





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ጀናዛ (ሬሳ) ቃሬዛ ላይ የተቀመጠች ጊዜና ሰዎች ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ ሬሳዋ መልካም ከሆነች "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች። መልካም ካልሆነች ደግሞ "ወዬውላት የት ነው ይዛችኋት የምትሄዱት?" ትላለች። ከሰው በቀር ያለ ነገር ሁሉ ድምጿን ይሰማል። የሰው ልጅ ቢሰማው ኖሮ ራሱን ስቶ ይወድቅ ነበር።"
ቡኻሪ ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጀናዛ ቃሬዛ ላይ የተቀመጠ ጊዜና ሰዎችም ትከሻቸው ላይ የተሸከሟት ጊዜ መልካም ከሆነች ከፊት ለፊቷ ፀጋዎችን ስለምትመለከት "ቀደም አድርጉኝ!" ትላለች። መልካም ካልሆነች ደግሞ ከፊት ለፊቷ ቅጣትን ስለምትመለከት በሚያወግዝ ድምፅ "ወይ ጥፋቷ! የት ነው ይዛችኋት የምትሄዱት?!" ትላለች። ከሰው በቀር ሁሉ ነገር ድምጿን ይሰማታል። ሰው ቢሰማው ኖሮ የሚሰማው ነገር ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ራሱን ይስት ነበር አሉ።
ከሚቅዳድ ቢን አስወድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "የትንሳኤ ቀን ፀሐይ ወደ ፍጡራን የአንድ ሚል (ማይል) ያህል ትቀርባለች።" ሱለይም ቢን ዓሚርም እንዲህ አለ "በአላህ እምላለሁ! እርሳቸው ሚል በማለት የፈለጉት የምድር ርቀት መለኪያውን ይሁን ወይስ ዐይን መኳያ እቃውን ይሁን ምን እንደፈለጉበት አላውቅም።" ነቢዩ እንዲህም ብለዋል "ሰዎችም እነደየስራቸው መጠን በላብ ይጠመቃሉ። ከነርሱ መካከል ላቡ እስከቁርጭምጭሚቱ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱ መካከል እስከጉልበቱ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱ መካከል እስከመታጠቂያው ድረስ የሚሆንም አለ፤ ከነርሱ መካከልም ላቡ የሚለጉመው አለ።" ብለው የአላህም መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በእጃቸው ወደአፋቸው ጠቆሙ።»
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የትንሳኤ ቀን ፀሐይ ወደ ፍጡራን ከጭንቅላታቸው በላይ የማይል ያህል እንደምትቀርብ ተናገሩ። ታቢዒዩ ሱለይም ቢን ዓሚርም እንዲህ አለ: በአላህ እምላለሁ! የአላህ መልክተኛ ሚል የሚለው ቃል ከሚሰጠው ሁለት ትርጓሜዎች የትኛውን እንደፈለጉበት አላውቅም። የምድር ርቀት መለኪያውን ማይል ነው ወይስ አይን መኳያውን ሚል ነው የፈለጉበት የሚለውን አላውቅም። እንዲህም አሉ: "በስራቸው ልክም በላብ ውስጥ ይጠመቃሉ። ከነርሱ መካከል ላቡ እስከቁርጭምጭሚቱ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱም መካከል ላቡ እስከጉልበቱ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱም መካከል ላቡ እስከሽርጥ መታጠቂያው እስከ ወገቡ ድረስ የሚሆን አለ፤ ከነርሱም መካከል ላቡ እስከ አፉ ድረስ የሚሆንና መናገር የሚከለክለው አለ።" ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህንን ብለው በእጃቸው ወደ አፋቸው ጠቆሙ።
ከአቢ ቡርዳህ ቢን አቢ ሙሳ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «አቡ ሙሳ ከባድ ህመምን ታመመና ራሱን ሳተ። ጭንቅላቱ ሚስቱ ታፋ ላይ ነበር። (ስታለቅስና ስትገጥም) በርሷ ላይ አንዳችም መልስ መስጠት አልቻለም ነበር። የነቃ ጊዜ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ራሳቸውን ካጠሩት ሰው እኔም የጠራሁ ነኝ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመከራ ወቅት ከምትጮህ፣ ከምትላጭና ልብሷን ከምትቀዳድድ ራሳቸውን አጥርተዋል።"»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።አቡቡርዳህ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - አባቱ አቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከባድ በሽታ እንደታመመና ራሱን እንደሳተ ተናገረ። ጭንቅላቱም ባለቤቱ ታፋ ላይ ነበር። እርሷም እየጮኸች ሙሾ አወረደች። ራሱን ስቶ ስለነበረ አንዳችም ሊመልስላት አልቻለም ነበር። የነቃም ጊዜ እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ራሳቸውን ካጠሩት ሁሉ እኔም አጥርቻለሁ። ነቢዩ: (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከነዚህ ራሳቸውን አጥርተዋል: ከ "ሷሊቃህ": በመከራ ወቅት ድምጿን ከፍ ከምታደርግ፤ ከ "ሓሊቃህ": በመከራ ወቅት ፀጉሯን ከምትላጭ፤ ከ "ሻቃህ": በመከራ ወቅት ልብሷን ከምትቀዳድ የጠራሁ ነኝ ብለዋል። እነዚህ ነገሮች የድንቁርናው ዘመን መገለጫ ስለሆኑ ነው። ይልቁንም በመከራ ወቅት ትእግስት በማድረግና ምንዳውን አላህ ዘንድ በማሰብ አዘዙ።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: «"አንድ ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ላይ ያሉት መብቶች ስድስት ናቸው።" ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ምንድን ናቸው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ያገኘኸው ጊዜ ሰላምታን አቅርብለት፤ የጠራህ ጊዜ ጥሪውን አክብር፤ ካንተ ምክርን በፈለገ ጊዜ ምከረው፤ አስነጥሶ አላህን ያመሰገነ ጊዜ "የርሐሙከሏህ" በለው፤ የታመመ ጊዜ ጠይቀው፤ የሞተም ጊዜ ቅበረው።"»
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ወንድሙ ላይ ካሉት ሐቆች መካከል ስድስቱን ጠቀሱ፡ የመጀመሪያው: ባገኘው ጊዜ "አስሰላሙ ዐለይኩም" (ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን) በማለት ሰላምታውን ያቅርብለት። እርሱም "ወዐለይኩሙ-ስሰላም" በማለት ሰላምታውን ይመልስለት። ሁለተኛው: ለሰርግና ለሌሎች ድግሶች በጠራው ጊዜ ጥሪውን ማክበር ነው። ሶስተኛው: ምክር ባስፈለገው ጊዜ ያለምንም ማሞኘትና ማታለል መምከር ነው። አራተኛው: አስነጥሶ "አልሐምዱሊላህ" (ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባው ነው) ያለ ጊዜ "የርሐሙከላህ" (አላህ ይዘንልህ፤ ይቅር ይበልህ) በማለት አስደስተው። እርሱም "የህዲኩሙሏህ ወዩስሊሕ ባለኩም" (አላህ ይምራህ፤ ጉዳይህንም ያስተካክልልህ) በማለት ይመልስ። አምስተኛው: በታመመ ጊዜ ይጠይቀው፤ ይጎብኘው። ስድስተኛው: በሞተ ጊዜ ይስገድበት፤ እስኪቀበር ድረስም ጀናዛውን ይከተለው።
ከአማኞች እናት ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ድነው ያልተነሱበት በሆነው በሽታቸው ወቅት እንዲህ አሉ: "አላህ አይሁድና ክርስቲያኖችን ረገመ። የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስጂድ አድርገው ያዙ። ዓኢሻም እንዲህ አለች: "ይህ (እርግማናቸው) ባልነበረ ኖሮ ቀብራቸው ይፋ ይሆን ነበር። ነገር ግን መስጂድ ተደርጎ እንዳይያዝ ተፈራ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።የአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጠንቶባቸው በርሱ ምክንያት የሞቱበት በሆነው በሽታቸው ወቅት እንዲህ ይሉ እንደነበር ተናገረች: "አይሁዶችና ክርስቲያኖችን አላህ ይርገማቸው። ከእዝነቱ ያባራቸው። ይህም እነርሱ የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስጂድ አድርገው ስለያዙ ነው።" ይህም መቃብሩ ላይ መስጂድ በመገንባት ወይም እርሱ ዘንድ ወይም ወደርሱ ዞሮ በመስገድ ነው። ቀጥላም ዓኢሻ (ረዺየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - "ይህ የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ክልከላና ማስጠንቀቂያ ባይኖር ኖሮና እንዲሁም አይሁዶችና ክርስቲያኖች በነቢያቶቻቸው መቃብር ላይ እንደፈፀሙት በነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቀብር ላይም እንዳይፈፀም ሶሐቦች ባይፈሩ ኖሮ ቀብራቸው ይፋና ግልፅ ይሆን ነበር።" አለች።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከየመን በቀረዝ ቅጠል ታሽቶ በተዘጋጀ ከረጢት ከማዕድኑ አፈር ያልጠራን የወርቅ ቁርጥራጭ ወደ አላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላከ። እሳቸውም ለአራት ሰዎች አከፋፈሉት። እነርሱም ዑየይና ቢን በድር፣ አቅረዕ ቢን ሓቢስ፣ ዘይድ አልኸይሊና አራተኛው ወይ ዐልቀማ ነው ወይም ዓሚር ቢን ጡፈይል ነው። ከርሳቸው ባልደረባ መካከል የሆነ አንድ ሰውዬም: "ከነዚህ የበለጠ እኛ የተገባን ነበርን!" አለ። ይህ ወሬም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘንድ ደረሰና እንዲህ አሉ: "እኔ በሰማይ ላለው (ለአላህ) ታማኝ ሆኜ፤ የሰማይ ወሬም ጠዋትና ማታ እየመጣልኝ አታምኑኝምን?!።" በዚህ ጊዜም አንድ አይኑ የጎደጎደ፤ ከአይኑ ስር ያሉት አጥንቶቹ ወጣ ያሉ፤ ከቅንድቡ በላይ ያለው ግንባሩም ወጣ ያለ፤ ፂሙ የበዛ፤ ጭንቅላቱ የተላጨ፤ ሽርጡን ከቁርጭምጭሚቱ በላይ ከፍ አድርጎ የታጠቀ ሰውዬ ቆመና: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አላህን ይፍሩ!" አላቸው። እርሳቸውም "ወዮልህ! ከምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አላህን ለመፍራት የተገባሁ እኔ አይደለሁምን?" አሉ። ከዚያም ሰውዮው ዘወር አለ። ኻሊድ ቢን ወሊድም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንገቱን ልቅላውን?" አላቸው። እርሳቸውም "በፍፁም! ምናልባት እርሱ ይሰግድ ይሆናል።" አሉ። ኻሊድም "ቀልቡ ውስጥ የሌለውን እምነት (ለይዩልኝ) በአፉ እየተናገረ የሚሰግድ ስንት ሰው አለ አይደል እንዴ?!" አላቸው። የአላህ መልክተኛም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "እኔ የሰዎችን ቀልብ እንድሰነጥቅ፤ ሆዳቸውንም ከፍቼ እንድመለከት አልታዘዝኩኝም።" አሉ። ከዚያም ወደዚህ ሰውዬ ጀርባውን ሰጥቶ እየተመለከቱት እንዲህ አሉ: "ከዚህ ሰውዬ ዘርና ባልደረቦች የሆኑ የአላህን መጽሐፍ ቀሏቸው የሚያነቡ፤ የሚቀሩት ግን ከጉሮሮዋቸው የማያልፍ፤ ቀስት ሲወረወር ከኢላማው እንደሚሾልከው ከእስልምና ሾልከው የሚወጡ ሰዎች ይመጣሉ።" እንዲህም ብለዋል ይመስለኛል: "እኔ ከደረስኩባቸው የሠሙድ ህዝቦችን አገዳደል እገድላቸዋለሁ።"»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በቀረድ ታሽቶ በተሰራ ከረጢት ከአፈሩ ያልፀዳ የወርቅ ቁርጥራጮችን ከየመን ወደ አላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላከ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለአራት ሰዎች አከፋፈሉት። እነርሱም: ዑየይና ቢን በድር አልፈዛሪይ፣ አቅረዕ ቢን ሓቢስ አልሐንዞሊይ፣ ዘይድ አልኸይሊ አንነብሃሊይ፣ ዐልቀማ ቢን ዐላሠህ አልዓሚሪይ ናቸው። ከርሳቸው ባልደረባ የሆነ አንድ ሰውዬም እንዲህ አለ: "በዚህ ስጦታ ከነዚህ በበለጠ እኛ የተገባን ነን።" ይህም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ ደረሰና እንዲህ አሉ: "እኔ በሰማይ ላለው (አላህ) ታማኝ ሆኜ የሰማይ ወሬ ጠዋትና ማታ እየመጣልኝ አታምኑኝምን?!" አይኖቹ ገባ ገባ ያሉ፤ የጉንጩ የላይኛው አጥንት ወጣ ያሉ፤ ግንባሩም ወጣ ያለ፤ ፂሙ ሳይረዝም የበዛ የሆነ፤ ጭንቅላቱን የተላጨ፤ የታችኛውን የሰውነት አካሉን የሚሸፍነው ሽርጡ ከፍ ያለ አንድ ሰውዬ ቆመና: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አላህን ይፍሩ!" አላቸው። እርሳቸውም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ወዮልህ! ከምድር ነዋሪዎች ባጠቃላይ አላህን ለመፍራት የተገባሁ እኔ አይደለሁምን?" አሉት። ከዚያም ሰውዬው ዞሮ ሄደ። ኻሊድ ቢን ወሊድም: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንገቱን አልቅላውምን?" አላቸው። እርሳቸውም "በፍፁም! ምናልባት የሚሰግድ ሊሆን ይችላል።" አሉት። ኻሊድም: "በቀልቡ የሌለውን በአፉ የሚናገር ስንት ሰጋጅ አለ?" አለ። እርሳቸውም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን): "እኔ የሰዎችን ቀልብ እንድሰነጥቅም ሆነ ሆዳቸውን ቀድጄ እንድመለከት አልታዘዝኩም። እኔ የታዘዝኩት ሰዎችን በውጫዊ ማንነታቸው እንድይዛቸው ነው።" አሉ። ከዚያም ሰውዬው ጀርባውን ሰጥቶ መሄዱን ሳለ እየተመለከቱት እንዲህ አሉ: "ከዚህ ሰውዬ ዘር፣ ከባልደረቦቹ ወይም ከጎሳዎቹ መካከል የአላህን መጽሐፍ በጥሩ ድምፅ አሳምረው በመቅራት ምርጥ ችሎታው ያላቸው፤ አብዝተው ከመቅራታቸውም ምላሳቸው ርጥብ የሆኑ፤ ንባባቸው ግን ከጉሮሮዋቸው የማታልፍ። ከጉሮሮ አልፋ ቀልባቸው ጋር ደርሳ የምታስተካክላቸው ያልሆነች፤ ንባባቸውን አላህ ከፍ የማያደርጋትም የማይቀበላትም፤ ቀስት ከኢላማው በላይ ፈጥኖና በቀላሉ እንደሚወጣው ከእስልምና የሚወጡ ህዝቦች ይመጣሉ።" እንዲህም ብለዋል ይመስለኛል: "በሰይፋቸው በሙስሊሞች ላይ መውጣታቸውን ብደርስበት ኖሮ እንደ ሠሙድ ህዝቦች አገዳደል ከባድ አገዳደልን እገድላቸው ነበር።"
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ «ጀነት ውስጥ የአንዳችሁ ትንሹ ደረጃ አላህ ለርሱ "ተመኝ" ይለዋል። እርሱም ደጋግሞ ይመኛል። አላህም ለርሱ "ተመኘህን?" ይለዋል። እርሱም "አዎን" ይላል። አላህም ይለዋል: "ላንተ የተመኘኸውንም ከርሱም ጋር የርሱን አምሳያ ሌላም ይሰጥሃል።"»
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጀነት ለገባ ሰው የሚሰጠው ትንሹና ዝቅተኛው ደረጃና ስፍራ አላህ ለርሱ እንዲህ ይለዋል: "ተመኝ" ከሚመኘው ሁሉ አንድም ነገር ሳያስቀር ይጠቅሳል። ደጋግሞም ይመኛል። አላህም ለርሱ እንዲህ ይለዋል: "ተመኘህን?" እርሱም "አዎን" ይላል። አላህም "የተመኘኸውንና ከተመኘኸው ጋር የርሱን አምሳያ ሌላም ይሰጥሃል።" ይለዋል።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «ለአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስጋ አመጡላቸው። ታፋውም ወደርሳቸው ቀረበ። ታፋ ያስደስታቸው ነበርና ከርሱ አንድ ጊዜ ከገመጡ በኃላ እንዲህ አሉ: "እኔ የትንሳኤ ቀን የሰዎች አለቃ ነኝ። ይህ ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁን? አላህ የመጀመሪያውንም የመጨረሻውንም ሰዎች አንድ ሜዳ ላይ ይሰበስባል። (ከመጠቅጠቃቸውም የተነሳ) የአንድ ተጣሪ ድምፅ ያሰማቸዋልም፤ አንድ ሰው አዳርሶ መመልከትም ይችላል። ፀሐይም ወደነርሱ ትቀርባለች። ሰዎችም የማይችሉትና የማይቋቋሙት ችግርና ጭንቅ ይደርስባቸዋል። ሰዎችም "የደረሰባችሁን አትመለከቱምን? ለናንተ ወደ ጌታችሁ ሄዶ የሚያማልድን አትፈልጉምን?" ይላሉ። ከፊላቸው ለከፊላቸውም "እባካችሁ አደም ጋር ሂዱ!" ይላሉ። አደም ዐለይሂ ሰላም ዘንድ ይመጡና "አንተ የሰው ዘር አባት፤ አላህ በእጁ የፈጠረህ፤ ከፈጠራቸው ነፍሶች አንዱን ነፍስ በውስጥህ የነፋብህ፤ መላእክቶችን እንዲሰግዱልህ ያዘዘልህና የሰገዱልህ ነህ። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ምን ያህል (ችግር) እንደደረሰብን አትመለከትምን? ለኛ ጌታህ ዘንድ አማልድልን" ይላሉ። አደምም "ጌታዬ ዛሬ የተቆጣው ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ነው። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። እኔን ከዛፏ ከለከለኝና አመፅኩት። ነፍሴ! ነፍሴ! ነፍሴ! ከኔ ውጪ ወደሌላ ሂዱ! እስኪ ወደ ኑሕ ሂዱ!" ይላቸዋል። ወደ ኑሕም በመሄድ "ኑሕ ሆይ! አንተ ወደ ምድር ነዋሪዎች የተላክ የመጀመሪያው መልክተኛ ነህ፣ አላህም አመስጋኙ ባሪያ ብሎ ጠርቶሃል። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ለኛ ጌታህ ዘንድ አማልድልን!" ይላሉ። ኑሕም "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። ለኔ የተሰጠችኝ አንድ ልመና ነበረች እርሷንም በህዝቦቼ ላይ አድርጌያታለሁ። ነፍሴ! ነፍሴ! ነፍሴ! ከኔ ውጪ ወደ ሌላ ሂዱ! እስኪ ወደ ኢብራሂም ሂዱ!" ይላቸዋል። ወደ ኢብራሂምም በመምጣት "ኢብራሂም ሆይ! አንተ የአላህ ነቢይና ከምድር ነዋሪዎች የአላህ ፍፁም ወዳጅ ነህ። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ለኛ ጌታህ ዘንድ አማልድልን!" ይላሉ። ኢብራሂምም "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። እኔ ሶስት ውሸቶችን ዋሽቼ ነበር። ነፍሴ! ነፍሴ! ነፍሴ! ከኔ ውጪ ወደሌላ ሂዱ! እስኪ ወደ ሙሳ ሂዱ!" ይላቸዋል። ወደ ሙሳም ይመጡና "ሙሳ ሆይ! አንተ የአላህ መልክተኛ ነህ፤ አላህ ከሰዎች ሁሉ መልዕክቱን በማሸከምና በማናገር የመረጠህ ነህ። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ለኛ ጌታህ ዘንድ አማልድልን!" ይላሉ። ሙሳም "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። እኔ መግደል ያልታዘዝኩትን ነፍስ ገድያለሁ። ነፍሴ! ነፍሴ! ነፍሴ! ከኔ ውጪ ወደሌላ ሂዱ! እስኪ ወደ ዒሳ ቢን መርየም ሂዱ!" ይላቸዋል። ወደ ዒሳም በመምጣት "ዒሳ ሆይ! አንተ የአላህ መልክተኛ ነህ፤ ወደ መርየም ባስተላለፋት ንግግር የተፈጠርክ፤ አላህ ከፈጠራቸው ነፍሶች መካከል አንዱ የሆንክ፤ በአንቀልባ ላይ ሆነህ ሰዎችን ያናገርክ ነህ። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ለኛ ጌታህ ዘንድ አማልድልን!" ይላሉ። ዒሳም "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። ስለዒሳ ምንም ወንጀል አልጠቀሰም። ነፍሴ! ነፍሴ! ነፍሴ! ከኔ ውጪ ወደሌላ ሂዱ! እስኪ ወደ ሙሐመድ ሂዱ!" ይላቸዋል። ወደ ሙሐመድም በመምጣት "ሙሐመድ ሆይ! አንተ የአላህ መልክተኛ ነህ፤ የነቢያት መደምደሚያ፤ አላህ ላንተ ያስቀደምከውንም ሆነ የሚመጣው ወንጀልህን ምሮሃል። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ለኛ ጌታህ ዘንድ አማልድልን!" ይላሉ። ወደ ዐርሽ ስር በመሄድም ለጌታዬ ሱጁድ አድርጌ እደፋለሁ። ከዚያም አላህ ከዛ በፊት ለአንድም ያልከፈተለትን የማመሰግንበትንና አሳምሬ የማወድስበትን አንዳች ቃላቶችን ይከፍትልኛል። ከዚያም "ሙሐመድ ሆይ! ራስህን ቀና አድርግ፤ ጠይቅ ይሰጥሃል፤ አማልድ ታማልዳለህ።" ይባላል። ራሴንም ቀና አደርግና "ጌታዬሆይ! ኡመቴ፤ ጌታዬ ሆይ! ኡመቴ፤ ጌታዬ ሆይ! ኡመቴ" እላለሁኝ። ለኔም "ሙሐመድ ሆይ! ከኡመትክ መካከል ሒሳብ (ምርመራ) የሌለባቸውን ከጀነት በሮች መካከል በቀኝ በር አስገባ። ከዛ ውጪ ባሉ በሮች ከሌሎች ሰዎች ጋር በጋራ ነው የሚገቡት።" እባላለሁኝ። ከዚያም እንዲህ አሉ "ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! በጀነት ሁለት መቃኖች መካከል ያለው ስፋት በመካና ሒምየር መካከል ያለውን ያህል ወይም ከመካ እስከ በስራ መካከል ያለውን ያህል ርቀት ነው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በአንድ የምግብ ጥሪ ላይ ከባልደረቦቻቸው ጋር ሳሉ ለርሳቸው የበግ ታፋ ቀረበላቸው። እርሳቸው ዘንድ ከበግ ስጋ ተወዳጁም እርሱ ነበር። ከርሷም በጥርሳቸው ጫፍ አንድ ግዜ ገመጡና እንዲህ በማለት አናገሯቸው: እኔ የትንሳኤ ቀን የአደም ልጆች አለቃ ነኝ። ይህንንም ያሉት የአላህን ፀጋ ለመናገር ነው። ቀጥለው "ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁን? የትንሳኤ ቀን ሰዎች ሰፊና ለጥ ያለ ዝርግ መሬት ላይ ይሰበሰባሉ። በውስጧ የተሰበሰቡትንም አንድ ተጣሪ ያሰማቸዋል፤ መሬቷ ቀጥ ስላለች አንድም ሰው ከተመልካች መሸሸጊያ ስለሌለው ተመልካች ከነርሱ መካከል አንድም ሳይሰወርበት አጠቃልሎ ያያቸዋል። ማለትም አንድ ሰው ቢያወራ ሌላኛው ሰው ይሰማዋል፤ አይንም ይመለከታቸዋል ማለት ነው። ፀሐይም ወደ ፍጡራን የአንድ ማይል ያህል ትቀርባለች። የማይቋቋሙትና የማይችሉት ጭንቅና ችግር ያጋጥማቸዋል። በምልጃ ነፃ የሚወጡበትን መንገድ ይፈልጋሉ። አላህም ለኢማን ባለቤቶች ወደ ሰዎች አባት አደም ዘንድ እንዲመጡ ያሳውቃቸውና አላህ ዘንድ ለነርሱ እንዲያማልዳቸው በመከጀል ወደርሱ በመምጣት ደረጃውን ያወሳሉ። ለርሱም "አንተ አላህ በእጁ የፈጠረህ፤ መላዕክቱንም ያሰገደልህ፤ የሁሉንም ነገር ስሞች ያሳወቀህ፤ ከፈጠራቸው ነፍሶች መካከል አንዱን በውስጥህ የነፋብህ የሰው ዘር አባት አደም ነህ።" ይላሉ። እርሱም አለመቻሉን ለማሳወቅ "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም።" በማለት ቀጥሎ ስህተቱን ይገልፅላቸዋል። እርሱም አላህ ዛፏን ከመብላት ከልክሎት መብላቱን ነው። ይልቁንም ነፍሴ ናት ምልጃ የሚገባት ይላቸዋል። ከኔ ውጪ ወደ ሌላ ሂዱ። ወደ ኑሕ ሂዱ ይላቸዋል። ወደ ኑሕም በመምጣት "አንተ የመጀመሪያ አላህ ወደ ምድር የላከው መልክተኛ ነህ። አላህም አመስጋኙ ባሪያ ብሎ ጠርቶሃል።" ይላሉ። ነገር ግን እርሱም እንደማይችል እንዲህ በማለት ያሳውቃቸዋል "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። ለኔ አንድ ዱዓ ነበረችኝ ህዝቦቼ ላይ አደረግኳት።" ይላል። ነፍሴ ናት ምልጃ የሚገባት ከኔ ውጪ ወደ ሌላ ሂዱ። ወደ ኢብራሂም ሂዱ ይላቸዋል። ወደ ኢብራሂምም በመምጣት "አንተ ምድር ውስጥ የአላህ ፍፁም ወዳጅ ነህ። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ጌታህ ዘንድ አማልድልን!" ይላሉ። እርሱም "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። እኔ ሶስት ውሸቶችን ዋሽቼያለሁ።" ይላቸዋል። ይህም ውሸት "አሞኛል" ማለቱ፣ "ይህ ታላቃቸው ነው የፈፀመው" ማለቱና ከንጉሱ ክፋት ለመዳን ለሚስቱ ሳራህ "እኔ ወንድምሽ እንደሆኑኩኝ ንገሪያቸው።" ማለቱን ነው። በእውነታው ስናየው እነዚህ ሶስት ቃላቶች ዘይቤያዊ ንግግሮች እንጂ ውሸት አይደሉም። ነገር ግን ይዘቷ የውሸት ይዘት ያላት ስለምትመስል ነፍሱን አሳንሶ ማማለድን ፈራ። አላህን እጅግ አዋቂ የሆነና ወደርሱ እጅግ ቅርብ የሆነ ሰው አላህን እጅግ በጣም ይፈራል። ስለዚህም ነፍሴ ናት ምልጃ የሚገባት። ከኔ ውጪ ወደ ሌላ ሂዱ ወደ ሙሳ ሂዱ ይላቸዋል። ወደ ሙሳ በመምጣትም "ሙሳ ሆይ! አንተ የአላህ መልክተኛ ነህ፤ አላህ ከሰዎች በተልእኮውና እርሱን በማናገር ያበለጠህ። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ጌታህ ዘንድ አማልደን።" ይላሉ። ሙሳም "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። እኔ በመግደል ያልታዘዝኩትን ነፍስ ገድያለሁ። ነፍሴ ናት ምልጃ የሚገባት። ከኔ ውጪ ወደሆነ ወደ ሌላ ሂዱ። ወደ ዒሳ ቢን መርየም ሂዱ።" ይላቸዋል። ወደ ዒሳም በመምጣት "ዒሳ ሆይ! አንተ የአላህ መልክተኛ ነህ፤ ወደ መርየም ባስተላለፋት ቃሉ የተፈጠርክና አላህ ከፈጠራቸው ነፍሶች መካከል አንዱ ነህ፤ በአንቀልባ ላይ ህፃን ሆነህ ሰዎችን አናግረሃል። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ጌታህ ዘንድ አማልደን።" ይላሉ። እርሱም "ጌታዬ ከዚህ በፊት ተቆጥቶ የማያውቀውን አይነት ቁጣ ዛሬ ተቆጥቷል። ዛሬ የተቆጣውን አይነት ቁጣም ከዚህ በኋላ መቼም አይቆጣም። (ምንም ወንጀል ሳይጠቅስ ነፍሴ ናት ምልጃ የሚገባት። ከኔ ውጪ ወደ ሌላ ሂዱ። ወደ ሙሐመድ ሂዱ።" ይላቸዋል። ወደ ሙሐመድም በመምጣት "ሙሐመድ ሆይ! አንተ የአላህ መልክተኛ፤ የነቢያት መደምደሚያ፤ አላህ ላንተ ያሳለፈከውም ሆነ የሚመጣውን ወንጀል ምሮሃል። ያለንበትን ሁኔታ አትመለከትምን? ለኛ ጌታህ ዘንድ አማልድልን!" ይላሉ። እኔም ከዐርሽ ስር እመጣና ለጌታዬ ሱጁድ እደፋለሁ። ከዚያም አላህ ከዛ በፊት ለአንድም ያልከፈተለትን የማመሰግንበትንና አሳምሬ የማወድስበትን አንዳች ቃላቶችን ይከፍትልኛል። ከዚያም "ሙሐመድ ሆይ! ራስህን ቀና አድርግ፤ ጠይቅ ይሰጥሃል፤ አማልድ ታማልዳለህ።" ይባላል። ራሴንም ቀና አደርግና "ጌታዬ ሆይ! ኡመቴ፤ ጌታዬ ሆይ! ኡመቴ፤ ጌታዬ ሆይ! ኡመቴ" እላለሁኝ። ምልጃዬም ተቀባይነት ታገኛለች። ለርሳቸውም "ሙሐመድ ሆይ! ከኡመትክ መካከል ሒሳብ (ምርመራ) የሌለባቸውን ከጀነት በሮች መካከል በቀኙ በር አስገባ። ከዛ ውጪ ባሉ በሮች ከሌሎች ሰዎች ጋር በጋራ ነው የሚገቡት።" ይባላሉ። ቀጥለው እንዲህ አሉ "ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁኝ! የጀነት በሮች ዳርና ዳር ከመካ እስከ የመን ሰንዓ ድረስ ያለውን ይደርሳል። ወይም ከመካ እስከ ቡስራ ሻም መካከል ያለውን ይደርሳል።" ይህም የሐውራን ከተማ ነው።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የሴት ልጅ አለባበስን የሚለብስን ወንድና የወንድ ልጅ አለባበስን የምትለብስ ሴትን ረገሙ።"
رواه النسائي في الكبرى وابن ماجه بمعناه وأحمدነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በአኳኋኑም ይሁን በቀለሙም፣ በአይነቱም ይሁን በአለባበስ መንገዱም፣ በመዋቢያነቱ (ማስጌጫዎች)ና በመሳሰሉ መንገዶች ሴት ልጅ የተለየችበት በሆነ ልብስ የሚመሳሰል ወንድ ላይ ከአላህ እዝነት እንዲባረርና እንዲርቅ ዱዓእ አድርገዋል። ወይም ልክ እንደዚሁ ወንድ ልጅ በተለየበት ልብስ የምትመሳሰል ሴት ልጅ ከአላህ እዝነት እንዲባረሩና እንዲርቁ ዱዓ አደረጉ። ይህም ከትላልቅ ወንጀሎች የሚመደብ ከባድ ወንጀል ነው።