦጣረርና መጥፎ ስነምግባር የተላበሰ ማለት ነው። "በኩራት የተሞላ" ማለት እውነትን ባለመቀበልና ሌላውን በመናቅ የሚኮራ ማለት ነው።