





























Hadeeth Cards
Da'wa cards that highlight great meanings from the noble prophetic hadiths in a simple style and attractive display that helps the Muslim to have a deeper understanding of his religion in an easy way
All
ከዑቅባህ ቢን ዓሚር አልጁሀኒይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው፦ "ወደ አላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተወሰኑ ሰዎች መጡ። ከዘጠኙ ጋር ቃልኪዳን ተጋቡና ከአንዱ ጋር ቃልኪዳን ከመጋባት ተቆጠቡ። ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከዘጠኙ ጋር ቃልኪዳን ተጋብተው ይህንን ለምን ተዉ?' አሉ። እርሳቸውም 'እርሱ ላይ ሒርዝ ስላለ ነው።' አሉ። (ይህንን ሲሰማ) እጁን አስገባና ቆረጠው። እርሳቸውም ቃልኪዳን ተጋቡትና 'ሒርዝ ያንጠለጠለ ሰው በርግጥም አጋርቷል!' አሉ።"
አሕመድ ዘግበውታል።የተወሰኑ ጭፍሮች ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መጡ። ብዛታቸውም አስር ነበሩ። ከነርሱ መካከል ከዘጠኙ ጋር በኢስላም ላይና እርሳቸውን በመከተል ላይ ቃል ተጋቡና ከአስረኛው ጋር ቃልኪዳን ሳይጋቡ ቀሩ። የዚህን ምክንያት የተጠየቁ ጊዜም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: እርሱ ላይ ሒርዝ አለበት። (ሒርዝ) ማለት፦ ዓይንን ወይም ጉዳትን ለመከላከል ከጨሌና ከሌላም ነገር የሚሰራ የሚታሰር ወይም የሚንጠለጠል ነው። ሰውዬውም ወደ ሒርዙ ስፍራ እጁን ከቶ በመቁረጥ ከሒርዙ ጠራ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የዚህ ጊዜ ቃልኪዳን ተጋቡት። ከሒርዝ ለማስጠንቀቅና ብይኗን ለመግለፅም እንዲህ አሉ: "ሒርዝ ያንጠለጠለ ሰው በርግጥም አጋርቷል።"
ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዐስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንደተላለፈው: እርሳቸው መስጂድ በሚገቡ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር: "አዑዙ በላሂል ዐዚም ወቢወጅሂሂል ከሪም ወሱልጧኒሂል ቀዲም ሚነሽ-ሸይጧኒ ረጂም" "የሚሉት ይህን ብቻ ነውን? " ተብሎ ተጠየቀ። "አዎን" አልኩኝ። "ይህን ያለ ጊዜም ሸይጧን 'የቀረውን የቀኑን ክፍል ከኔ ተጠበቀ።' ይላል።" ትርጉሙም "ታላቅ በሆነው አላህ፣ በተከበረው ፊቱ፣ መጀመሪያም በሌለው ስልጣኑ ከተረገመው ሰይጣን እጠበቃለሁ።"
አቡዳውድ ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መስጂድ በሚገቡ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር: (አዑዙ ቢላሂል ዐዚም) በአላህና በባህሪያቱ እከለላለሁ፣ እጠበቃለሁም። (ወቢወጅሂሂል ከሪም) ሰጪና ቸር በሆነው፤ (ወሱልጧኒሂ) ከፍጡራኖች መካከል በፈለገው ላይ ባለው አሸናፊነቱ፣ በችሎታውና በበላይነቱ (አልቀዲም) የመጀመሪያና ዘላለማዊ በሆነው፤ (ሚነሽ-ሸይጧኒ ረጂም) ከአላህ እዝነት የተባረረና የራቀ ከሆነው ሰይጣን እጠበቃለሁ። ማለትም: አላህ ሆይ! ከሰይጣን ጉትጎታ፣ ከማጥመሙ፣ ከእርምጃዎቹ፣ ውስጣችን ላይ ከሚፈጥረው ውልታና ማጥመም ጠብቀኝ ማለት ነው። ይህም የጥመት ምክንያትና ለመሀይምነትና መጥመም የሚያነሳሳው (ጠንሳሽ) እርሱ ስለሆነ ነው። ለዐብደላህ ቢን ዐምርም "ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያሉት ይህን ብቻ ነውን?" ተብሎ ተጠየቀ። እርሱም "አዎን" አለ። መስጂድ የሚገባ ሰው ይህን ዱዓ ካለም ሰይጣን እንዲህ ይላል: ይህ መስጂድ የገባው ሰው ነፍሱን በአጠቃላይ ወቅቱ ቀኑንም ምሽቱንም ከኔ ጠብቋታል።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ተባረከ ወተዓላ ለጀነት ነዋሪዎች እንዲህ ይላቸዋል: 'እናንተ የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!' እነርሱም 'ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል' ይላሉ። አላህም 'ተደሰታችሁን?' ይላቸዋል። እነርሱም 'ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸን እንዴት ነው የማንደሰተው?' ይላሉ። እርሱም 'እኔ ከዚህም የተሻለ ነገር እሰጣችኋለሁ።' ይላል። እነርሱም 'ጌታችን ሆይ! ከዚህ የተሻለ ምን አይነት ነገር ይኖራል?' ይላሉ። አላህም 'በናንተ ላይ ውዴታዬን አሰፍናለሁ። በናንተ ላይ ከዚህ በኋላ መቼም አልቆጣም።' ይላቸዋል።"»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ ((የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ለጀነት ነዋሪዎች በውስጧ እያሉ እንዲህ እንደሚል ነገሩን: "የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!" እነርሱም "ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል" በማለት ለርሱ ይመልሳሉ። እርሱም ለነርሱ: ተደሰታችሁን? ይላቸዋል። እነርሱም: አዎን ተደስተናል። ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸን እንዴት ነው የማንደሰተው? ይላሉ። አላህም: ከዚህ የተሻለ ነገር ልስጣችሁን? ይላቸዋል። እነርሱም: ጌታችን ሆይ! ከዚህ የተሻለ ነገር ምን አለና? ይላሉ። እርሱም: ዘውታሪ የሆነውን ውዴታዬን አሰፍንባችኋለሁ። ከዚህ በኋላ በናንተ ላይ መቼም አልቆጣም። ይላቸዋል።
ከአቡዘር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምተዋል: "አንድ ሰው ሌላን ሰው በአመፀኝነትም ሆነ በከሃዲነት አያነውረውም ባለቤቱ እንደዚያ ካልሆነ ወደርሱ ብትመለስ እንጂ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለሌላ ሰው "አንተ አመፀኛ" ወይም "አንተ ከሃዲ" ያለ ሰው ያ ሰው እንደተናገረው ካልሆነና ለተጠቀሰው ባህሪ የተገባ ካልሆነ ንግግሩ ወደራሱ የሚመለስ መሆኑን አስጠነቀቁ። እንደተናገረው ከሆነ ግን በተናገረው ንግግር እውነተኛ ስለሆነ አንድም ነገር ወደርሱ አይመለስበትም።
ከአቡ ጦልሓ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "መላዕክቶች ውሻና ስዕል ወዳለበት ቤት አይገቡም።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የእዝነት መላዕክቶች ውሻና ነፍስ ያላቸው የፍጡራን ስዕል ወዳለበት ቤት እንደማይገቡ ተናገሩ። ይህም ነፍስ ያለበት ምሥል አስከፊ ወንጀል ስለሆነ፤ ከአላህ አፈጣጠር ጋር መፎካከር ስለሆነ፤ የሽርክ መዳረሻም ስለሆነ፤ አንዳንዶቹ ምሥሎችም ከአላህ ውጪ የሚመለኩ ምሥሎች ስለሆኑ ነው። ውሻ ያለበት ቤት ከመግባት የመቆጠባቸው ምክንያት ደግሞ: በብዛት ነጃሳ ስለሚመገብ፤ አንዳንዶቹም ሸይጧን ተብለው ስለተጠሩ ነው። መላዕክት ደግሞ የሸይጧን ተቃራኒ ናቸው። በተጨማሪ የውሻ ሽታ አፀያፊ ስለሆነ ነው። መላዕክት ደሞ መጥፎ ሽታን ይጠላሉ። ስለዚህ ውሻን ማሳደግ ተከለከለ። የሚያሳድግ ሰውም የእዝነት መላዕክት ቤቱ ባለመግባታቸው፤ ለቤቱ ዱዓእ ባለማድረጋቸው፤ ለርሱ ምህረት ባለመጠየቃቸው፤ ለርሱና ለቤቱ በረከት ባለመጠየቃቸው፤ የሸይጧንን ጉዳት ከርሱ ላይ ባለመከላከላቸው ተቀጣ።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "መላእክት ውሻ እና ቃጭል ካላቸው መንገደኞች ጋር አብረው (አይጎዳኙም) አይሄዱም።"
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በጉዞ ወቅት በመካከላቸው ውሻ ካለ ወይም በእንስሶች ላይ የሚንጠለጠለውና ሲንቀሳቀስ ድምፅ የሚያወጣው ቃጭል ካለ መላእክት ከነርሱ ጋር በወዳጅነት እንደማይጎዳኙ ተናገሩ።
ከዐብዲረሕማን ቢን ሰሙራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "በጣዖታትም ሆነ በአባቶቻችሁ አትማሉ።"»
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አጋርያኖች ከአላህ ውጪ ያመልኳቸው በነበሩትና ለክህደታቸውና ጥመታቸው ምክንያት በነበሩት ጣዖታት ከመማል ከለከሉ። በድንቁርና ዘመን የዐረቦች ልማድ ከነበሩት ነገሮች መካከል ለመኩራራትና ለማላቅ በአባቶቻቸው መማል ነበርና ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአባቶች ከመማልም ከለከሉ።
ከቡረይዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "(በአማና) በአደራ የማለ ሰው ከኛ አይደለም።"
አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአደራ ከመማል ከለከሉም አስጠነቀቁም። ይህን ድርጊት የፈፀመም ከኛ አይደለም አሉ።
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ተሰባስበን ተቀምጠን ነበር። ከኛ ጋር ከነበሩት መካከልም አቡበከርና ዑመር ነበሩ። የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከመካከላችን ተነስተው ሄዱ። ወደ እኛ ሳይመለሱም ዘገዩ። ከኛ ርቀው ባሉበት ጥቃት ይደርስባቸዋል ብለን በመፍራታችንም ደንግጠን ቆምን። ደንግጨ የተነሳሁት የመጀመሪያ ሰው እኔ ነበርኩኝ። የአላህ መልክተኛን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለመፈለግም ወጣሁ። በመፈለግ ሳለሁም ባለቤትነቱ ከአንሷሮች መካከል ለአንድ የበኒ ነጃር ተወላጅ የሆነ የአትክልት ግቢ ጋር ደረስኩ። የመግቢያ በሩን ለማግኘትም አጥሩን ዞርኩት። በሩንም አላገኘሁም። ድንገት ግን ከግቢ ውጪ ከሚገኝ ጉድጓድ ወደ አትክልቱ ግቢ ውስጥ የሚገባ ቦይ አገኘሁ። ሰውነቴን ሸምቅቄ የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ ገባሁ። እርሳቸውም "አቡ ሁረይራ" አሉኝ። እኔም "አቤት የአላህ መልክተኛ ሆይ!" አልኳቸው። "ምን ሆነህ ነው?" አሉኝ። እኔም "እርሶ በመካከላችን ነበሩ። ከመካከላችን ተነስተው ሄዱና ዘገዩብን። ከኛ ርቀው ባሉበት ጥቃት እንዳይደርስቦት ፈርተን ደነገጥን። መጀመሪያ የደነገጠውም ሰው እኔ ነበርኩኝ። ይህ የአትክልት ግቢ ዘንድ መጣሁ። ቀበሮ ሰውነቱን ሸምቅቆ እንደሚገባውም ሰውነቴን ሸምቅቄ ገባሁ። የተቀሩት እርሶን የሚፈልጉ ሰዎች ከኋላዬ ናቸው።" አልኳቸው። እርሳቸውም "አቡ ሁረይራ ሆይ! … " አሉኝና ሁለት ጫማቸውን ሰጥተው እንዲህ አሉኝ "እነዚህን ሁለት ጫማዎቼን ያዝና ሂድ! ከዚህ የአትክልት ግቢ ውጪ የምታገኘውን ላኢላሃ ኢለሏህን ከልቡ አምኖበት የሚመሰክርን ሰው በጀነት አበስረው።" መጀመሪያ ያገኘሁትም ዑመርን ነበር። እርሱም "ምንድናቸው እነዚህ ጫማዎች?" አለኝ። እኔም "እነዚህ የረሱል ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጫማዎች ናቸው። እነዚህን ጫማዎች ሰጥተው ከአጥሩ ውጭ ያገኘሁትን ላኢላሃ ኢለሏህን ከልቡ አምኖ የሚመሰክርን ሰው በጀነት እንዳበስረው ልከውኝ ነው።" አልኩኝ። ዑመርም በሁለት እጆቹ ደረቴን መታኝና በመቀመጫዬ ወደቅኩ። እንዲህም አለኝ "ተመለስ አንተ አቡ ሁረይራ" እኔም ወደ አላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንባ እየተናነቀኝ ተመለስኩኝ። ዑመርም ከኋላየ ነበር ሳስተውልም እኔን ተከትሎ መጥቷል። የአላህ መልክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ምን ሆንክ አንተ አቡ ሁረይራ!" አሉኝ። እኔም "ዑመርን አገኘሁት። የላኩኝን ጉዳይም ስነግረው ደረቴ ላይ መቶኝ በመቀመጫዬ ወደቅኩ። ተመለስም አለኝ።" አልኳቸው። የአላህ መልክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "አንተ ዑመር ለዚህ ተግባርህ ምን አነሳሳህ?!" አሉት። እርሱም "እናትና አባቴ ለርሶ ፊዳ ይሁኑና የአላህ መልክተኛ ሆይ! አቡ ሁረይራን ላኢላሃ ኢለሏህን ከልቡ አምኖበት የሚመሰክር ሆኖ ያገኘውን ሰው በጀነት እንዲያበስር ልከውታልን?" አለ። እርሳቸውም "አዎ" አሉ። እርሱም "እንዲህ አያድርጉ። ሰዎች በርሷ ላይ ጥገኛ ይሆናሉ (ይሳነፋሉ) ብዬ እፈራለሁ። ተዉዋቸው ይስሩ።" አለ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ተዉዋቸው (አትንገሯቸው)" አሉ።»
ሙስሊም ዘግበውታል።ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከባልደረቦቻቸው ጋር ተቀምጠው ነበር። ከመካከላቸውም አቡበከርና ዑመር ይገኙ ነበር። ነቢዩም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ተነስተው ሄዱ። ከዚያም ሳይመለሱ ዘገዩባቸው። የመማረክ ወይም ሌላ የጠላት ጉዳት ደርሶባቸው እንዳይሆን ስጋት አደረባቸው። ሶሐቦችም ረዲየሏሁ ዐንሁም - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ደንግጠው ቆሙ። መጀመሪያ የደነገጠውም አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - ነበር። እርሳቸውን እየፈለገም የአንድ የበኒ ነጃር የሆነ ሰው አትክልት ግቢ ጋር መጣ። ክፍት በር ለማግኘትም አጥሩን ዞረው። በር ግን አላገኘም። ነገር ግን ግድግዳው ላይ ውሃ የሚገባበት ትንሽ ቀዳዳ አገኘና ሰውነቱን ሰብሰብ አድርጎ ወደ ውስጥ ገባ። ነቢዩንም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አገኛቸው። እርሳቸውም "አንተ አቡ ሁረይራ?" አሉት። እርሱም "አቤት" አለ። እርሳቸውም "ምን ሆነህ ነው?" አሉት። አቡ ሁረይራም "እርሶ በመካከላችን ነበሩ። ከመካከላችን ተነስተው ሄዱና ዘገዩብን። ከኛ ርቀው ባሉበት ጥቃት ደርሶቦት ፈርተን ደነገጥን። መጀመሪያ የደነገጠውም ሰው እኔ ነበርኩኝ። ይህ የአትክልት ግቢ ዘንድ መጣሁ። ቀበሮ ሰውነቱን ሸምቅቆ እንደሚገባውም ሰውነቴን ሸምቅቄ ገባሁ። የተቀሩት እርሶን የሚፈልጉ ሰዎች ከኋላዬ ናቸው።" ነቢዩም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለእውነተኝነቱ ምልክት የሚሆን ሁለት ጫማቸውን ሰጡትና እንዲህ አሉት: "እነዚህን ጫማዎች ይዘህ ሂድ። ከዚህ ግቢ ውጪ ያገኘኸውን ላኢላሃ ኢለሏህን ብሎና ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ከልቡ አምኖበት የሚመሰክርን ሰው እርሱ የጀነት እንደሆነ ንገረው።" መጀመሪያ ያገኘውም ዑመርን ነበር። እርሱም "ምንድናቸው እነዚህ ጫማዎች?" አለው። እርሱም "እነዚህ የረሱል -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጫማዎች ናቸው። እነዚህን ጫማዎች ሰጥተው ላኢላሃ ኢለሏህን ከልቡ አምኖ የሚመሰክር ሆኖ ያገኘሁትን ሰው በጀነት እንዳበስረው ልከውኝ ነው።" አለ። ዑመርም በእጆቹ የአቡ ሁረይራን ደረት መቱትና በመቀመጫው ወደቀ። እንዲህም አለው: "አንተ አቡ ሁረይራ ተመለስ!" እርሱም "ወደ ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ደንግጬ፣ ፊቴ ተለዋውጦና እንባ ተናንቆኝ ተመለስኩ። ዑመርም ከኋላዬ ተከትሎኝ መጣ።" ነቢዩም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "አንተ አቡ ሁረይራ ምን ሆነህ ነው?" አሉት። እኔም "ዑመርን አገኘሁት። የላኩኝን ጉዳይም ስነግረው ደረቴ ላይ መቶኝ በመቀመጫዬ ወደቅኩ። ተመለስም አለኝ።" አልኳቸው። ነቢዩም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "አንተ ዑመር ሆይ! ለዚህ ተግባርህ ምን አነሳሳህ?!" አሉት። ዑመርም "እናትና አባቴ ለርሶ ፊዳ ይሁኑና የአላህ መልክተኛ ሆይ! አቡ ሁረይራን ላኢላሃ ኢለሏህን ከልቡ አምኖበት የሚመሰክር ሆኖ ያገኘውን ሰው በጀነት እንዲያበስር ልከውታልን?" አለ። እርሳቸውም "አዎ" አሉ። እርሱም "እንዲህ አያድርጉ። ሰዎች ስራ ሳይሰሩ እርሷን በማለታቸው ላይ ብቻ ጥገኛ ይሆናሉ (ይሳነፋሉ) ብዬ እፈራለሁ። ተዉዋቸው ይስሩ።" አለ። ነቢዩም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "እንዲያ ከሆነ ተዉዋቸው።" አሉ።